Thursday, July 3, 2014

ሃገር አለን ወይ?


ቤቴል ሰለሞን

ወያ ሀገር ወይ ሀገር አሁን ሀገር አለኝ ይባላል??  ሀገር ማለት እኮ ለአንድ ስው ከለላ ነፃነት የሚሰጥ እና ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶች ሲኖር ነዉ ሰዉ ሀገር አለኝ ብሎ ሊያወራ የሚችለዉ::  ግን አሁን ያለችዉን ኢትዩዺያን ስናያት ግን ሀገር አለኝ ብሎ ደፍሮ ለመናገር በጣም ይከብዳል:: ምክንያቱም የኢትዩዺያን ነባራዊ ሁኔታ የተመለከትን እንደሆነ በአሁኑ ጊዜ ኢሰባዊ የሆኑ ድርጊቶች በተለያዩ ዜጋዌች ላይ እየተፈፀመ ሲሆን የሀገሪቱዋም የኢኮኖሚ ሁኔታ ብዙ ድሆችንና ጥቂት የወያኔሃብታሞችን ፈጥሯል::
አንድ ሰው ሀገር አለኝ ብሎ ማውራት የሚችለው ከሀገሩ ማግኘት ያለበትን መብት ነጻነት የዜጎች ሃሳብን በነፃነት  የመናገር እና የመፃፍ መብት ሲከበርለት ነው::
የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ:: 
የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር:   ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: 
በጣም የከፋው ደግሞ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈው ከፍተኛ ሀብቶች ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ::
እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር::  
ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን  እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን  የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::
ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ  የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ; የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: 
ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::
መቼ ናት ያቺ ቀን ሀገሬ ሁሉም ወገንሽ ጠግቦ የሚያድርበት: መሰረታዊ ፍላጎታችን ተሙዋልቶልን የምድንኖርበት የባእድን አገር የማንናፍቅበት: የማንሰደድበት: በየበርሃው በየገደሉ የማንሞትበት: በአረብ ሃገሩ የማንታሰርበት የማንደፈርበት:: መቼ ናት ያቺ ቀን የኢትዩዺያ አምላክ ሀገሬን ተመልከታት: መከፋፈላችንን አቁመን በአንድ ልብና ሃሳብ ለሃገራችን እድገት የምንሰራበት: በጥሩ ቅንነት ሃገራችንን የምናገለግልበት: ወገኔ ተነስ ለጋራ ነፃነት ለሃገር እድገት ተነስ ክንድህን አበርታ ልብህን አጨክን እነዚህን ሃገር አፍራሽ መሬህን ቸርቻሪ ጥላቻን በብሄር የሚዝሩትን ለጋራ ነፃነትና እድገት የማይሰሩት ምሪዎች ተዋጋ ታገል በአንድ ልብ ተነስ::

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.