Monday, November 24, 2014

ሀና ላላንጎ የተደፈረችው ሺሻ ቤት ውስጥ ነበር! ፖሊስም ተጠያቂ ነው!

ለዚህ እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ የምናገኘው ደግሞ ከውስጥ አዋቂ ምንጭ ነው:: ይህ ውስጥ አዋቂ ሃና የተደፈረችው ያለ ፍላጎቷ ሺሻ ቤት ተወስዳ መሆኑን በዝርዝር ያስረዳል:: ይህ የሃና ጉዳይ በጣም የብዙ ሺህ እህቶቻችን ጉዳይ መሆኑንም ያብራራል:: በተለይም እነዚህ ሺሻ ቤቶች በትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኙ በመሆናቸው ለወጣት ተማሪዎች መጥፊያ እየሆኑ ነው:: በውጭ አገር በትምህርት ቤት እና በአምልኮ ቦታዎች አቅራቢያ የመጠጥ እና የንዲህ አይነት ነውረኛ ድርጊት መፈጸሚያ ቦታዎች እንዳይኖሩ አጥብቆ ይከለክላል:: በአገራችን ግን እነዚህ ሺሻ ቤቶች በትምህርት ቤት አቅራቢያ እየተከፈቱ ለወጣቶች መጥፊያ እንደሆኑ የሃና ጉዳይ አንዱ ምስክር ነው::
hanna

ይህን ጽሁፍ አንብበው ሲጨርሱ “ፍትህ ለሃና” ከሚለው ዘመቻ በተጨማሪ; ሺሻ ቤቶች ከትምህርት ቤት አቅራቢያ እንዲነሱ የሚጠይቅ አዲስ ዘመቻ መከፈት ያለበት ይመስለናል:: “ፍትህ ለሃና” ካልን’ ፖሊስ ጭምር በሃና ሞት ምክንያት ከተጠያቂነት መዳን የለበትም:: “የፖሊሶቹስ ጥፋት ምን ነበር?” ካላቹህ ይህንን ጽሁፍ በሙሉ ማንበብ ይኖርባችኋል:: ለማንኛውም አንዳንድ ማስተካከያ አድርገን ያቀረብንላችሁ የውስጥ አዋቂው (ሰይፈዲን ሙሳ) ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል::

ይህንን መረጃ ያገኘሁት ጦርሀይሎች ሙሉ ወንጌል ከሚገኘው የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ነው፡፡ ከታሰሩት አንዳንዶቹ የእነዚሁ መረጃ ሰጪዎችም ጓደኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የነገሩን ምንነት ከፖሊስም በላይ የሚያውቁ ናቸው ቢባል ሀሰት አይሆንም፡፡ የነገሩኝን ነገር እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ በ21/1/07 ዓ.ም ሀና በሴት ጓደኛዋ ምክንያት ያለ ወትሮ በምሳ ሰአት ወደ ቤት እንሂድ ብለው ያመራሉ፡፡ ይህ ሀሳብ የተፈጠረው በጓደኛዪቱ ሲሆን ቀድማ በሀና ጉዳይ ከአንድ ሹፌር ጋር ተስማምታ ነበር፡፡ “ምሳ ይዛ ስለማትመጣ ምሳ እንብላ ብያት ይዣት እመጣለሁ ያኔ ትቀላጠፋለህ” በሚል፡፡ ሀና እንደተባለው ጓደኛዋ ባዘጋጀችው ወጥመድ ውስጥ ገባች፡፡ አብረው ወደ ጦር ሀይሎች ጉዞ ተጀመረ፡፡ ሀና፣ ጓደኛዋ፣ ሹፌርና አንድ ረዳት፡፡ ሀና ከመውረጃዋ ራቅ ብላ መሄዷ በክፉ አልጠረጠርችውም፣ ብታቅማማም በጓደኛዋ ግፊት ግን ቶሎ እንመለሳለን ዛሬ ስለደበረን ሻይ ቡና ብለን ልክ በሰአታችን ወደ ቤት እንሄዳለን ብላ ካግባባቻት በኋላ ጉዞው ቀጠለ፡፡
ሹፌር “ችግር የለም ልክ በሰአቱ እኛ እናመጣቿለን፣ ሰፈራችሁ ድረስ እናደርሳቿለን” ተብለው ተነገሩ፡፡ የጉዞ መጨረሻ ሙሉ ወንጌል ታክሲ ተራ ነበር፡፡ እዛው ያ እነ ሀና ይዞ የመጣው ታክሲ ለሌላ ሹፌር ተሰጠና እነ ሀና ይዘዋቸው ከመጡት ሰዎች ጋር ከጋና ኤምባሲ ወረድ ብሎ ወደ የሚገኝ ቤት ሆነ፡፡ ተገባ፡፡ውስጥ ሌሎች ወንድችም ነበሩ፡፡ ጫት ና ሺሻ እንደ ጉድ የሚደራበት ቤት ነው፡፡ “የሀና ጓደኛ ከዚህ በፊትም ልማድ አላት” ብሎኛል ይህንን ያስረዳኝ ሰው፡፡ ሀና ግን የመጀመሪያዋ ነበር:: ትንሽ እዚህ እንቆይና እንመለሳለን ተብላ ሻይ ተፈልቶላት እዛው “..አትፍሪ ተጫወቺ” እየተባለች ቆይታለች፡፡

