Tuesday, June 18, 2013

ጥቂት ስለ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች

በአለማየሁ ጥበቡ
 ክፍል አንድ
 በምንም ተከሰስ ከመታሰር አትድንም ፡፡ ህግና ህገመንግስት በወረቀት ላይ ቢኖርም በትክክል አይሰራበትም ላም አለኝ
በሰማይ ልትለው ትችላለህ ፈፅሞ እንዳታስብ ሰባዊ መብት ምን እንደሆን እዚህ ምድር ላይ አይታወቅም ፡፡በየጉራንጉሩ
ያሉ እስርቤት ሳይሆኑ መታጎርያ ቤቶች ቁጥራቸው ሀገሪቱ ላይ ካሉ ሆስፒታሎችና መስርያ ቤቶች ይበልጣሉ፡፡ በነዚህ
መታጎርያ ቤቶች ታስሮ ምንም ሳይሆን ከነጤናው የወጣ ሰው በጣም እድለኛ ምናልባትም የፈጣሪ ሸሪክ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ እስር ቤቶች በሁለት ይከፈላሉ እነሱም ፡-
1...ፈዴራል መንግስት ስር ያሉ እስር ቤቶች 1.
- ቃሊቲ ማረምያ ቤት
- ዝዋይ ማረምያ ቤት
-ሸዋ ሮቢት ማረምያ ቤት
- ድሬደዋ ማረምያ ቤት
2... በክልል መንግስት ስር ያሉ ቁጥራቸው የትየለሌ የሆኑ እስር ቤቶች ናቸው 2.
አዲስ አበባ ላይ ወንጀል የሰራም ያልሰራም ቢሆን ብቻ የመታሰር እጣ የወጣበት ሰው እንደወንጀሉ የሚታሰርበት ቦታ
ይለያያል ከዚህ በታች ያሉት እስር ቤቶች ጊዛዊ እስር ቤቶች ናቸው ፡፡ከፍተኛው ፍርድ ቤት /ልደታ ያለው ከፍተኛ ችሎት /
እስክትቀርብ ድረስ ጊዛዊ ምርመራ የሚደረግባቸው ናቸው
/ ሀ ፤ለ እና ሐ በደንብ ተመልከት/
ሀ.... ለምሳሌ ጫማ ሲሰርቅ የተያዘ ሰው /የአንድ እግር ጫማም ሊሆን ይችላል/ የሚታሰረው በየቀበሌው ባለ እስር ቤት ነው ፡
፡ቀላል ወንጀሎች ስርቆት፤ስድድቦሽ ፤ወዘተ እንደወንጀላቸው መጠን በየወረዳው ባሉ ዳኞች ይዳኛሉ ፡፡ ዋስ ቶሎ ያገኛሉ
ይገባሉ ይወጣሉ ይህ አይነቱ ወንጀል እና ወንጀለኛ መንግስትን ፈፅሞ አሳስቦት አያቅም ፡፡
ለ.... ወንጀሉ ከበድ ያለነው ከተባለ ለምሳሌ ሰው መግደል ፤ከባባድ ስርቆቶች ፤አስገድዶ መድፈር፤ በቼክ ሰውን ማጭበርበር ፤
ከባባድ ማታለሎች ወዘተ የመሰሉት ወንጀሎች ላይ የተሰማራ ሰው የሚታሰረው ሶስተኛ የሚባለው እስርቤት ነው ይህ እስር
ቤት ግማሽ አካሉን ለማእከላዊ ሰጥቶ ፕያሳ ምድር ላይ የሚገኝ ዘግናኝ እና አስፈሪ እስር ቤት ነው ፡፡ ያረከውንም
ያላረከውንም በዱላ ብዛት የምታምነበት ቤት ይሄ ነው፡፡ በቀላል በበሩ ትገባለህ መውጫዋን ግን አታቀውም፡፡ በትንሹ
ምርመራ ላይ እስከ ስድስት ወር ልትቆይ ትችላለህ፡፡ለይስሙላ ፍርድ ቤት ይወስዱሀል ያመጡሀል ምክንያቱም ህገ
መንግስቱ ላይ
