Sunday, February 22, 2015

የISIS ሁኔታ አቅሎ ማየት እና መደባበስ ሳይሆን ትክክለኛውን ነገር በመናገር በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማስቆም ያስፈልጋል

ISIS Ethiopia

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

የISIS ሁኔታ አቅሎ ማየት እና መደባበስ ሳይሆን ትክክለኛውን ነገር በመናገር በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማስቆም ያስፈልጋል!!!
ልናውቀው የሚገባው ነገር ቢሮር ነገሮችን በመደባበስ አልያም በፍራቻ ልናልፋቸው የምንሞክረው ነገር ካለ አደገኛነቱን ከመጨመር ውጪ የምንቀንሰው ነገር እንደሌለ ልናውቀው ይገባል። ዛሬ ልናገር የምፈልገው የISIS እንቅስቃሴ ከአገራችን ሁኔታ ጋር በማያያዝ ነው። ለዚህ ቀውስ ዋና አቀጣጣይ እና ይሄ እንቅስቃሴ እንዲከሰት የሚፈልገው የተቀናጁ እና የተደራጀ ሃይል ያላቸው ነው። ወያኔ ከስልጣን የማውረዱ እንቅስቃሴ በቅርብ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ስለሚኖር እናም በህዝብ ሃይል እንደሚደመሰስ ቢታወቅም በዚህ መሃል ሊመጡ የሚችሉትን አደጋ ለመቆጣጠር ፖለቲከኞችም ሆኑ ህዝቡም የISIS እንቅስቃሴን በንቃት እና በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል።

