Wednesday, July 9, 2014

የይሉኝታ ፖለቲካ ማብቃት አለበት!!


ቤቴል ሰለሞን
እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ወያኔ በስልጣን ላይ የቆየበት ሚስጥር የተበዳዮች ህብረተሰብ በጋራ ተባብረው አለመታገላቸው ብቻ ነው ። በወያኔ በደል ተፈጽሞብኛል የሚሉት ተህብረተሰብ ክፍሎች ወይም ድርጅቶች ተነጣጥሎ በመታገል ተራ በተራ የወያኔ የጥቃት ሰለባ እየሆንን ቆይተናል።

የወያኔ አፓርታይዲዝም በብሄር ወይም በሃይማኖት መከፋፈል ብቻ የሚቆም አይደለም ፣ በመንደር በቀበሌ እያለ እስከቤተሰብ ድረስ የሚወርድ ነው። አንደኛው የህብረተሰብ ክፍል በደል ወይም ጥቃት ሲፈፀምበት ሌላኛው የህብረተሰብ ክፍል ከጥቃቱ የተረፈ ይመስለዋል።


የቅርብ ግዜ በወያኔ መንግስት የተፈፀሙትን የሽብር ወንጀሎችን እንኯን ብንመለከት
  • በምስራቅ አፍሪካ ባሉ ሃገሮች ሱማሊያ ሱዳን የመን ኬንያ ጅቡቲ የሚኖሩ የወያኔ ተቃዋሚዎችንና ዜጎችን አፍኖ መውሰድ እና የሽብር ጥቃት መፈጸም::
  • በአፋርና በሱማሌ ጎሳዎች መካከል ወያኔ ሆን ብሎ የለኮሰው ጦርነት ብዙ ሰዎች ሞተዋል ንብረትም ወድሟል::
  • በሶማሌና በኦሮሞ ጎሳዎች መካከል የተካሄዱ ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ሆን ተብለው በወያኔ የተንኮል ሴራ የተሸረቡ ናቸው::
  • የትየለሌ ቁጥር ያላቸው ታዋቂ ሃገር ወዳድ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ያለምንም ማስረጃና ክስ በህገወጥ መንገድ በእስር ቤት ታጉረዋል::
  • በኦሮምያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርቲዎች ተማሪዎች ህገ መንግስታዊ ጥያቔ በመጠየቃቸው ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያና የአካል ጉዳት ፈጽሟል።
  • በሚሊያን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩበት ተፈናቅለዋል (በጋምቤላ፣በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ህዝቦችና በሶማሌ ክልሎች) ሀብት ንብረታቸው ወድሟል ተዘርፏ ንጹሃን ዜጎች ተሰደዋል፣ ለእንግልትና ለሞት ተዳርገዋል።

ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ ማጠር ምክንያት ብልህ የፖለቲካ አመራር የሚሰጡ ሰዎች የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: በወያኔው የካንጋሮ ፍርድ ቤት አሸባሪ በማስባል የሽብር ወንጀል መፈጸም;መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን ፈጽመዋል አሁንም እየፈጸሙ ነው ወደፊትም ይፈጽማሉ።

የብሄር ብሄረሰብ መብት በሚል ሰበብ ከትግራይ የተውጣጡ የወያኔ ዘራፊዎች የራሳቸውን ኢምፓየር መስርተዋል :: ለምሳሌም በተለያየ በከፍተኛ የውሳኔ የሚሰጥባቸው የስልጣን ቦታዎች፤ ለሙስና የተጋለጡ መስሪያቤቶች፤ የህግ ክፍተት ያላቸውና፤ ብዙ የህዝብና የሀገር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቦታዎች ላይ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ በትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ መያዙ; እጅግ ትንሽ የሆኑ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች በሌሎች የብሄር ተወላጆች ቢያዙም ከአሻንጉሊትነት የዘለለ የመወሰን ስልጣን የላቸውም::

ለምሳሌ በወያኔ መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች ከሞላ ጎደል በትግራይ ተወላጆችና ለጥቂት ለሆዳቸው ባደሩና ታማኝ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች መያዙና የፌደራል ፓሊስን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ፤አየር መንገድ፤ በተለያዩ የታክስና የጉምሩክ ገንዘብ መሰበሰቢያ ቦታዎች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ከዘጠና በመቶ በላይ የተያዙ ናቸው፧ (በሁሉም የሀገሪቱ ከተሜዎች ላይና የጠረፍ ከተሞች በሚገኙት የጉሙሩክ ኬላዎች ላይ በሙሉ የሚሰሩት የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው)::

እስርና ሰቆቃ የኢትዮጵያውያን የለት ተለት ከስተቶች ሆነዋል። በውሸት የተቀነባበረ የሰው የቪዲዮና የፅሁፍ ማስረጃና ምስክር ቀርቦ እስር ቤት መወርወር እንደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ከተቆጠረ ሰነበተ:: ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የሚፅፉትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ መዳረጋቸው ዘወትር በወያኔ የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ የምንሰማውና የምናየው ድራማ ሆኖል:: በከተማችን የሚከሰቱ ከባድ ወንጀሎችና ሽብሮች በወያኔ ደህንነቶች ሆን ተብለው የተቀነባበሩ መሆናቸውን ዓለም የመሰከረውና ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ለምሳሌ በቅርቡ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ከሁለት ሚሊያን ብር በላይ ከግለሰቦች ገንዘብ ዘርፈው የተሰወሩት የፌደራል ፖሊሶች በቂ ምስክር ናቸው::

ጎበዝ የይሉኝታ ፖለቲካ ማብቃት አለበት! ሁላችንም ተራ በተራ መታሰር መደብደብ መገደል መሰደድ የለብንም! አሁን በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔ አምባገነን ስርኣት በጋራ ተባብረን ከማስቆም ውጭ ሌላ ምንም መፍትሄ የለውም። ሁሉም ህብረተሰብ ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በጋራ መታገል እስካልጀመሩ ድረስ ወያኔ በስልጣን የመቆየቱ ሁኔታ ምንም አጠራጣሪ አይደለም።

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.