አንቀጽ 19 /የተያዙ ሰዎች መብት/
ቁጥር 3 ‹‹የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰአት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው ፡፡››
ይላል ስለዚህ ትሄዳለህ መርማሪው ምርመራዬን አለጨረስኩም ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ ይላል ዳኛውም የተቀመጠው ለዚሁ
ነው ተጨማሪ ቀን በደንብ ይሰጠዋል፡፡በደንብ ትታሻለህ መረጃው ሲደልብ ከፍተኛ ፍርድቤት ፋይልህ ይላካል አቃቢ ህግ
ጥሩ አንቀፅ ከፍቶ ዳኛ ፊት ያቀርብሀል፡፡ በስድስት ወር ምርመራ ምንም ካላገኙብህ በነፃና ካሳ ሰጥተው አይሸኙህም እንዲህ ካደረጉማ ኢትዮጵያም ትከስራለች ሀገሪቷ ላይም ህግ የለም ይባላል ስለዚህ በመታወቅያ ዋስ ይፈቱሀሀል ይህ ማለት ምን
ማለት ነው እስከግዜው ተፈተሃል ማለት ነው፡፡
ሐ.. . . ሌላኛው እስር ቤት ማዕከላዊ የሚባለው ነው
ከመንግስት ጋር ተቃርነሃል? የሀገርን ጥቅም እነሱ እንደሚሉት ለሌላ ሀገር አጋልጠሀል ?ፖለቲከኛነት ተጠናውቶሀል ? እቺን
የጥጋብና የፈንጠዝያ ሀገር ደሃ ናት ብለሃል? የዜጎች መብት አለተከበረም ብለሀል ? የመናገር መብቴ ይከበርልኝ ብለሀል?
ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመሀል ?
በነፃ ፕሬስ አለ ባይነት መንግስትን ወይ ባለስልጣኑን ተችተሀል? እነዚህንና የነዚህን ተዛማች ተግባሮችን ካረክ የትም
አትታሰርም እድሜ ለማዕከላዊ እስር ቤት ፡፡ ምርመራህ እስኪያልቅና ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እስትቀርብ ጥፍርህ
ይነቀላል ብልትህ ይመግላል አካልህ በዱላ ብዛት ይበጣጠሳል ቶርች ትገለበጣለህ ይሄ ሁሉ እናት ሀገርህ ምድር ላይ ነው
የሚሆነው ያውም ባንተው ዜጎች ፡፡
በ ሀእና ለ /የ ሐ አላቅም/ እስር ቤቶች ካቦዎች አሉ /እስረኛን የሚያስተዳድሩ እስረኞች / እንደገባህ ያስቀምጡህ እና በምን
እንደታሰርክ ይጠይቁህ እና አይዞህ ብለው የቤት መዋጮ ስጥ ይሉሀል ካለህ እስከ ሶስት መቶም ልትሰጥ ትችላለህ ይሄ ብር
ልቃ አጣቢዎች ለቤት አፅጂዎች ለሽንት ደፊ ቅጥረኛ እስረኞች የሚሰጥ ነው ይልሀል ካቦው ፡፡ ሽንት ዲፋዎች ማለት
እስረኞቹ ለሊት በትልቅ ባሊ ሲሸኑ ያደሩትን ሽንት መደፋ ማለትነው ለዚህም አገልግሎቱ ይከፈለዋል፡፡ ካቦው ሲጠይቅህ
ገንዘብ ከሌለህና ጠያቂህ ሲመጣ ተቀብለህ የማትሰጥ ከሆነ እስረኛው የበላበትን እቃ ታጥባለህ ሽንት ትደፋለህ ቤት