ISIS ማን ነው? አላማውስ ምንድን ነው ብለን ስናይ ISIS ማለት Islamic State of Iraq and Sorya ማለት ሲሆን መጀመሪያ አነሳሱ ኩርዲሽ የራሳቸውን ይዞታ ለመፍጠር የተለያየ እንቅስቃሴ በማድረግ ይታገሉ ነበር። ኩርዲሾች በአምስት ሃገር ውስጥ የሚሮሩ ሲሆን እንዚህ በአምስት አገር መሃል ያሉት ኩርዶች የራሳቸው ግዛት እንዲኖራቸው የመፈለግ እንቅስቃሴን ያካሂዱ ነበረ። ለአምስቱም አገር ኩርድ የራሳቸው አገር እንዲመሰርቱ ጥያቄዎችን አቅርበው የነበረ ሲሆን። ከእነዚህ አገራት የተሰጣቸው መልስ ይህ አገር የናንተ አገር ነው እንደዜጋ በሃገራችን ያለምንም አድሎ መኖር ትችላላላቹ አይ አንፈልግም ካላችሁ ግን ለቃችሁ መሄድ ትችላላላችሁ ከአገራችን ቁራሽ መሬት አታገኑም የሚል ነበረ። በተለይ ቱርክ ውስጥ ሰፊ መሬት ላይ የሚኖሩት ኩርዶች ቱርክ ጠንከር ያለ ነገር እንደተናገረች ይታወቃል። እነዚህ አምስቱ አገር ቱርክ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ኢራን እና አርመን ሲሆኑ በአምስቱ አገር የሚኖሩት ኩርዶችን የራሳቸው ግዛት እንዲኖራቸው በመፈለግ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በኃላም ይሄ ትግል አዋጪ አለመሆኑን ሲያውቁ እንቅስቃሴውን በመቀየር ISI Islamic State of Iraq በማለት እንቅስቃሴአቸውን ማድረግ ጀመሩ። በዚህም ቀላል የማይባል የሰው ኃይል አላማቸውን በመደገፍ ተቀላቅለዋቸዋል። ISI ከ2006-2013 ድረስ ከቀጠለ በኋላ ለሶስተኛ ግዜ ሃሳቡን በመቀየር ከፍ በማድረግ ISIS Islamic State of Iraq and Sorya በሚል የበለጠ የሰው ኃይል በማግኘት ለሙስሊሙ የሚታገሉ በማስመሰል ሃሳባቸውን ከፍ አድርገውታል።June 2014 ላይ Islamic State በማለት በካርታ በተደገፈ በማውጣት ካርታው ላይ ያሉት አገራት በሙሉ እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ አዋጅ አውጀው መንቀሳቀስ ጀመሩ።የዚህን ግዜ በርካታ ሙስሊም ሱኒ(suuni) በመቀላቀል ኃይላቸውን እያጠናከሩ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ከተለያየ አለማት ተቀላቀሏቸው። ለዚህም ማስረጃ የሚሆን የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሱማሌዎች።የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው እንዲሁም በኖርዌይ ውስጥም የኖርዌይ ፓስፖርት ያላቸው የሱማሌ እና የኤርትራ ትውልድ ያላቸው ሙስሊሞች መሳተፋቸው እንቅስቃሴው ምን ያህል እንደሰፋ ማየት ይቻላል።
ISIS በአሁኑ ሰአት አላማውን ግልጽ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ በእስልምና ስም አላዋ ክበር በማለት ሁሉንም ክርስቲያንን ብቻ ለማጥፋት ሳይሆን በሌላ እምነት ያለውም በሙሉ የሚያጠፋ ኃይል ነው። ሌላው ቀርቶ እስላምም ሆነው ሱኒ(Sunni) ካልሆኑ ኢሻ(Shia) የሆኑት ምስሊሞች ሁሉ የሚያጠፋ ምንም ሰባዊነት የማይታይበት የዘመኑ አረመኔ እና አደገኛ ቡድን ነው። ቃስ በቃስ እንቁላል በግሯ ትሄዳለች ይላሉ አበው። ይህ ቡድን መጀመሪያ ስለ ድንበሩ መታገል ጀመረ ቀጥሎም ኢራቅን ሱኒ ሙስሊም ለማድረግ ተንቀሳቀሰ ከዛም ሶሪያ ጨምሮ መንቀሳቀስ ቀጠለ በኋላም አላማው ፍጹም ተቀይሮ ኢስላም ስቴት ለመመስረት ካርታ በማስቀመጥ በግድ ሊሰልሙ የሚገቡትን አገራትን ይፋ አድርጓል። እንቢ ያሉትን እንደ በግ ሊያርድ አልያም መሬት ላይ አጋድሞ በጥይት መረሸን የ አልያም በጥይት አናት አናት እየመቱ ወደ ባህር መወርወር የምናየው ሃቅ ነው።
ታዲያ ይህ አደገኛ ኃይል ከፊለፊቱ ያሉትን በሙሉ እያረደ እና እያጠፋ አረመኔአዊ ተግባር የሚሰራ ሴጣናዊ ተግባር የሚያራምድ ቡድን ነው። ISIS አለም እያወገዘው ቢገኝም የተለያዩ ደግሞ የማለባበስ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። እውን የማለባበስ ስራ የሚሰሩት በራፋቸው ሲመጣ በማለባበሳችን ሊያልፈን ይችላል ብሎ መገመት አልያም እኛ መንደር አይገባም ብሎ ማሰብ በጣም የዋኅነት ነው። ብልጥ ከሰው ይማራል ሞኝ ግን በራሱ ይማራል የሚባለው ነገር ተፈጻሚነት እንዳይሆንብን ነገሮችን ቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው።

