Friday, June 19, 2015

“መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው

የዓረና/መድረክ አባል ታንቀው ተገደሉ
three
* “ልማታዊ ግድያውን” ተጠናክሮ ቀጥሏል
እየሠራሁ ነው ለሚለው ልማትና ግድብ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” እያለ የሚፈክረው ኢህአዴግ በየእስር ቤቱ የሚያሰቃያቸው ወገኖች ቁጥር እንዳለ ሆኖ “ልማታዊ ግድያውን” አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሰሞኑን በግፍ የተገደለው ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ማክሰኞ ዕለት የዓረና-መድረክ አባል የሆኑት አቶ ታደሰ አብርሃ ታንቀው መገደላቸው ተሰማ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሚያዚያ ወር በእንግሊዙ አምባሳደር የተጎበኙት አንዳርጋቸው ጽጌ ለመሞት ደስተኛ እንደሆኑና ምናልባትም የተሻለ መሆኑን ተናገሩ፡፡
የአቶ ታደሰ አብርሃን አገዳደል በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨው አምዶም ገብረሥላሴ በዚህ መልኩ አቅርቦታል፡-
አቶ ታደሰ አብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አመራር አባል ትናንት ማታ 09/10/2007 ዓ/ም በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።
tadesseአቶ ታደሰ አብርሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው አስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ አባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።
አቶ ታደሰ ማታ 03:00 በሶስት ሰዎች አንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ህወታቸው እስከ 09:15 አላለፈችም ነበር። አደጋውን 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ እንዳልወሰዱት ተናገረው ነበር።
የአቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል እንዳይመረመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና አባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት አካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ አባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል። ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል አባሎቻችን የተከራዩት ሞተር ሳይክል በፖሊስ ትራፊክ ተከልክሏል።
የአቶ ታደሰ አብራሃ ቤት አከራይና ሌሎች ሰዎች ከአደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአቶ ታደሰ አብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ አባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ አስተባባሪና የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው አቶ ልጃለም ኻልአዩ በአዲስ አበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል። አቶ ታደሰ አብርሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።
“መሞቴ … የተሻለ ነው” አንዳርጋቸው
በሌላ በኩል ዘ ኢንዲፔንደንት የተሰኘው የእንግሊዝ ጋዜጣ እንደዘገበው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዜጋቸውን ለመጎብኘት በሄዱ ጊዜ የሰሙትንና ያዩትን ምስክርነት ለመ/ቤታቸውና ለአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት መላካቸውን አስታውቋል፡፡ ዘገባው ለባለቤታቸው በተሰጠበት ወቅት እጅግ ስሜትን የሚረብሽና መንፈስን የሚጎዳ ይዘት ስላለው ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው እንዲያነቡት የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ለባለቤታቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡
አምባሳደሩና አንዳርጋቸው የተገናኙት በእስር ቤት ሳይሆን የደኅንነት ባለሥልጣናት በተገኙበት ቦታ ነበር፡፡ “በአካላቸው ላይ የሚታይ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም” ያሉት አምባሳደሩ ለብቻቸው በመታሰራቸውና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚደርስባቸው ስቃይ መንፈሳቸውንና ስነልቡናቸውን እንደጎዳው በዘገባው ላይ ተናግረዋል፡፡andargachew
ሪፖርቱ ሲቀጥልም በውይይታቸው ወቅት አንዳርጋቸው ለአምባሳደሩ “እውነቱን ለመናገር ለመሞት ደስተኛ ነኝ – ምናልባትም የተሻለና ሰብዓዊነት ያለው ነው” ብለው እንደነገሯቸው በዘገባቸው ላ አስፍረዋል፡፡ “መንግሥት ይገድለዋል ብዬ ለማመን ይከብደኛል” ያሉት አምባሳደሩ አንዳርጋቸው በፈቃድ የመሞትን (ዩታኔዥያ) አከራካሪነት ያስተውላሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