ታፀዳለህ ይሄን እናዳታደርግ ከ 50 ብር ጀምሮ ለካቦው ስጠው ፡፡ካቦው ተሰሚነት አለው፡፡ከሱ ጋር መጣላት የለብህም፡፡
እንግዲህ ከሶስቱም እስር ቤቶች ማለትም ከ ሀ፤ለ እና ሐ ግዚያዊ እስር ቤቶች ምርመራህን ጨርሰህ ወደ ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ከቀረብክ በኃላ በዛኑ ቀን አልያም በማግስቱ ወደ ቃሊቲ ማረምያ ቤት ትላካለህ እድለኛ ከሆንክ ፤ገንዘብ ካለህ ፤ ጥሩ
ዘመድ ካለህ ምንም ወንጀል ስራ ‹‹ ገንዘብ ሲናገር ህግ ዝም ይላል›› ይባላል ከነተረቱ ስለዚህ ዋስትና ይፈቀድልህና ቃሊቲ
ሳትወርድ ከውጪ ሆንሀ ክስህን ትከታተላለህ ፡፡ የኔ ብጤው ምስኪን ይህን እድል በጆሮው ከመስማት በቀር ሆኖለት
አያቅም ቃሊቲ መውረድ ግድ ነው፡፡
ቃሊቲ ማረምያ ቤት /የፈዴራል መንግስት እስር ቤት/
የሚገኘው ቃሊቲ ነው ፡፡ በሰፊ መሬት ላይ የተሰራ ሲሆን አሁን ያለው መመንግስት ነው የሰራው ፡፡ ደፋር እስረኛ ካለ አጥሩ
አያሳስብም ህብረት ካለ እስር ቤቱ ለማምለጥ ቀላል ነው ፡፡ ግን ህብረት የለም አንድነት በዘፈን ካልሆነ አይታወቅም አንዱ
አንዱን ይፈራል ፡፡እንዴት አንፈራራ ? በስንት ዱላ እና ቶርች ከግዚያዊ እስር ቤት ወደዚህ የመጣ ምስኪን ታሳሪ ባይፈራ
አይገርምም ፡፡
ቃሊቲ ብዙ ዞኖች አሉት ዝሆን ስል እንስሳውን እንዳይመስልህ ቀጠናዎች /ግቢዎች /አሉት በአንዱ ቃሊቲ ውስጥ ሌላ
ስድስት ወይ ሰባት ግቢዎች አሉት እያልኩህ ነው፡፡ አንደኛው ጊቢ የሴቶች ክልል የሚባለው ሲሆን የተቀሩት የዎንዶች ነው
እኔ ከቃሊቲ ልለቅ አካባቢ ሌላም ዞኖዎች ሳይጨመር አይቀርም ፡፡ትንንሽ ግቢዎችም እንዳሉት ሰምቼያለሁ፡፡በአንድ ቀን
ግቢውን ዞረህ አጨርሰውም፡፡
ከሀ፤ከለ፤ከሐ ጊዛዊ እስር ቤቶች ወደ ቃሊቲ በመኪና ትወሰዳለህ ግቢው ጋ ስትደርስ አጥሩ የሽቦ ሆኖ በሩ በትልቅ ግንብ
የተሰራ ነው በትላቅ አርማም ቃሊቲ ማረምያ ቤት የሚል ከበሩ ላይ ተሰቀሏል ፡፡ እንደገባህ ከመኪና እየሰደቡና እየገላመጡ
ትወርዳለህ ስትወርድ ደሳሳ ቢሮዎች ትልልቅ እንጨት የያዙ ቦታዎች ታያለህ ይህ በስተቀኝ እና ፊት ለፊት ያለ ሲሆን
በስተግራ ያንበሳ አጥር የመሰለ በሽቦ አጥር የተከለለ ቦታ ታያለህ አይዞህ እዚህ ውስጥ አትታሰርም ይሄ የታጠረ ቦታ
በቀጠሮህ ቀን ፍርድቤት ልትሄድ ስትል የምትሰበሰብበት ቦታ ነው፡፡ተቆጥረኽ ከዚህ ቦታ መኪና ላይ ተጭነህ ፍርድቤት ትሄዳለህ ስትመለስም ከዚሁ ቦታ ተቆጥረኽ ትገባለህ ፡፡በዚህ ለአይን በሚያደክም ግቢ ውስጥ ት/ቤቶች ፤ትንሽ ክሊኒክ፤የምግብ ማብሰያ ቤቶች ፤ ወርክ ሾፖች አሉ፡፡ከመኪናው እንደወረድክ እቃህን አሲዘው አሰልፈው በየተራ በስተቀኝ ካለ
ቢሮአቸው /ቆርቆሮ በቆርቆሮ/ ውስጥ ትገባለህ አንድ ከማርጀት አልፈው የሻገቱ ሰውዬ ከውስጥ ይጠብቁሀል እንደቆምክ
ስምህን ይጠይቁሀል ለመፃፍ ስለሚቸግራቸው ስምህን ደጋግመህ መናገር ግድ ነው፡፡ ታጋይ ስለሆኑ መሰለኝ ጡረታ
ያልወጡት፡፡ በተለይ ለመፃፍ አስቸጋሪ ስም ካለህ ትሰደባለህ ከዛም በድሮ ካሜራ የእውነት ይሁን የውሸት አላቅም ፎቶ
ያነሱሀል፡፡እዚህ ቢሮ ውስጥ የመጨረሻው ነገር ሎሚ የሚያክል መዳኒት መዋጥ ነው፡፡ እንዳትኮረሽም ይሉሀል ያን ትልቅ
መድሀኒት መዋጥ ግደታ ነው፡፡ባረጀ ጣሳ ውሀ ያቀብሉሀል እየዘገነነህ መዳኒቱ ከጉሮሮህ እንዲወርድለህ ስትል በዛ አስቀያሚ
ጣሳ ውሀውን ትጠጣለህ፡፡ በፖሊሶች እየተመራህ ወደ ዞን ሶስት ትሄዳለህ ፡፡ ይህ ዞን ማንኛውም እስረኛ ቃሊቲ ሲወርድ
በመጀመርያ ያርፍበታል፡፡እዚህ ካላረፈ ግን አንድ ነገር አለ ማለት ነው ፡፡ምን አልከኝ ምን መሰለህ ከመንግስት ጋር ንክኪ
ኖሮታል ለብቻው መታሰር አለበት አለበለዚያም ሚድያ ያናፈሰው እና ህዝብ የሚያወቀው ከሆነ ለብቻው ይታሰራል ከነዚህ
ውጪ ግን ገንዘብ ያላቸው ሰዎችና ዞን ሶስትን ጠንቅቀው የሚያቁ ሰዎች ለመዳቢው ፖሊስ ጠጋ ብሎ በጆሮው አንድ ነገር
ይነግረዋል ፡፡አንተ ጠጋ ብለህ በጆሮው ያልነገርከውን ምስኪኑን እየነዳ ካሉት ሰባት ዞኖች መሀል ዞን ሶስት ይከትሀል፡፡
ካለነሱ ፍቃድ ሌለውን ዞን ምን እንደሚመስል አታይም፡፡ማየትም የተከለከለ ነው፡፡ግራውንድ ስርም የሚታሰሩ አደገኛ
እስረኞች አሉ፡፡
ዞን ሶስት /ግቢ ሶስት/
በዚህ ዞን ውስጥ አምስት ትልልቅ ቤቶች ይገኛሉ አንድ ቁጥር ቤት፤ሁለት ቁጥር ፤ሶስት ቁጥር፤አራት ቁጥር፤ አምስት ቁጥር
፡፡ የተሰሩት ቆርቆሮ በቆርቆሮ ሲሆኑ አንደኛው ቤት ካንደኛው በቆርቆሮ ግድግዳ ይያያዛሉ ፡፡ አዲስ እስረኛ ቀጥታ አንደኛ
ክፍል ይገባል ወደሌላ ክፍል ወይም ዞን የምትዘዋወረው ከአንድ ሳምንት በኃላ ነው ፡፡ይህ ቁጥር አንድ ክፍል ከሌሎቹ
ክፍሎች ጠባብ ነው ለራስህ ካልሳሳህ እዚህ ክፍል ውስጥ ላለመኖር እራስህን ታጠፋለህ ፡፡በዞን ሶስት የሚገኙ ሌሎች
ክፍሎች እያንዳንዱ ክፍል ስፋት /40 በ 20/ ያክል ሲሆን እነዚህ ቤቶች ሻወር እና ሽንት ቤታቸው ከቤት ውስጥ ነው
የሚገኘው ፡፡በያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ከ 200-350 እስረኛ ይኖርባቸዋል ደልቶህ እንደማትኖር እርግጠኛ ነኝ፡፡ጥቂት
