ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከህዝብ የተሰባሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው ህዝቡ በሙስና በመማረሩ ስራ መስራት በማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሙስና የሚጠይቁ ሰዎችን ማጋለጥ ህይወትን እስከ ማስከፈል እንደሚደርስም የተሰባሰበው መረጃ ያመለክታል።
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት ሙስናን ለማጋለጥ ቢፈለግም ፣ ለሚያጋልጡ ሰዎች በቂ የሆነ የህግ ከለላ አያገኙም
ሙስናን ለማጋለጥ ስንሄድ “ጀርባቸው ይጠና ተብለን እንደገና ጉዳቱ ሙስናን በምናጋልጥ ሰዎች ላይ ” ይሆናል ያሉት አንድ የሚሊሺያ አባል ፣ ይባስ ብሎ ደግሞ አሸባሪዎች እንባልና ችግር ይደርስብናል ብለዋል
ሙስናን የማናጋልጠው ተፈጻሚ አይሆንም በሚል ነው የሚሉት አንድ የቀድሞ የትምህርት ባለሙያ ደግሞ ሙስናን በመዋጋታቸው ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። የባለስልጣናት ሃብት ቢመዘገብም እስካሁን ይፋ አለመደረጉን አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል
ጸረ ሙስና የተባለው መስሪያ ቤት ራሱ አገሪቱን እያጠፋ ነው የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ የባለስልጣናት ልጆች በውጭ አገር እየተመሩ እኛ መጠለያ ለማግኘት በማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ብለዋል
በሙስና ላይ ህዝቡ የሰጠውን አስተያየት በልዩ ዝግጅት የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.