Sunday, January 11, 2015

ሰሚ ያጣ ጮኸት ከካርቱም – አጥናፉ መሸሻ

 በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጽያዊያኖች ሁሉ    ፤ በተለያዩ ግዜያት  ሰብአዊ  መብታችን  ይከበር ዘንድ ፤  ከምድር ሱዳን የሲቃ ጮኸታን ሰምታችሁ  በተቻላችሁ መጠን ትታደጉን ዘንድ ደጋግመን በፁሁፍ አሰምተናል ፤ እንሆ  በአሁኑ ሰአት ወያኔ ከምንግዜውም በላይ በከፋ መልኩ  ፤ ካርቱም ውስጥ  ስደተኛውን አንደተለመደው እያሳፈሰ ፤ ወዳልታወቀ እስር ቤት እያሳወሰደ ይገኛል ፤ በተለይ ጀዋዛት እየተባለ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ፤ በሸህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ታጉሮው ይገኛሉ ፤ ከእነዚህም ውስጥ ለልደት ደሮ ለመግዛት ገበያ የሔዱ እህቶቻችን ከነደሮቸው ፤ ልደትን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን አክብረው የሚመለሱ ነጭ የለበሱ ወገኖች  እስር ቤቱን ሞልተውታል ፤ በተጨማሪ ዴም እየተባለ ከሚጣረው ሰፈር ውስጥ አንድ ወጣት ሀለፎም አዲሱ ተካልኝ የተባለ የአንገት መስቀሉን በጥሰው መኪና ላይ ጭነው እስር ቤት አጎረውት ይገኛል ፤ መታወቂያ ለማውጣት እድሜው የማይፈቅድ ወጣት ሳይቀር  ያለ አንዳች እርህራሔ አስር ቤት ይገኛል ፤ ይህን ወጣት እንደምሳሌ ተጠቀምንበት እንጅ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን አናሳስባለን;;
ዛሬ አንባገነኑ ወያኔ ፤ በከፍተኛ መረበሸ ውስጥ አንዳለ ፤ እድሜው እያጠረ ፤ የቆመበት መሬት እየከዳው መሆኑን  እንገነዘባለን ፤ ለዚህም ሱዳን ሀገር የሚኖረውን ስደተኛ ፤ ከኤርትራ በኩል ከሚንቀሳቀሱትና ከሌሎች በነፍጥ ከሚታገሉት ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው ስለሚየምኑና ፤  እንዲሁም ሰሞኑን በሱዳን አጎራባች አርማጭሆ አካባቢ በተፈጠረው ሁኔታ በመስጋት ፤ ካርቱም የሚኖረውን ስደተኛ ሕጋዊ የሰደተኛ መታወቂያ ፤ በየሶስት ወር የሱዳን መንግስት ሲያድስ የነበረውን፤ ኢትዮጽያዊ ስደተኛ የለም በማስባል ፤ መታወቂያችን ወያኔ ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል መታወቂያ እንዳይታደስ አስደርጎል ፤ ይህም ማለት ፤ የሚፈልጉትን ስደተኛ   በአፈሳ መልክ አፍነው እንዲወስዱ ያስችላቸዋል ፤ ባሳለፈነው ወር የወያኔ ምክር ቤት ያፀደቀወን  በአሸባሪና ወንጀለኛን ስም ስደተኛውን አሳልፍ በመስጠት የተደረገውን የትብብርን ውል ልብ ይሎል ፤ በተጨማሪ ጀዋዛት እየተባለ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ   የታጎሩትን የስደተኛ መታወቂያ የያዙትን እያሳነጠቁ ፤  ወያኔ ከሱዳን መንግስት ጋር በመመሳጠር ፤ አለማአቀፍ የስደተኞችን ህግ በመጣስ ፤ ስደተኛ መብትን በመንፈግ  ሕገ ወጥ በሆነ  አሰራር መታወቂያ አስር ቤት ውስጥ አስገድደው ፎቶ እያስነሱ ስደተኝነትን የማይገልፅ መታወቂያ በመሰጠት ላይ  መሆናቸውን አጥብቀን እንናስገነዝባለን ;;
ባሳለፍነው ወር የወያኔን መሰሪ ተንኮል ማጋለጣችን ይታወቃል ፤ ይኸውም ስደተኛውን ማህበረሰብ ቅጥ ባጣ አፈሳ በማስመረር በወያኔ ሰላዮች አማካኝነት የወያኔ ኢንባሲ ካርቱም ውስጥ በ28/11/2014 ሰላማዊ ሰልፍ አስደርገውል ፤ የሰልፉም አላማ   የኢሳትን ሚዲያ በመጠቀም ፤ ወደ ሀገራች አንግባ የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ የታቀደ ነበር ፤ እነዚህ ሰብአዊ ክብር ያልፈጠረባቸው ቅጥረኞች  በግፍአን እንባ አንዳላገጡ እንረዳል ፤ በተጨመማሪ እነዚህ በደል የበዛባቸው ወገኖቻችን ፤ለጥያቂቸው መልስ የሚያገኙ መስሎችው ተመልሰው ወያኔ ኢንባሲ በሳምንቱ ሔደው ማንም ሳያናግራቸው በመጡበት አኾሖን ተመልሰዋል;;
ውድ ወገኖቻችን ፤ ሱዳን ሀገር ውስጥ የሚደረሰውን በዝምታ የማይታለፍ በደል ከከፈ ደረጀ ከመድረሱ  በፊት ፤ በመላው ዓለም የምትገኙ ለሰብአዊ መብት መከበር የምትታገሉ   አለም አቀፍ ትብብር የፈጠራችሁ ወገኖች ሁሉ ፤ዛሬም ጨኻታችን ጣራ አልባ እንዳይሆን ፤ ለሱዳን መንግስትና ለዩ ኤን ኤች ስ አር በተቀነባበረ መልኩ ሰብአዊ መብታች ይከበር ዘንድ ፤  በሱዳን ሀገር የምንገኝ ኢትዮጽያዊያን ልሳን ትሆኑን ዘንድ  በአክብሮት እንማፀናለን ;;       ባሳለፍነው ወር 2000 ወገኖቻችን  የ ኤች አይቭ ና የሀቢታይትስ በሸተኞች ናቸው ተብለው ፤ ገንዘብ ንብረታቸውን ሳይውሰዱ ከሱዳን ሲባረሩ  አንድም ተቆርቆሪ ዜጋ የነዚህ ግፍአን     ልሳን ሳይሆን በመቅረቱ  ልብን ያደማል ፤   አሁንም ፤ አሁንም ፤ ይኽ የወያኔ ተንኮል በሰፊው ሳይደገም አፋጣኝ ወገናዊ ትብብራችሁን አንጠይቃለን;;
አጥናፉ መሸሻ

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.