Tuesday, March 4, 2014

በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት ህዝባዊ ውይይት እና የኢሳት ምሽት ፕሮግራም በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

March 1/2014

በኖርዌይ ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን  ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት   ሐሙስ የካቲት20,2006 ዓ ም  በአንድ ላይ በመሰብሰብ ውይይት እና ምክክር አድርገዋል :: ስብሰባው በኖርዌይ የስደተተኛ ማህበር የተዘጋጀ ሲሆን በስብሰባው  ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ እና በኦስሎ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የተሳተፉ ሲሆን የኢሳት ጋዜጠኛ የሆኑት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ጋር በመሆን በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፥፥


   በስብሰባውም ኢትዮጵያኖች በሀገራቸው እንዳይኖሩ የወያኔ መንግስት በሚያደርስባቸው ጫና እና በደል ሀገራቸውን ጥለው ቢሰደዱም ነገር ግን ኖርዌይ ከገቡ በኋላም የኖርዌይ መንግስት የኢትዮጵያኖችን የፓለቲካ ጥገኝነት በሚገባ እንደማያየው እና እንደማይቀበለው በየጊዜው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን  በስብሰባው ላይ ከነበሩት ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና የየእራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ እና ኖርዌይ ከገቡ ጀምሮ በሕይወታቸው ያለፈውን እና እየኖሩ ያለው ኑሮ ምን እንደሚመስል እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ውይይት አድርገዋል  ::

 አንዳንድ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከሀገር እየወጡ  ኖርዌይ ገብተው የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ወረቀት ካገኙ በኋላ ወይም ፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ መስለው ትንሽ ጊዜ በመቆየት ካዛም በገዛ ፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ እና  በኢትዮጵያ መንግስትም ምንም አይነት በደል እንዳልደረሰባቸው የኖርዌይ መንግስት እንደሚያውቅ ከዚህም የተነሳ ሌሎች ኢትዮጵያን ስደተኞ ላይ ወደ የፓለቲካ ጥገኝነት እንደማይቀበል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም የኖርዌይ መንግስት የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በስብሰባው ከነበሩ ተሳታፊዎች የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን  እንደነዚህ አይነት ሰዎች በመጀመሪያ ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት እንዳላቸው እና ምክንያታቸውም  በኖርዌይ የሚኖሩትን እውነተኛ የወያኔ ተቃዋሚዎ ችን ለመሰለል እና ለማደን ሲሆን  እንደነዚህ አይነት ሰዎችን እንዳሉ እና እንደሚያውቆቸው ነገር ግን ኢትዮጵያውን እነዚህ የወያኔ ሰላዮች መፍራት እንደሌለባቸው ይህንንም ለኖርዌይ የስደተኞችን ጉዳይ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት utlendingsnemnda (UNE) በተለያየ ጊዜ መሳወቃቸውን በስብሰባው ላይ ተገልጾል ::

በስብሰባው ላይ በመገኛት በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጥያቄ ሲጠይቁት የነበሩት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ኖርዌይ በሚኖሩት ኢትዮጵያኖች በሚያደርጉት ትግል ወይም እንቅስቃሴ በጣም እንደሚደሰቱ እና እንደሚደነቁ በመናገር ማንኛውንም ማድረግ ያለባቸውን እና ማድረግ የሚችሉትን  ነገሮች በማድረግ ከጎናቸው በመቆም አብራቸው እንደሚሰሩ ቃል ገብተውላቸዋል::


ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት ቅዳሜ የካቲት 22, 2006 ዓም በዛው በኖርዌይ ኦስሎ ኢሳት የእኔ ነው (ESAT IS MINE) በሚል መሪ ቃል የኢሳት ምሽት ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን  የኢሳት ጋዜጠኛ የሆኑት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ የዝግጅቱ ተጋባዥ እንግዶች በመሆን በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል :: 

 በፕሮግራሙ የተለያየ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያዩ ሰዎች የኢትዮጵያን  የፖለቲካ ሁኔታ የሚዳስስ ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን  ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት መረጃን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይን እና ጆሮ የሆነውን  ኢሳትን መርዳት እንደሚገባ በኖርዌይ የሚኖሩ የኢትዩጵያን ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ፋሲል እና  የኢሳት ኖርዌይ ዋና ተወካይ ጋዜጠኛ አበበ ደመቀ  እንዲሁም በኖርዌይ የኢሳት ም/ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሙባረክ ንግግር አድርገዋል::በተጨማሪም አቶ እንግዳ ታደሰ የኢሳት በኖርዊይ አመሰራረት እና ስለ ኢሳት ባለቤትነት በህዝብ ዘንድ የሚወራው የተሳሰት ወሬ ትክክል እንዳልሆነ ኢሳት የማንም የፖለቲካ ድርጅት ንብረት እንዳልሆነ እና ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት እንደሆነ ሕዝቡም ኢሳት የእኔ ነው በሚል ስሜት ኢሳትን እንዲረዳ እና እንዲደግፍ የኢሳትም አባል እንዲሆን ጥሪ በማቅረብ ንግግር አድርገዋል::


በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ አስደሳች ግጥሞች እና መነባንቦች በተለያዩ ሰዎች የቀረበ ሲሆን በጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ኑ ሀገራችንን እንስራ በሚል ርዕስ ኢትዮጵያኖችን ለስደት የዳረገው ወያኔ በሰዎች ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና በደል እንደሆነ እና  ስደት በሰው ሀገር  ምንም ቢመችም ደስታን እንደማይሰጥ የስደትን  ህይወት በሚመለከት አስደሳች እና ልብን የሚነካ ግጥም የቀረበ ሲሆን በጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላም ሁሉም ሰው የሀገሩ ሁኔታ ግድ እንዲለው እና ስለ ሀገር መቆርቆር ፣ሀገርን በሚመለከት ጉዳይ ላይ መሳተፍ  ፖለቲከኛ መሆን እንዳይደለ ሀገራችን ከወያኔ ስርዓት ነጻ እስከምትሆን ሁሉም ሰው በጽናት መታገል እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥታ ንግግር ያደረገች ሲሆን በስብሰባው ላይ ዋናው አላማ የነበረው ማንኛውም ሰው ኢሳት የእኔ ነው በሚል ቃል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኢሳት የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው ኢሳትን እንዲረዱ ከመሆኑ አኳያ በፕሮግራሙ ላይ ሲተላለፉ የነበሩት ግጥምም ሆነ ንግግር በዋናነት ኢሳት በመርዳት ላይ ያተኮረ ነበር :: በእለቱ የፕሮግራሙ አላማ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በእለቱ ለኢሳት ማጠናከሪያ የሚሆን የተለያዩ ምግቦች ፣መጠጦች፣ ቀለበቶች፣እና ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል :: በተለያየ ጊዜ ለኢሳት እና ለፖለቲካ ድርጅቶች በሚደረጉ የገንዘብ ገቢ ማሰባሠቢያ ፕሮግራም ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ይታወቃል::

posted;- Bethel Solomon

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.