በእነ አንዱዓለም አራጌ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለለፈው ፍርድ በ/ጠ/ፍ/ ቤት ፀና፡፡ እነ አንዱዓለም አራጌ ያቀረቡትን ይግባኝ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጠ/ፍ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 24 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በሰጠው ብይን፣ ይግባኝ ባዮች በሽብርተኛነት ተግባር ላለመሳተፋቸው አሳማኝ የሆነ መከላከያ አላቀረቡም ብሏል፡፡ በዚህ የተነሳ የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አፅንቷል፡፡ የጀርመን ሬዲዮን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።
“እውነት ተደብቆ አይቀርም” እስክንድር ነጋ (ከፍርዱ በኋላ በችሎት ውስጥ)
“የተከራከርነው ፍትህ እናገኛለን ብለን አይደለም፤ ፍትህ ወዳድ በመሆናችን ነው” ናትናኤል
“ የእኛን ጉዳይ ለመከታተል እዚህ ስለተገኛችሁ እናንተ የእኛ ጀግኖች ናችሁ” አበበ ቀስቶ “የእስክንድር ወንጀል አገር መውደድ ብቻ ነው” (ሰርካለም ፋሲል- ከፍ/ቤት ውሳኔ በኋላ)
“ግንቦት ሰባት የእስክንድርን እጅ የመጠምዘዝ ኃይል የለውም” (ሰርካለም ፋሲል በችሎት ውስጥ የተናገረችው)
Reported by: Wosenseged Geberekidan
ይህን በተመለከተ የጀርመን ሬድዮ ዘገባ ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ነው።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤ በእነ አንዱዓለም አራጌ መዝገብና በሌሎች መዝገቦች ፤ በአሸባሪነት ተከሠው ይግባኝ የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአመራር አባላትና የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጉዳይ መርምሮ፣ ከአንደኛው በስተቀር የሁሉንም የእሥራት ብይን እንዲጸና አድርጓል።
የክንፈ ሚካኤል በየነ እሥራት ፤ ከ25 ዓመት ወደ 16 ዓመት ዝቅ እንዲል ወስኗል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተወነጀሉት እና ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ እስር ላይ ያሉትን፤ አምደኛ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዉ አንዱአለም አራጌ፤ ያቀረቡትን ይግባኝ ዉድቅ አደረገ።
«ብይኑ አሁንም ትክክል ነዉ፤ ምንም አይነት ቅነሳ አይኖርም ሲሉ» የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ደጀኔ መላኩ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዲፕሎማቶች በዘመድ እና በጓደኛ በተሞላዉ ብይን ላይ ከዉሳኔዉ በኋላ « እዉነት አንድ ቀን ይወጣል» ሲል በስሜት መናገሩ ተገልጾአል።
ጠበቃ አበበ ጉታ
«ብይኑ አሁንም ትክክል ነዉ፤ ምንም አይነት ቅነሳ አይኖርም ሲሉ» የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ደጀኔ መላኩ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዲፕሎማቶች በዘመድ እና በጓደኛ በተሞላዉ ብይን ላይ ከዉሳኔዉ በኋላ « እዉነት አንድ ቀን ይወጣል» ሲል በስሜት መናገሩ ተገልጾአል።
ጠበቃ አበበ ጉታ
እስክንድር ነጋ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዉቅ የምንፈልገዉ እዉነት እራሱ በግዜዉ ይወጣል፤ የግዜ ጉዳይ ብቻ ነዉ» ብሎአል። አንዱአም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ተቃዋሚ ቡድን ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለዉ እስክንድር የ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አንዱዓለም ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር እጎ እ 2012 ዓ,ም ዓለም አቀፉ የደራስያን ድርጅት ፔን በዓለምአቀፍ ደረጃ በሥራቸው ምክንያት
ለታሠሩ ወይም አደጋ ላይ ለወደቁ ደራስያንና ጋዜጠኞች የሚበረከተዉን የመፃፍ ነፃነት ሽልማት ማግኘቱ ይታወቃል። ዝርዝሩን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ተከታትሎታል። ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።
ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.