ተደራራቢ አልጋዎች በየክፍሉ ሲኖሩ መሬት ላይ የሚተኙት ይበልጣሉ፡፡ገንዘብ ካለ ችግር የለውም አንድ አልጋ እስከ
1000ብር ልትገዛ ትችላለህ፡፡የምትገዛው አልጋ በወረፋ ከደረሰው ሰው ነው፡፡በድብቅ ይሰራል ቢባልም አንዳንድ ፖሊሶች
ተሳታፊ መሆናቸውን ታያለህ፡፡ይሄን ያህል ብር የሌለው እስረኛ ደቦቃ መተኛት ይጠበቅበታል፡፡
ደቦቃ ማለት ቦታ ለማብቃቃት የሚተኛ መኝታ ሲሆን የአንዱ እግር ሌላው ፊት ላይ ያደርገዋል የዛኛው ሰው እግር
እዚህኛው ፊት ላይ ይሆናል አስቀያሚ መኝታ የማትገላበጥበትና ለሽንትህ የማትነሳበት ለሊትን ትጋፈጣለህ፡፡ቆርቆሮ
በቆርቆሮው የሆነው ቤት ይግላል ያዣል፡፡አልጋ ላይ ያለው ቁልቁል ወደታች ይሄን ትይንት እያየ ያዝናል፡፡ ፍራሽ ወደ
ቃሊቲ ስትወርድ ይዘህ ካሌድክ ባዶ መሬት ላይ ትተኛለህ፡፡ቃሊቲ እንደገባህ ኪኒን እንጂ ፍራሽና ብርድልብስ አይሰጥህም፡፡
እዚህ ዞን ውስጥ አንድ ትንሽ ካፌ ፤ሁለት ፀጉር ቤቶች፤አንድ ህግ ማማከርያ ቢሮ፤በጣም ትንሽ ላይብረሪ ገፅ ከሌላቸው
መፅሀፍት ጋር፤ሶስት ከረንቡላዎች፤በጣም ትንሽ የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን በጣም ትንሽ ባዶ መሬት ኳስም እጅ ኳስም
የሚጫወቱበት ቦታ ፤የእንጨት ስራ የሚሰሩበት ትንሽ ቤት፤ በጣም የሚያስቅ ጉሊት፤ ሲጋራና ሀሺሽ በድብቅ የሚሸጡ
ሰዎች፤ እብዶች፤ሊያብዱ የተዘጋቹ ሰዎች፤አዋቂዎች ፤ ኢ-አዋቂዎች ብቻ የሰው አይነት ይገኛል ፡፡ሁሉም ዞን ላይ ይሄ
እንደሚኖር ገምት፡፡
ኮሚቴዎች ከስረኞች ይመለመላሉ በየክፍሉም አሉ
የምግብ ኮሚቴ /ምግብ ከተሰራበት ቦታ አምጥተው የሚያድሉ /
የጤና ኮሚቴ /የተማመሙትን መዝግበው ነጭ ጋዎን ለሚያደርጉ ሀኪም ተብዬዎች የሚወስዱ/ የፅዳት ኮሚቴ /የቤቱን ፅዳትን በተመለከተ የሚቆጣጠር ሲሆን ሁሉም እስረኛ በየወሩ አንድ አንድ ብር ያዋጣና የቤቱንውበት ለመጠበቅኦሞ ሳሙና ሌሎች ነገሮችንም ይገዛሉ /
የመኝታ ኮሚቴ /እስረኛው እንዲተኛ ቦታ የሚሰጡ ባይተኛም ለቂጡ ቦታ እንዲያገኝ የሚያረጉ/
የስፖርትና መዝኛኛ ኮሚቴ /በቤት ውስጥ ያለውን ቴሌብዥን እንደየቤቱ ስፋት ይለያያል አንዳንዱ ቤት ሁከት ተቪ ሊኖር
ይችላል ይሄን ተቪ የሚቆጣጠሩ የሚከፍቱ የሚዘጉ ናቸው ለሊቱን ሙሉ ፊልም ይታያል/
ሶስት የቤቱ አስተዳደሮች /ጠቅላላ የቤቱን ሁኔታዎች የሚቆጣጠሩ ሲሆኑ እንደገባህ ማስጠንቀቅያ ይሰጡሀል ከዛም ፎቶህየሌለው መታወቅያ ይሰጡሀል / በጥቂቱ ኮሚቴዎች እነዚህ ናቸው
ይቀጥላል

Friday, June 14, 2013

ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?

"በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ" (Goolgule.com)



June 8, 2013
በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ
ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም
ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ።
በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማሳሰብ ለጎልጉል አስተያየት የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት በርካታ ጉዶች
ያሉበትን የአባይን ግድብ ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተነሳው ውዝግብ አስቀድሞ የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስልትና ውጤት ነው።
አሁን ድረስ አገር እየመራ በነጻ አውጪ ስም የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ “ዲሞክራሲ አመጣሁ” በማለት ኢትዮጵያን
መምራት እንደጀመረ የሚያወሱት የኢህአዴግ ሰው፤ አቶ መለስ ብቻቸውን ይነዱት የነበረው ኢህአዴግ እንደፈለገ ቆዳውን እየቀያየረ
የተጠቀመበትንና በእስስት በመመሰል “ከሽፏል የሚሉትን” ስልት ያብራራሉ።
በዲሞክራሲ ስም የተጀመረው የኢህአዴግ አገዛዝ ቆየት ብሎ “ልማታዊ ነኝ፣ ልማት ግቡን የሚመታው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቀመር ነው”
በማለት ፕሮፓጋንዳውን አሰፋ። የልማት ህልመኛነቱ ሲነቃበት “የትራንስፎርሜሽን ዘመቻ” በማለት አዲስ የፕሮፓጋንዳ እቅድ ነድፎ
ህዝብና አገር ሲያታልል ቆየ። ይህም አላራምድና በህዝብ የመታመን ድል ሊያስገኝለት እንደማይችል ሲታመን “የህዳሴያችን ግድብ”
ተብሎ አባይ አጀንዳ እንደተደረገ ያመለከቱት ዲፕሎማት፤ “ኢህአዴግ አገር ውስጥ የሚያምታታባቸው መንገዶች ሲጠናቀቁበት
የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ አንድ ደረጃ ከፍ አደርገው” በማለት አሁን ከግብጽ ጋር ስለተጀመረው ውዝግብ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
አባይን በመገደብ ኢትዮጵያን በልማት ለማሳደግ እየተጋ እንደሆነ የሚናገረው ኢህአዴግ፤ አስቀድሞ በመላው የብአዴን የበታች
አመራሮችና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ቂም ስላስቋጠረው የጣና በለስ ሰፊ ፕሮጀክት ዝርፊያና ውድመት የጠራ
መልስ ሊሰጥ እንደሚገባ ዲፕሎማቱ ይናገራሉ።
በጣሊያን መንግስት ሙሉ ድጋፍ አባይ ወንዝን መሰረት አድርጎ የተገነባውን የጣና በለስ ፕሮጀክት ህዝብ እያየ አፈራርሰው እንደወሰዱት፣
የተዘረፈው ንብረት ወደ ኤርትራ እንዲጓጓዝ መደረጉን ያመለከቱት እኚሁ ሰው፣ “ጣና በለስን አፈራርሶ ያስዘረፈ ፓርቲና አመራሮቹ አሁንአባይን ለመገደብ የተነሱበት መነሻ ለአብዛኛው የኢህአዴግ አባላት እንቆቅልሽ ነው” ባይ ናቸው። በማያያዝም በወቅቱ ዝርፊያው ሲካሄድ
ህዝብ አካፋና ዶማ በመያዝ “ንብረቱ አይዘረፍም” በማለት መንገድ በመዝጋቱ ዝርፊያው በሌሊት እንዲካሄድ ያደረገ ድርጅት እንዴትስ
ይታመናል የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።
“ኢህአዴግ የህይወት ዘመኑ የሚጠናቀቅበት ጠርዝ ላይ ስለሚገኝ፣ በአባይ ጉዳይ አመካኝቶ ህዝባዊ ማዕበል ለማቀጣጠል አቅዷል።
የአባይ ጉዳይ ከዚህ የተለየ ተግባርና ዓላማ የለውም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ፣ የጣና በለስ ፕሮጀክት እንዲወድም መመሪያ የተሰጠው
ከግብጽ እንደነበር መረጃ እንዳላቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላት የሆነችው ግብጽ አባይ ላይ የሞትና የህይወት
አቋም ቢኖራትም አሁን የተጀመረው ውዝግብ ከወሬ የዘለለ ግጭት እንደማያስነሳም ተናግረዋል።