ታዲያ ISIS ኢትዮጵያን ሊያሰጋት እንዴት ይችላል? ኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያኑ እንዲሁም ዋቄ ፈናም አልያም የአይሁድ እምነት ከእምነቱም የሌለበት ጥምር ተዋደው ያሉባት አገር ላይ ነው ያለነው ብለን እናስብ ይሆናል። ማሰባችን መልካም ነበረ ግን ሃሳባችን ትክክል ነው ወይ? ግምታችንስ ምን ያህል ወደ እውነቱ የቀረበ ነው? ካልን አከራካሪ ነጥቦችን እናስተናግዳለን። ለመከራከር ሳይሆን የሌላው እምነት ማለትም ከእስልምናው ውጪ ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በአንክሮት ሊያስቡበት እና ሊታገሉት በገኃድም ሊቃወሙት የሚገባ ሴጣናዊ አካሄድ ስለሆነ ስለዚህ አደገኛ ቡድን ትንሽ ልጠቋቁምና ሁሉም ተወያይቶበት የራሱን አስተያየት እንዲሰጥበት እፈልጋለው።
የአለማችን ስጋት የሆነው ISIS የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መቃወም እስልምናን መቃወም መስሎ የሚታያቸው ሙስሊም ወገኖቻችን አሉ። እንደ እኔ አመለካከት ከእውነት የራቀ ነው። ለምን ቢባል ሁሉም ሙስሊም ISIS ደጋፊ አይደሉምና። እንደውም ISIS ሺአ(Shia) ሙስሊሞች በነዚህ ቡድኖች ማለትም በሱኒንዎች(Sunni) መስኪዳቸውን በማቃጠል ጭምር የሚያጠፉ ኃይል መሆኑን አይተነዋል።
የISIS እንቅስቃሴ የሚጀምረው በየትኛውም አገር የውስጥን ችግር መነሻ በማድረግ ነው። የውስጡ ፖለቲካ ሲጦዝ መረጋጋት ሲያቅተው በየአካባቢው ችግር ሲነሳ እነዚህ ሃይሎች ይነሳሉ። ችግሮችም እንዲባባሱ ፖለቲካውስጥ ገብተው የማጦዝ ስራንም በከፍተኛ ይንቀሳቀሳሉ። ለዚህም እንደአስረጅ ብንወስድ ኢራቅ ሳዳም ከወደቀ በኃላ የውስጥ መረጋጋቱ እንዳይመጣ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገው የአሁናን ኢራቅ የሰው ደም እንደ ጎርፍ የሚወርድባት አገር አድርገው ፈጠሯት። ቀጥለውም በሶሪያ በተፈጠረው አለመረጋጋት የኢራቁ አክራሪ እስላሙ ወደ ሶሪያ በመዝለቅ የኢራቅ እና የሶሪያ እስላማዊ እንቅስቃሴ ብሎ ሶሪያንም የደም ጎርፍ እንድታስተናግድ አድርገዋታል። የመንም እንደዚሁ እንቅስቃሴ አለ። ሊቢያም ከጋዳፊ ውድቀት በኃላ መረጋጋት ባለመቻሏ በዚህ አጋጣሚ እነዚህ አይሎች አንድ ትልቅ ከተማን በመቆጣጠር በከተማዋ የሚኖሩትን ክርስቲያኖችን ባህር እስከሚቀላ ድረስ ደማቸውን አፍሰው አረመኔአዊ ተግባራቸውን ለአለም ህዝብ አሳይተዋል። እንግዲህ ልብ በሉ በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ እንዳለ። እንቅስቃሴአቸው በሙሉ የአገር የፖለቲካ ሰላም እንዲናጋ በማድረግ በዚህ መሃል የራሳቸውን ስር በፍጥነት መትከልና ህዝብን መፍጀት ነው።
በአለማችን ላይ የISIS ደጋፊ ቁጥር ከፍተኛ የሆኑት አገራት ሳውዲአረቢያ 28.8% ኢራቅ 15.7% ግብጽ 7.8% ሶሪያ 7.0% አፍጋኒስታን 7.0% ሊቢያ 5.4% ሲሆኑ ከግብጽ እና ከሳውዲ አረብያ ውጪ የተቀሩት አገራት ላይ በሰፊው እንቅስቃሴውን ጀምሯል። ግብጽ እና ሳውዲአረቢያ ጠንካራ መንግስት ስላላቸው ነው እንጂ እነዚህ አገር ውስጥ አለመረጋጋት ከመጣ እና የውስጥ ሰላም ከተናጋ አቅጣጫቸው ወደት እንደሚያመራ ግልጽ ነው።
ሱኒን(Sunni) ISISNን የሚያራምዱ ሙስሊም በአገራችን የሉም ለማለት አይቻልም። የሉም የሚል ካለ ይህ ሰው ከእውነት የራቀ አልያም ነገሮችን መደባበስ የሚፈልግ ከእውነት የራቀ ሰው መሆን አለበት። ባገራችን የተደረጉትን እንቅስቃሴ በጥቂቱ እንመልከት…. ጅማ ላይ ሌሊት ማህሌት ቆመው ምስጋና የሚያቀርቡትን ካህናትን እና ምዕመናንን በቤተ መቅደስ ውስጥ ማረዳቸው። በአርሲ ውስጥ የክርስቲያን ቤቶችን እና የህህል ጎተራቸውን እና ክምር ሰብላቸውን ማቃጠላቸው። በስልጤ ውስጥ የክርስቲያን እና የውሻ ድምጽ መስማት አንፈልግም ብለው ቤተክርስቲያንን ማቃጠላቸው እና አሁንም በውስጣችን ቁጭ ብለው አጋጣሚዎችን የሚጠብቁ እንዳሉ ልናውቅ ይገባናል። የጅማን ክርስቲያኖች በታረዱ ሰሞን የነበረው የቃላት ጦርነት ምን ያህል እንደነበረ ልንረሳው አይገባም። እንደውም አጠገባችን ካለ ክርስቲያን አፍጋኒስታን ያለ ሙስሊም ለኛ ቅርብ ነው ብለው አፍጋኒስታኑን አብሮ ከኖረው ከአገሩ ህዝብ አስበልጠው እንደሚወዱ የተናገሩበትም ግዜ ነበረ። ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ብረት ያነሱ ሙስሊሞች እናዳሉና የትጥቅ ትግልም እንደጀመሩ ልናውቅ ይገባል። ይህንን እውነት ማናችንም ልንሸፍነው አይገባም።መሸፈን ዋጋ የለውም ወደፊት ገጦ የሚመጣ ሃቅ ስለሆነ። ዋናው ነገር ነገርን በእንጭጩ የሚለውን አባባል መጠቀሙ ነው አዋጩ።
በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ወያኔ እየሰራ ያለውን የዘቀጠ እና የTPLF የበላይነት እንቅስቃሴ ህዝቡ አልቀበልም በማለቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ወያኔ ክስልጣን የማስወገድ ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ በጎላ መልኩ ተቃውሞዎች እየበረቱ እና እየጠነከሩ ነው። በዚህም ምክንያት ለህዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ንቀት ገሃድ እያወጡት ነው። ሰሞኑን በOMN ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ በለቀቀው ዜና አቦይ ጸሃዬ ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን በውስጣቸው የነበረውን ንቀት እና ጥላቻ አውጥተውት መስማታችን ቀድሞ ወያኔን አንቅሮ የተፋው ህዝብ ትግሉን እንዲያጠናክር ሃይል ሆኖታል።
ወያኔን ከስልጣን የማስወገዱ ጉዳይ ከሁሉም አቅጣጫ በተቀጣጠለ መልኩ እየተካሄደ ነው። እዚህ ጋር ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ መወሰድ ያለበት ነገር ስለ ወያኔ መውደቅ ወይም መጥፋት አይደለም የሚያሳስበው። በወያኔ መደምሰስ ጉዳይ እራሳቸው ወያኔዎችን ሊያሳስባቸው ይገባል።ምክንያቱም የሰሩት ግፍ የትም ቢሄዱ ሊደበቁ ስለሚያስችላቸው። ሊያሳስበን እና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ወያኔ የማጥፋት ስራ በሚሰራበት ግዜ በመሃል አቅጣጫውን ሊያስቱ የሚችሉት የISIS ግሩፕ እንዳይገቡ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ሊያስቡበት እና ኃላፊነትን እንዳለባቸው ሊያውቁት ይገባል። የውሻ እና የክርስቲያን ድምጽ መስማት የማይፈልገው አክራሪው ቡድን ለክርስቲያኑ፣ ለሺአው ሙስሊም፣ ለዋቄ ፈናው፣ ለይሁዲው፣ እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት የተነሳ ኃይል ሰለሆነ በህብረት እንቅስቃሴውን በነቃ ሁኔታ ልንጠብቀ ይገባል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሸፋፈን አደጋውን ልናስቆመው አንችልም።
ከላይ ካርታው ላይ እንዳየነው ኢትዮጵያ እስላም እስቴት የሚለው ላይ የተካተተች አገር በመሆኗ ለአደጋው ከታለሙላት አገር ተርታ ተሰልፋለች ማለት ነው። ISIS በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ብዙ አገራትን በመያዝ እና በመንቀሳቀስ የንጹኃኑን ደም በከንቱ በአረመኔአዊ እና ሴጣናዊ ሁኔታ እያፈሰሰ ይገኛል። ይህ ቡድን የአገራትን የፖለቲካ አለመረጋጋትን አይቶ ሰርጎ በመግባት ለከፍተኛ ብጥብጥ እና ጥፋት የሚዳርግ ስለሆነ ለውጡ በሚመጣበት ሰአት የፖለቲካ ታጋዮች ግምት ውስጥ በማስገባት የISISን እንቅስቃሴ በአገራችን ሰርጎ እንዳይገባ በጥንቃቄ መራመድ አለብን።
ከ-ከተማ ዋቅጅራ 25.02.2015 Email- waqjirak@yahoo.com

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39225#sthash.ttVujhxr.dpuf

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.