(ዘሐበሻ) የአማራው ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን የሚመሩትን የአማራ ሕዝብ በጸያፍ ቃላት መሳደባቸውን ተከትሎ አንድነትእና መኢአድ ፓርቲዎች በጋራ በባህርዳር ዛሬ በባህርዳር የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በሰላም ተጠናቀቀ። “ህዝቡ ከባዶጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።
በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች ቁጣቸውን ለመግለጽ በወጡበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በአቶ አለምነው የተሰደበውን ለማስታወስናቁጣውንም ለመግለጽ በባዶ እግሩ እንደነበር ከስፍራው መረጃ ያደረሱን የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ገልጸዋል። “ሰልፈኛው ጫማውን አንገቱ ላይበማንጠልጠል በሰላማዊ ሁኔታ በባዶ እግሩ በመሄድ በአዲስ የተቃውሞ ስልት ድምጹን አሰምቷል” ያሉት በስፍራው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎችእንዲህ ያለው የትግል አገላለጽ የሚደነቅና ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል።
በባህር ዳር በተደረገው በዚህ ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር በትላልቅ ስፒከሮች ለሰልፈኛውበድጋሚ የተሰማ ሲሆን ሰልፈኛውም በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን በአንድ ድምጽ አሰምቷል።
“ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም
“ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ”
“ነፃነታችን በእጃችን ነው”
ህዝቡ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”
“የመሬት ቅርምቱ ይቁም”
“አማራውን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ለመለየት የሚደረገውን የኢሕ አዴግ ሴራ በጥብቅ እናወግዛለን”
“ብአዴን/ኢሕአዴግ አማራውን የመምራት የሞራል ልእልና የለውም የለውም”
“ሕዝብን ከእርስቱ ማፈናቀል ይቁም!”
የሚሉና አቶ አለምነው ለፍርድ እንዲቀርቡና ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚጠይቁ መፈክሮች በዛሬ ፌብሩዋሪ 23 ቀን 2014 ሰልፍ ላይ ተሰምቷል።
በባህርዳር ግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 የሚገኘው አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መነሻውን አድርጎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የተጀመረው ይሄው የተቃውሞ ሰልፍከግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 ተነስቶ በድብ አንበሳ አካባቢ ዞሮ ወደ ክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት ያመራ ሲሆን በሰልፉ ላይ ንግግር ያደርጉት የአንድነት ፓርቲሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው አቶ አለምነው መኮንን ይቅርታ የማይጠይቁና ከስልጣናቸው የማይወርዱ ከሆነ ፓርቲያቸው በድጋሚ በባህርዳርየተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ባለስልጣኑን በፍርድ ቤት እንደሚከስ አስታውቀዋል። የህዝቡን ከፍርሃት መላቀቅ ያደነቁት ኢንጂነር ግዛቸውበሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኘውን ሕዝብ አመስግነዋል። በተጨማሪም በዚህ ሰልፍ ላይ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ ንግግር አድርገዋል።አቶ አበባው በንግግራቸው አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ፣ ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆምና አቶ አለምነው መኮንንየአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አስረግጠው ተናግረዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13073
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.