በግብጽ አሁን ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለማስቀየር እየሰሩ ያሉት ፕሬዚዳንት ሙርሲ፣ የአባይን ጉዳይ ልቡን ከነፈጋቸው የአገራቸው
ህዝብ ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣ የአገራችን ተቃዋሚዎች እንደ ግብጽ ተቃዋሚዎች
መጫወቻ እንዳይሆኑ ይመክራሉ። “ኢህአዴግ የሚቃወሙትን ፓርቲዎች አባይን ተንተርሶ በአገር ክህደትና የአገርን ብሔራዊ ጥቅምን
በመጻረር ፈርጆ ከህዝብ ጋር ሊያጋጫቸው ተዘጋጅቷልና ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ” ሲሉ ይመክራሉ።
በሌላ በኩል ሙርሲ እንዳደረጉት ኢህአዴግ በወቅቱ ጉዳይ ላይ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ሊያነጋግር
እንደሚገባ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
አቶ ኦባንግ እንደሚሉት “አገር የህዝብ ነው። ህዝብ በተለያየ መልኩ ይወከላል። ከሚወከልበት መንገድ አንዱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች
ናቸው። አገርን አስመልክቶ በየደረጃው ያሉ የህዝብ ወኪሎችን ማግለል ህዝብን የማግለል ያህል ነው። ይህን ማድረግ ይቅር የማይባል
ወንጀል ይሆናል”
አገር ቤት ያሉትን ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ያሉትንም ፓርቲና ድርጅቶች በዚህ ጉዳይ ማነጋገር ግድ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ
“ለዚህ አገራዊ ውይይት ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ አይገባም” ብለዋል።
አጋጣሚው ለምንናፍቀውና ሁሉንም የአገሪቱን ህዝብ በእኩል ደረጃ ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር እንደሚረዳ አቶ ኦባንግ
ጠቁመዋል። የተለየ አመለካከት በማራመዳቸው ብቻ ዜጎችን እስር ቤት በማጎር እስከ ወዲያኛው መዝለቅ እንደማይቻል ያመለከቱት አቶ
ኦባንግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የውይይት በር በመክፈት የማያልፍ ታሪክ ሊሰሩ እንደሚገባ መክረዋል።
“ሙስሊም ወንድሞች ፍትህ የጠማቸው ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ የሚያረጋግጡበትን መድረክ አቶ ሃይለማርያም በማመቻቸት የማይረሳ
ታሪክ ሊሰሩ ይገባል” በማለት ጥሪ ያስተላለፉት አቶ ኦባንግ “አገር የህወሃት አይደለችም፤ አገር የኢህአዴግ አይደለችም፣ አገር የግለሰቦች
አይደለችም። አገር የሁሉም ነው። ባገር ጉዳይ ባይተዋር ሊደረጉ የሚገባቸው ዜጎች ሊኖሩ አይገባም። ኢህአዴግ ይህን ጉዳይ ሊያስብበትና
በሩን ለእርቅና ለውይይት በመክፈት ህዝብንና ራሱን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይገባል” ብለዋል።
“ባድመ በተወረረች ጊዜ የተፈጠረው ህብረት በስተመጨረሻ በክህደት መጠናቀቁ፣ በዜጎች አጥንትና ደም ላይ የአገር ብሔራዊ ጥቅም
ተላልፎ እንዲሰጥ መደረጉና በበርካታ ቁልፍ አገራዊ ጉዳዮች ኢህአዴግ በህዝብና በአባላቱ ጭምር እምነት ያጣ ፓርቲ ነው” በማለት
ኢትዮጵያ የከፋ ችግር ቢያጋጥማት እንዴት ልትቋቋም ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላቸው አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
ስርዓቱ በየደረጃው በችግር የተተበተበና በህዝብ የማይታመን፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን እስር ቤት ያጎረ፣ በሰብአዊ መብት ጥሰት
ከፍተኛ ቂም የተቋጠረበት፣ ፍትህና ርትዕ የተጓደለባቸው ያዘኑበት፣ በየአቅጣጫው ጠላት ያከማቸ፣ አገርን የሚፈትን አደጋ ቢፈጠር
ህዝብን አስተባብሮ አደጋውን ለመመከት የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የገለጹት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ አጋጣሚውን አሁንም