ሰሞኑን ከታሰሩ አንድ ዓመት የሚሆናቸው የ60 ዓመቱ አንዳርጋቸው የእስር ቤት ጠባቂዎቻቸው ራሳቸውን ይገድላሉ ብለው እንደሚፈሩ እርሳቸው ግን እስካሁን እንዳልሞከሩት ተናግረዋል፡፡
የአምባሳደሩን ሪፖርት ያነበቡት ባለቤታቸው ሪፖርቱን በጽሁፍ ሲያነቡ እንዴት እንደሰበራቸውና እንደጎዳቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡ ለሌሎች የእንግሊዝ ዜጎች እንደተደረገው በእንግሊዝ መንግሥትም ሆነ በአምባሳደሩ ከዚህ የከረረ ጫና ባለመደረጉ ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚደረገው ጫና ሰሞኑን እየገፋ እንደመጣና ጉዳያቸው በተባበሩት መንግሥታት ልዩ ራፖርተር እየተመረመረ በመሆኑ ወደ እንግሊዝ እንዲመለሱ የሚደረገው ግፊት አንዱ አካል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የአንዳርጋቸው በእስር መቆየት ለኢትዮጵያና እንግሊዝ ግንኙነት መሻከር አስተዋጽዖ ያደርጋል በማለት የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ለኢትዮጵያው እስካሁን በ13 የተለያ ጊዜያት እንዳነሳ ጋዜጣው አስታውቋል፡፡ አንዳርጋቸው የኤምባሲው ሰዎችም ሆኑ ጠበቃ እንዳያገኙ ተደርጎ በእስር የመቆየታቸው ሁኔታ አግባብነት እንደሌላው አሁንም መወትወታችን እንቀጥላለን በማለት የአምባሳደሩ ዘገባ ገልጾዋል፡፡
“መሞቴ … የተሻለ ነው” በማለት አንዳርጋቸው መግለጻቸው በምን ዓይነት የመንፈስ ጭንቀትና ስቃይ ውስጥ እንዳሉና ምን ያህል እረፍት ለማግኘት እንደሚፈልጉ የሚያመለክት እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እየደረሰባቸው ያለውን እጅግ መራራ ስቃይም ሊስተዋሉ በሚችሉ ቃላት መግለጻቸው እየተሰቃዩ ከመኖር መሞትን እንዲመርጡ እንዳደረጋቸው ያሳያል፡፡
“በልማታዊ ግድያ” እና ማሰቃየት ላይ የተሰማራው ህወሃት/ኢህአዴግ ምርጫውን በግልጽ ከማጭበርበሩ አልፎ ቸሁ ደግሞ በተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት ወደ ግድያ ከፍ ማለቱ የዜጎችን ምሬት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋል የሚለው አስተያየት ከምንጊዜውም ይልቅ እየበረታ መጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሁኔታና አሠራር ለዕርቅ በመንቀሳቀስ ላይ ለሚገኙ ወገኖች እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥና ሃሳባቸውን እንዲተዉ የሚያስገድድ እንደሆነባቸው በጉዳዩ ላይ ከተሰማሩት ለመረዳት ተችሏል፡፡

Thursday, June 18, 2015

Ethiopia Opposition Candidate Dies After Attack in Northwest

June 16, 2015
Samuel Awoke Opposition Candidate
Samuel Awoke (PHOTO: NegereEthiopia)
(Bloomberg) – An Ethiopian parliamentary candidate for the opposition Blue Party died after being assaulted in Debre Markos, a town in the country’s northwest, the group said.
Two people attacked Samuel Awoke, 29, with a club and knife as he returned home alone from a night out with friends, spokesman Yonatan Tesfaye said by phone Tuesday from the capital, Addis Ababa.
“We are trying to figure out who are the killers and the reasons,” he said, citing suspicions it was politically motivated. Ethiopian Communications Minister Redwan Hussien said in a text message that a suspect has been apprehended and the attack may have stemmed from a legal dispute.
Samuel reported previous death threats and a beating during campaigning for the polls that were held May 24, Yonatan said. The lawyer had been active in challenging election procedures and results in the Amhara region town, 295 kilometers (183 miles) northwest of the capital, he said.
All 442 of 547 federal seats announced so far were captured by the ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front and allied parties.

Wednesday, June 10, 2015

ምርጫ ሲባል፣

መሳይና አስመሳይ
eth election 2015
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ።
ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ እንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም።