-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
Minilik Salsawi
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ከቤት በማስቀመጥ እና በማዝናናት ያሳልፋሉ የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን በልባቸው ላይ በተገጠመላቸው አርቴፊሻል መሳሪያ በጤንነታቸው ላይ ከባድ እክል እንደፈጠረባቸው እና ከወራት በፊት ሳኡድ አረቢያ ታክመው ቢመጡም ሊሻላቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ቢሄዱም ሆስፒታሉ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ሲታወቅ ከሕክምና መልስ ወደ ቢሯቸው የገቡት በጣት የሚቆጠር ቀናት እንደሆነ ታውቋል::
ይህን ሰሞን ስብሰባ መምራት አለብህ በሚዲያ መታየት አለብህ የሚል ግዳጅ ከሕወሓት ባለስልጣናት ወርዶላቸው የተደናበሩት አቶ በረከት ማገገም እንኳን ሳይችሉ በስራ መደራረብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው ሲሉ ከቤተሰባቸው አንዱ የሆኑት ሲናገሩ ተሰምቷል::አቶ በረከት በከፍተኛ ህመም ውስጥ እንዳሉ ሲታወቅ የሕወሓት ባለስልጣኖች የአዜብን ቡድን እንደመቱት ወዲያው በረከትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ አሽቀንጥረው ካሳንቺስ አዲስ ቢሮ እንደሰጡት ሲታወቅ መገፋቱ እያንገበገበው በሽታውን እንዳባባሰበት ታውቋል::
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.