ሊጠቀምበት ይገባል” ሲሉ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ኦባንግ የሰማያዊ ፓርቲ ያስተባበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ ኢህአዴግ ክስ ለመመስረትና ዜጎችን ለማሰር እያደረገ ያለውን ዝግጅት
በመቃወም ሰሞኑን ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል። ከደብዳቤያቸው በተጨማሪ ከተለያዩ አካላት ጋር
በመነጋገር ኢህአዴግ ዜጎችን ከማሰሩ በፊት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች መግባባት ላይ መደረሱን ጨምረውገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ የአባይ ግድብን አስመልክቶ በከፍተኛ ደረጃ ውዝግብ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ግብጽ መጨረሻቸው ምን ሊሆን
እንደሚችል ከወዲሁ በርካታ አስተያየትና ትንተና እየቀረበበት ነው። ሁለቱ አገሮች ወደ ጦርነት አያመሩም፤ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታከመጠቀም ውጪ ሌላ አጀንዳ የላቸውም የሚሉ ያሉትን ያህል ግብጽ በጦር አቅሟ ያላትን የበላይነት በማመልክት ባልታሰበ ሰዓት ጥቃት
ለመፈጸም መዘጋጀቷን የሚያትቱም በርካታ ናቸው።
የግብጽ ፕሬዚዳንት ከተቃዋሚዎች ጋር ያደረጉትና ይፋ የተለቀቀው ቪዲዮ ላይ “ተቃዋሚዎችን በመርዳት ኢትዮጵያን ማተራመስ፣
ኢትዮጵያን መደብደብ ነው … ” በማለት ሲዝቱ የነበሩት ጽንፈኛ ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት የከረረ ቃላት ሲወረውሩ ሰንብተዋል።
ኢትዮጵያም በበኩሏ የግብጽን አምባሳደር በማስጠራት ማብራሪያ እንዲሰጣትና በይፋ ይቅርታ እንድትጠይቅ ማዘዟን ይፋ አድርጋለች።
ግብጽ በችግር መተብተቧን፣ የሶማሌ መበታተንና፣ የሱዳን ሁለት አገር መሆን፣ የኤርትራ መሽመድመድ ኢትዮጵያን በቀጠናው ጉልበት
ያላት አገር አድርጓታል የሚሉ ተንታኞች በበኩላቸው ግብጽ ወደ ጦርነት እንደማታመራ ሰፊ መከራከሪያ በማቅረብ ይናገራሉ። ከግድቡ
ግንባታ ጀርባ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ አገሮች እጅ እንዳለበትም የሚጠቁሙ ዘገባዎች በየፊናው ተሰራጭተዋል።
“ኤርትራ ተነፈሰች” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ግብጽ ተቃዋሚዎችን ለመርዳት ከተንቀሳቀሰች ኤርትራ
ርዳታውን በማከፋፈልና ቀድሞውንም ቢሆን ኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነቷን የጠበቀች ጠንካራ አገር እንድትሆን ስለማትፈልግ በችግሩ
ዙሪያ ቤንዚን ለማርከፍከፍ አጋጣሚው እንደሚመቻችላት ያስረዳሉ። የአረብ ሊግ የክብር አባል የሆነችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ
ተቃዋሚዎች ጋር በተያያዘ በበርካታ ጉዳዮች የምትታማ አገር እንደሆነች የሚታወስ ነው።
ዘግይታ “እኔ ከግብጽ የተለየ አቋም ነው ያለኝ” በማለት የገለልተኛነት ስሜት እንዳላት ይፋ በማድረግ ለግብጽ የድጋፍ ጥሪ መልስ
የሰጠችው ሱዳን እንደማትታመን የሚግለጹ ደግሞ “አቶ መለስ ደቡበን ሱዳን ላይ ሲከተሉ በነበረው አቋምና ደቡብ ሱዳን እንድትገነጠል
በመናደረጓ ሱዳን አቂማለች” ይላሉ፡፡ እንደነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ምንም ይሁን ምን በአገር ውስጥ ያለውን ችግር በውይይት
በመፍታት ብሔራዊ አንድነትና ህብረትን ማጠናከሩ ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊዋ ነው። ስለዚህ “በር ይከፈት በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም
እንያዝ” የሚለው የአቶ ኦባንግ ብቻ ጥያቄ አይደለም።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም (http://www.goolgule.com/)