ጪሱ ጪሳጪሱ ያማራት አይመስለም፡፡ ሀና እየቆየች እየደከማት፣ እንቅልፍ እንቅልፍ እያላት ሄደ ከዛም ውስጥ ወደሚገኝ መተኛ ቤት አስገቧት፡፡ ይዟትም የገባው መጀመሪያ ሹፌሩ ነው፡፡ ሀና ሰውነቷ ሞላ ያለ በሺሻ ቤት አንደበት ያልተበላችና ያልረገበች ልጅ ነው የምትባለው፡፡ ከሹፌሩ በኋላም ሌሎች ተከታትለው ገብተው ድርሻቸውን ወስደዋል፡፡ የሀና ጓደኛም እዛው ሌላ ክፍል ከሌሎች ወንዶች ጋር ነበረች፡፡ ያ ሃሺሽ እና ሺሻ ያነወዘው ስሜት ሀናን ስቃይ ውስጥ ከቷታል፡፡ በዚህ አይነት ጊዜው እየገፋ ሳለ ተማሪዎች የሚለቀቁበት ሰአት ደረሰ፡፡ ሀና ግን መንቃት አልቻለችም፡፡ እንደ ሌሎቹ ብድግ ብላ እራሷን ጠራርጋ የምትዘጋጅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ቢባል ቢባል አልተቻለም፡፡ ታክሲ መጣ፡፡ ቢያንስ ታነክሳለች ተብሎ ነበር የተጠበቀው እሷ ግን ካለችበት መነሳትም አልቻለችም፡፡ እንዲህ ሆና እንዴት ነው የምንወስዳት ተባብለው እዛው ውይይት ተጀመረ፡፡ ጓደኛዋ የሆነ መላ ፈጥራ ሀኪም ቤት እንድትወስዳት ሀሳብ ተነሳ፡፡ አይሆንም ለብቻዬ እፈራለሁ አለች፡፡ በቃ እስከማታ ልትነቃ ትችላለች እስከዛ አንዳችን ቤት ትረፍ ተባለ፣ ሹፌሩ ባለትዳር ስለሆነ ወደእሱ ቤት አይታሰብም፡፡ ሌላኛው እኔ ዘንድ ትሂድና ትረፍ ብሎ ተቀበለ፡፡ ሀናን ተሸክመው ጫኗት፡፡ የሀና ጓደኞችም ምንም እንደማያውቅ ምንም እንደሌለ መስላ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ ከወላጅ ተደውሎ ተጠየቀች አላውቀው አለች፡፡ ከልጆቹ ግን ተደውሎ እስካሁን እንዳልተሸላትና እዛው እንደምታድር ተነገራት፡፡
እንደዚህ የሆነችው ለነገሩ አዲስ ስለሆነች ነው በደንብ ከተደረገች ይሻላታል ተብሎ ማታም በቁስሏ ላይ ቁስል ተጨመረባት፡፡ አደረችበት፡፡ ቤተሰብ እስከ ትምህርት ቤት ሄዶ ነገሩን ለማጣራት ተሞከረ፡፡ መልስ አልተገኘም፡፡ ጓደኛ ተጠየቀች፡፡ መልስ የለም፡፡ ሌሎች የክፍል ልጆች ግን አብረው እንደነበሩና አብረው ሲሄዱ እንዳያቿው ተናገሩ፡፡ የክፍል ሀላፊው በፖሊስ ተያዘ፡፡ በጓደኛዋም ላይ ክትትል ቀጠለ፡፡ እስከዛ ጊዜ ድረስ ግን ጓደኛ የተባለችው ልጅ ለሀና የምትቀይረው ልብስ እንደወሰደችላት፣ እየተመላለሰችም ትጠይቃት እንደነበረ ታውቋል፡፡ ይህንን ሁሉ ለወላጅ ባትናገርም፡፡ በአምስተኛ ቀን ፖሊስ አጨናንቆ ሲጠይቃት የሆኑ ልጆች በስልክ እየደወሉ እሷን እንደሚያስፈራሯትና ታክሲ ተራ አካባቢ የሚከታተሏት እንዳሉ አድርጋ ተናገረች፡፡ ስልክ ቁጥሩንም ለፖሊስ ሰጠች፡፡ እስከ አምስተኛው ቀን ያለው በዚህ አለቀ፡፡
ከዛ በኋለ ፖሊስ የስልክ ቁጥሩን ባለቤት ሲያፈላልግ ጥቆማ ደረሰው፡፡ እነዛ ጠቋሚዎች እራሳቸው ሀና ላይ ሲከመሩ ከነበሩ ታክሲ አስከባሪዎች መካከል ናቸው፡፡ ታክሲ ተራ ወንጀል መደባበቅና ከፖሊስ ጋርም መሞዳሞድ ያለ ነው፡፡ ስልክ ቁጥሩ የታወቀበት መረጃ ደረሰውና ከአካባቢው ተሰወረ፡፡ ለፖሊሶች አዲስ ሀሳብም መጣ:: “በቃ ልጅቷን (ሃናን) ይለቋታል እናንተ ወላጆቹን አሳምኑልን” የሚል ነገር፡፡ ፖሊስም ነገሩን ጠለፋ አድርጎ ስለወሰደውም ጭምር ነገሩ በሰላም የሚፈታ ከሆነ ብሎ ለተከታታይ አምስት ቀናት ወላጆችን የማጽናናትና እየደረስንበት ነው ታገሱ እያሉ ቆይ፡፡ ሌላ አምስት ቀንም ቢጨመርበት የሀና ቁስል እያመረቀዘ ሄደ፣ እራሷን መቆጣጠር ሳትችል ቀረች፡፡ ፖሊስ ቀነ ገደብ ሰጣቸው – ለአፋኞቹ፡፡
“ሃናን በቶሎ ካለቀቃችሁ እርምጃ እንወስዳለን” የሚል፡፡ በመጨረሻ በ11ኛው ቀን ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አካባቢ በታክሲ አምጥተው ጣሏት፡፡ የሐና ጓደኛ ጨምሮ ሌሎች ሁለት ወንጀለኞች በዛው ታክሲ ከአካባው ተሰወሩ፡፡ የሐና እዛው መጣል ወላጅ ዘንድ ደረሰ፡፡ ሄዱ፡፡ መጀመሪያ ላይ ፖሊስ ነገሩን እንደማያውቅ ሆኖ ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ነገሩን የአየር ጤና አካባቢ ፖሊስ የነበረ ቢሆንም; ፖሊስ የሚከታተለው ልጅቷን ከማትረፍ ይልቅ ወንጀሉን የሰሩትን ልጆች ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት አድረጓል፡፡

አሁን ወደ እነዛ ታክሲ ተራዎች ስትሄዱ ልጅቷ የተደፈረችው በአምስት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እዛ በሺሻና በጫት መርቅነው የነበረና ለጋ ገላዋን እያዩ ምራቅ ይውጡ በነበሩ ሁሉ ናቸው፡፡ ከአምስት በላይ፡፡ አስገድዶ በመድፈር ሁሉም ወንጀሎች ቢሆንም ልጅቷን ለሞት የሚያደርስ ወሲብ የፈጸሙባት ሰዎች ግን ከፖሊስ ጋር ተባባሪና ጠቋሚ መስለው በመቅረባቸው እስካሁን አለመያዛቸውን እየተነገረ ነው፡፡ በተለይ ልጅቷ ወሲብ ሲፈጸምባት ለብዙ ሰአታት እራሷን ስታ ስለነበረ በእሷ ላይ በትክክል ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱትም ወንጀለኞች መለየት አትችልም፣ ፖሊስ ግን ጥቆማ ተሰጥቶታል ሊቀበል ግን አልፈለገም እየተባለ ነው፡፡ በተለይ የጉሮሮና የፊንጢጣ ችግር ያደረሡባት ሰዎች ተጠቃለው አልታሰሩም፡፡
ፖሊስ ልጅቷ በሺሻ ቤት መደፈሯንም እንዲነገርበት አይፈልግም፡፡ ፖሊሶቹ ሌላም የሚሸፋፍኑት ነገር አለ:: ወላጆችን “ተጽናኑ እየተገኙ ነው” ብሎ በጎን ከወንጀለኞች ጋር ሲደራረር እንደነበረም እንዲታወቅበት አይፈልግም፡፡ ሀና ጦር ሀይሎች አካባቢ የተጣለችውም ፖሊስ ያደርገው በነበረው ድርድር መሆኑንም እንዲታወቅበት አይፈልግም፡፡ እዛ መጣሏን እያወቀ ልጅቷን ወደ ሀኪም ቤት ከመውሰድ ይልቅ ወላጅ አባት ሳይቀሩ ሲያመለክቱ በዳተኝነት ነገሩን ለማድበስበስ የሞከሩትም ለዛ ነው፡፡ እንዲሁም ፖሊስና የታክሲ ተራ የ1ለ5 አደረጃጀት መዋቅር እንዲፈርስ ስለማይፈለግ በሀና ላይ ችግር ያደረሱ ግን መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጋር የተባበሩ የተባሉ ወንጀለኞች እስካሁንም አልተያዙም፡፡ የተያዙት ሀና በነቃ አእምሮዋ ሆና ችግር ሲፈጥሩባት ያየችውን ብቻ ነው፡፡

