የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ተከዜን ተሻግሮ እስካሁን በሃይል የወሰዳቸው የጎንደር ወልቃይትና ፀገዴ ቦታወች ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ፀለምት፡ እና ከፀገዴ ከነበሩት ጠቅላላ 39 ቀበሌወች ውስጥ 25ቱን ቀበሌወች ወደ ትግራይ ወስዶ አንድ ወረዳ የመሰረተ ሲሆን ወደ አማራ ክልል ከፀገዴ የቀረው 14 ቀበሌ ብቻ ነው። አካባቢው በለምነቱ የታወቀና ድንግል መሬት ያለበት ሰፊ አካባቢ ሲሆን በብዛት የሚመረቱት የአዝርዕት አይነቶች ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ ስኩኣር አገዳ፣ ፍራፍሬና አትክልት በስፋት ይመረታሉ።
በዚሁ በወልቃይት ፀገዴ አካባቢ የሚገኙና ወደ ትግራይ የተወሰዱ ትላልቅ ከተሞች ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ /ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞች ተወስደዋል። የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህንኑ የመስፋፋት ስስቱን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት አንገረብ ወንዝን በመጠቅለል የፀገዴ ቀሪ ቀበሌወችን እና የታች አርማችሆ ለም መሬትን ለመውሰድ እየተዘጋጀ እንደሆነ ያካባቢው ጭብጦች ያስረዳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይትና የፀገዴ ህዝብ አሁንም በጉልበት የተነጠቀውን የጥንት የጠዋቱን መሬት ለማስመለስና መብቱን ለማስከበር ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ለትግሉም መላው የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም የአማራ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ እያቀረበ ነው።
ይህንን የተረዳው የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅትም የሚያጋጥመውን የህዝብ ተቀዋውሞ ለመጨፍለቅና ያሰባቸውን ተጨማሪ መሬቶች ለመውሰድ ባካባቢው የተለያየ የፀጥታ ሃይሎችን እያደራጀና እያዘጋጀ ነው።
ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶችም፡-
1ኛ. 120 የትግሬ ተወላጆች በልዩ ሁኔታ ተመልምለው በሁመራ ከተማ ለሁለት ወር ያክል ልዩ ስልጠና በሚስጥር ተሰጥቷቸው ስልጠናቸውንም ነሃሴ 7 2006 ዓ.ም አጠናቀዋል። የነዚህ ልዩ ሰልጣኞች ተልዕኮ በወልቃይት ፀገዴ ውስጥ ትግሬ አይደለንም አማራ ነን የሚሉትን እና መሬታችን ይመለስ የሚል ጥያቄ የሚያነሱትን እየለዩ እንዲደበደቡ እንዲገርፉ እንዲያስሩና እንዲገድሉ የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህ ገዳይ የወያኔ ሚሊሻወች ቋሚ ደመወዝና ቀለብም የሚሰፈርላቸው ሲሆን የሚመሩትም በህወሃት ከፍተኛ መሪወች እንደሆነ ታውቁኣል።
2ኛ. የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት በወረራ የያዛቸውን የጎንደር ወልቃይት ፀገዴን መሬት አስተማማኝ በማድረግ የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ ይረዳው ዘንደ በፀለምት ዲቪዝን ከተማ 1500 የሆኑ የትግሬ ተወላጆች ከተለያዩ የፀጥታ ተቋሞች በማውጣጣት በዚሁ ከተማ አደራጅቶና አዘጋጅቶ ለማንኛውም የአካባቢው ስራ ዝግጁ አድርጎ አስቀምጧቸዋል። እነዚህ አባላት አብዛኛወቹ የቀድሞ የህወኃት አባላት የነበሩ ሲሆኑ ከመከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስና ከትግራይ ፈጥኖ ደራሽ /ልዩ ሃይል/ ከሚባሉት የፀጥታ መዋቅሮች ተውጣጥተው የተደራጁና በተጠንቀቅ ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ናቸው።
3ኛ. ይህንኑ እንቅስቃሴ ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ የትግራይ ልዩ ሃይልም ማዕከሉን ማይካድራና ዳንሻ አድርጎ እንዲቀመጥና ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን ተደርጉኣል። በተጨማሪም ተከዜን ተሻግሮ የሰፈረው የትግራይ ተወላጅ በሙሉ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቅ ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይም በፀገዴ ወረዳ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ግደይ አዛናው የተባለውና የዚሁ አስተዳዳሪ አባት የሆኑት የምድረ-ገበታ ቀበሌ አስተዳዳሪና የወያኔ ተቀጣሪ ካድሬ አቶ አዛናው ገብርየ በትውልዳቸው የደባርቅ ተወላጅና አማራ ቢሆኑም በጥቅም በመገዛት አማራነታቸውን የከዱና የፀገዴ ህዝብ አማራ አይደለህም አማርኛ እንዳትትናገር እያሉ በስብሰባ ሁሉ የሚቀሰቅሱና ፀገዴን ለመሸጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ካሉት ባንዳወች ግንባር ቀደሞቹ በመሆናቸው በአካባቢው ህዝብ ጥርስ ውስጥ መግባታቸው ታውቁል።
ሌላ በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ አቶ ካሳሁን ሲሳይ የተባለ በፀገዴ ወረዳ ምድረ-ገበታ ቀበሌ ይኖር የነበረ ሰው በ1982 ዓ.ም ህወኃት በማናለብኝነት የወልቃይት ፀገዴን መሬት በሃይል ሲወስድ ከተቃወሙት ሰወች አንዱ ስለነበር፣ በወቅቱ የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰውየውን ይዘው ገርፈውና አስረው ሽሬ በመውሰድ ለ20 አመት ያክል ካሰሩት በኋላ በሃምሌ 2006 የፈቱት ሲሆን ሰውየው ከስር ተመልሶ ወደ ቀየው ሲመጣ “ይህ ያንተ አገር ስላልሆነ እዚህ መኖር አትችልም” ተብሎ ከተወለደበት፣ እትብቱ ከተቀበረበትና ካደገበት ቦታ በአሳዛኝ ሁኔታ እንዲባረር ተወስኖበት እንዲሰደድ ተደረጉኣል።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.