የሐናም ጓደኛ በተላላኪነት ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት እየመለመለች ለሌሎች የማስበላትና የማታለል ተግባሯ ፣ ወንጀለኞች ያሉበት ቦታና ማንነታቸውንም በደንብ እያወቀች ለወንጀል ተባባሪና ዱላ አቀባይ መሆኗ ግምት ውስጥ ሳይገባ፣ ለፖሊስ መረጃ መስጠቷና በተራ አስከባሪዎች ዘንድ ጥብቅና ስለተቆመላት አልተያዘችም፡፡የእሷ መያዝ ሌሎች አስወጊ ተማሪዎችምን ለስጋት ስለሚዳርግና የተማሪን ገላ የለመዱ ቡድኖችን አንሶላ ስለሚያርቁት እንዲሁም በተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የወሲብ ንግድ ችግር ያጋጥመዋል ገቢያችንን ያስቀርብናል” ሰለተባለ ይመስላል (ቦስተን ማራቶን ላይ ቦምብ በተደረገ ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ወንጀሉን እያወቅ እንዳላወቀ ሆነሀል ተብሎ መከሰሱና እንደታሰረ ልብ ይሏል)፡፡ ፖሊስ ሀና ትማርበት የነበረውን ትምህርት ቤት ስም በመግለጫው እንዳይጠቀም በትምህር ቤቱ ልመና ቀርቦለታል፡፡ የሺሻ ቤት አላፊው አልተያዘም፣ ስሙም አልተነገረም፡፡ ፖሊስ ከተወሰኑ ደጋፊ ሚዲያዎቹ ጋር ሆኑ ህዝብና ፍትህ ላይ እየቀለደ ነው፡፡ ልመናው ምን እንደሚያጠቃልል ግን በደንብ አልተገለጸም፡፡
አሁን በሀና ጉዳይ የፖሊስ ሚና እንዳየነው ፖሊስ እራሱ የወንጀል፣ በሴት ላይ ለሚደረግ ጥቃት ተባባሪ ብቻ ሳይሆን ከፍ ያለ ተዋናይ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሀና ወደ ሀኪም ቤትም ሄዳ ህክምና ማግኘት አልቻለችም፣ ለሀና ሞት የህክምና ተቋማችንም በዋናነት የፖሊስ አሰራርም ጭምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ድርጓል፡፡ አሁን እየሆኑ ያሉ ዘገባዎችና ዘመቻዎች ባብዛኛው ፖሊስ የሰራውን ወንጀል የመደበቅ ተግባር ነው፡፡ በሀና ጉዳይ ሳይነሳ መተው የሌለበት ግን “ትማርበት የነበረው ትምህርት ቤት እንዴት ተማሪዎች በትምህርት ሰአት እንዲወጡ ለምን አደረገ ታማ ከሆነም የተፈቀደላት ለወላጅ ተደውሎ ለምን አልተነገረም?” የሚል ጥያቄ ነው!!
ከሀና ታረክ ጋር በተያያዘና የሳያት ደምሴንም ጉዳይ ማንሳት ይቻላል፡፡ ሳያት ደምሴ ከጥቂት አመታት በፊት ጦር ሀይሎች አካባቢ አፍሪካ ኮከብ ተብሎ በሚጠራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትማር ነበር፡፡ አስረኛ ክፍል፡፡ እንዲሁ በጓደኛ ግፊት ሺሻ ቤት ገብታ በታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶች እንደተደፈረች እናስታውሳለን፣ ለሰባት፡፡ ሳያት የተደፈረችበት ቤት እስካሁንም ፖሊሶች የሚቅሙበት ቤት ነው፡፡ እንዳውም ቅርንጫፍ ሺሻ ቤት ተከፍቷል:: አማኑኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ያለው የራዲካል ት/ቤት ተማሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ይህ ሺሻ ቤት ከራካዲል ት/ቤት ቢያንስ በ400 ሜትር ርቀት ነው የሚገኘው፡፡ በጋራጅ ስለተሸፈነ አይታይም ብዙ የት ይደርሳሉ የተባሉ ቆነጃጅት ሴቶች ገብተው በቡድን ሳይቀር የሚደፈሩበት ቦታ ነው፡፡
እኔ በግሌ ብዙ ጊዜ ለፖሊስ አመልክቻለሁ የሰማኝ ግን አላገኘሁም፡፡ አሁን አሁን ሊፒስቲክ ተቀብተው እንደሴት የሚያደርጋቸው ወንዶች ሳይቀሩ ሲወጡበትና ሲገቡበት አያለሁ፡፡ እዚህም ባብዛኛው ተማሪዎችን እየቀጠፉ ያሉት፣ አንዳንድ የታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶች እንዲሁም ስድ ጋራጅ ሰራተኞች ናቸው፡፡ ቦታውን በደንብ ለመጠቆም ከራዲካል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ካለው የወጣቶች ማእከል አቅጣጫ ወደ ኮካ በሚወስደው መንገድ የገንዳ ማስቀመጫው አካባቢ ነው፡፡ በጣም ብዙ ህጻናት የሚደፈሩበት ቦታ ነው፡፡ በሺሻ ቤት ምን ያህል የቡድን ወሲብ እንዳለ የሳያት ደምሴን ነገር ሰምተን በቀልድና በማላገጥ ማለፋችን አሁን በሀና ላይ ለደረሰው ነገር እንዳበቃን ልብ ልንልም ይገባል፡፡ ይህ ተማሪዎችን የማጥቃት ዘመቻ እስከ ትልልቅ ሆቴሎቻችን ድረስ እንደሚደርስ እንዲሁም በዚህ ነገር ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ደላሎች እንዳሉበት እድሜያቸው ሳይፈቅድላቸው በብርና በተማሪ ደላላ ተታለው ብዙዎች እየተቀጠፉ እንደሆነ በእነ ሀና ላይ የደረሰው ነገርም ሳይቅድሙን እንቅደማቸው በሚል ስሌት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ እንደእውነት የሀና መደፈር በሀገር ውስጥ ሰው መሆኑን እንጂ ህገወጥ እያልን ያለነው በየሆቴሉ የብዙዎች ህይወት እንደሚያልፍ ይህም ወንዶች ሳይቀሩ ያሉበት መሆኑን፣ ይህም በተለያየ ጊዜ በቪሲድ ሳይቀር ያየነው እውነት መሆኑን የሚታወቅ ነው፡፡ ፍትህ ለተማሪዎቻን!!! ፍትህ ለሃዎች!! ፍትህ ለዜጎቻችን!!
unnamed

———————————————————
ሀና መዳን ጀምራ ነበር ፍርድ ቤት ላይ ቆማ እንዴት እንደምትመሰክርም መለማመዷን ድግሞ አንድ ውስጥ ሌላ ሰው ያስታምም የነበረ ሰው እየነገረን ነው፡፡ ታዲያ ድንገት እየዳነች የነበረች ልጅ የሞተችው እንዴት፣ በማን ስህተትና ጥፋ ወይም ሸር ነው እንበል? ሀና ለምን በምን ሞተች? ስለተደፈረች?
————–
ሀና በዘውዲቱ ሆስፒታል!!

እህታችን ሀና ላላንጎ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ህክምና ለማግኘት ስትል የብዙ ሆስፒታል ደጆችን ረግጣለች። ለመጨረሻ ጊዜ ግን ህክምናዋን ስትከታተል የነበረውና ህይወቷም ያለፈው በዘውዲቱ ሆስፒታል ነበር።
ዘውዲቱ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ትከታተል በነበረበት ሰዓት የማውቀው ወዳጄ ሀና የተኛችበት ክፍል ውስጥ የታመመች ጓደኛውን ያስታምም ነበር። እሱ ጓደኛውን ሲያስታምም የሀናን የህመም ስቃይ አብሮ ተጋርቷል። ብዙ የማይነገሩ ስቃዮች ነበሯት። ይሄ ጓደኛዬ ሀና በሆስፒታል ውስጥ የሆነቻቸውን ሁለት አጋጣሚዎች ለኔ በውስጥ መስመር ነግሮኝ ነበር። እኔ ደግሞ ለናንተ ልንገራችሁ።
አንድ!
_____

ፖሊስ ‘ወንጀለኞቹ ናቸው’ ብሎ ከያዛቸው ተጠርጣሪዎች መሀከል አንደኛውን ተጠርጣሪ ፖሊስ ጥርጣሬውን በማስረጃ ለማስደገፍ ሲል ዘውዲቱ ሆስፒታል ድረስ በካቴና አስሮ ተጠቂዋ ሀና ፊትለፊት አቆመው።
ተጠቂዋ ሀና ‘ተጠርጣሪ’ ተብሎ የመጣውን ‘ሰው’ ስታይ በጣም አለቀሰች። ‘አንደኛው እሱ ነው’ ስትልም እያለቀሰች አረጋገጠች!! ተጠርጣሪው ግን ካደ። ክፍሉ ውስጥ ያሉ አስታማሚዎች ካልገደልነው ብለው ተነሱ። ተጠርጣሪው መካዱ እንደማያዋጣው ሲያስብ ሌላ የሚዘገንን ምክንያት ሰጠ። በኋላ ግን አመነ። በዚያ ክፍል ውስጥ የአስታማሚዎች የታማሚዎች እምባና ጩኸት ሞላው። ፖሊስ ቃሉን ይዞ ተጠርጣሪውን እንደታሰረ ከሆስፒታሉ ይዞት ወጣ!!
ሁለት!
_____

የሀና ህይወት ከማለፉ በፊት ለነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ በአካል ተገኝታ ችሎት ፊት ቀርባ ቃሏን እንደምትሰጥና እንደምትመሰክር ከተነገራት በኋላ ‘ችሎት ፊት ስቀርብ እንዲዚህ ብዬ ነው የምናገረው’ እያለች በሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ ልክ ፍርድ ችሎት ውስጥ እንደቆመችና ዳኛው ፊት እንደቀረበች ሁሉ አክት እያደረገች ክፍሏ ውስጥ ላሉ ታማሚዎችና አስታማሚዎች ፊት ልምምድ ታደርግ ነበር!!
ሀና የሆነ ህልም ነበራት። ጥቃት ያደረሱባትን ወንጀለኞቹን በህግ ተፋርዳቸው ትክክለኛውን ፍርድ አስፈርዳና አስቀጥታቸው ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የእሷ አይነት በደል ለደረሰባቸው ሴቶች የፍትህ ተምሳሌትና ለመሆን ‘ከኔ በኋላ እንደዚህ አይነት በደል ይብቃ!” ለማለት!! ይመስለኛል!!
እናም ለሀና እና ለሀናውያን ትክክለኛና ፍትሀዊ ፍርድ እስኪገኝ ድረስ “ፍትህ ለሀናውያን” እንላለን!

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.