በነገው እለት May 17 ከአለም ሃብታም የምትባለው ትንሿ ሃገር ኖርዌይ የህገ መንግስት ቀኗን ታከብራለች። የኖርዌይ ህገመንግስት የጸደቀውና ለኖርዌይ ቅኝ ተገዢ ህዝብ በስራ ላይ የዋለው May 17, 1814 ቢሆንም አንድ ጥይት ሳይተኮስ ታላቅ ወንድሜ ከምትላች ከስዊዲን ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችው ግን እ.ኤ.አ 1905 ነው። በ 1905 ምንም ብሄራዊ ስሜት የሚፈጥር ግጭት ባለመፈጠሩ ዛሬ እንደ ነጻነት ቀን እንኳን አይከበርም። ከስዊዲን በፊት ኖርዌይ ለ500 አመታት በውጭ ንጉሶች ስትመራ ነበር። ኖርዌይ ከስዊዲን ነፃ የወጣችው በሪፈረንደም ሆኖ ከዴንማርክ የተሾመላትን ተወዳጁ ንጉስ ሆኩን ሰባተኛን Haakon VII, ተቀብላ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን በቅታለች። የዛሬው በጣም ተወዳጁ ንጉስ ኖርዌይ በመወለድ 3ኛ ሲሆን አያቶቹ ግን የዴንማክ ንጉስ ትውልድ ናቸው።
እኛና ኖርዌይ .....
ኖርዌይ በጣም ድሃ ሃገር ስለነበረች በሁለቱ የአለም ጦርነቶች መሃከል (interwar period 1915-1939) በተለይ በ1922 በዋና ከተማዋ ኦስሎ በፓርላማው መግቢያ በር ፊት ለፊት በረሃብ የሚሞቱ ሰዎች ነበሩ። እ.ኤ.አ እስከ 1955 ድረስ ምግብ በራሽን ካርድ በቀበሌ ይሰጥ ነበር። ስኳር ቅንጦት ነበር። ኖርዌይ ከአውሮፓ ነገሥታት የ500 አመታት ቅኝ ግዛት በ1905 ነፃ በወጣች ጊዜ እኛ ነፃ ሃገር ነበርን። እነርሱ ነፃ የወጡት እኛ ነፃ ሆነን በምኒሊክ መሪነት ጣሊያንን ከኢትዮጵያ ከተባረረ ከ9 አመታት በኋላ ነው።
በ9 April 1940 አዶልፍ ሂትለር ኖርዌይን ወረረ። ከ20 000 በላይ የሚሆኑ ዜጎቻቸውን ገደለባቸው ሃገሪቷን በእሳት አቀጣጠላት። በ1945 ሂትለር በራሺያዎች ከተሸነፈ በኋላ League of Nations ፈርሶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (United Nations) ሲቋቋም ኢትዮጵያ መስራች ሃገር ነበረች። February 1946 የመጀመሪያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የኖርዌዩ ተወላጅ Trygve Lie ነበር።
የሃይለ ስላሴ ብልህነት ...
በ1952 የተባበሩት መንግስታት ኤርትራ ከጣሊያን ነፃ ወጥታ ስለነበር እንዴት መተዳደር እንዳለባት ውይይት ሲካሄድ አፄ ሃይለስላሴ በአዶልፍ ሂትለር ለፈራረሰችው በችጋርና ጦርነት ለተጎዳችው ኖርዌይ ያልተጠበቀ የገንዘብ እርዳታ ያጎርፉ ጀመር። አፄ ሃይለስላሴ ይህን ያደረጉት ኤርትራን ከተባበሩ መንግስታት በአደራ ለመረከብ ስለፈለጉ ነበር። በወቅቱ ብቸኛዋ ከቅኝ ገዢዎች ነፃ የአፍሪካ ሃገርና የተባበሩት መንግስታት አባል ሃገር ኢትዮጽያ ለአንዲት ድሃ የነጮች ሃገር የምትሰጠው መጽዕዋት አስጋራሚ ሆኖባቸው ነበር። ለኖርዌይ እርዳታ እየሰጡ በጎን ደግሞ ንጉሱ የኖርዌይ ተወላጁ የተባብሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊን Trygve Lieን ጠበቅ አድርገው በመያዛቸው (lobby) ኖርዌይ በተባበሩት መንግስታት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴረሽን እንድትተዳደር በሚለው ውሳኔ ላይ ጥብቅና እዲቆሙ አደረጓቸው። በዋና ፀሃፊው ምርቃት ኤርትራ ለነጮች በድጋሚ በአደራነት ከምትሰጥ ከኢትዮጵያ ጋር በፈዴራል መንግስቷ ራሷን እንድታስተዳደር አደረጉ።
አሳፋሪው ትውልድ ...
ዛሬ ከወንድምና እህቶቻችን ጋር ያለያዩን ይባስ ብለው የኤርትራን ህዝብ እንደ ጠላት በ100 ሺህ ወታደር ድንበር በማስጠበቅ "ልማታዊ መንግስት" የሚሉትን ታሪክንና ብሄራዊ ጥቅምን የማያውቁ የክዱ መሆናቸውን እያየን ነው። ይባስ ብሎ 21ኛው ክፍለ ዘመን ይሄንን አገዛዝ እንደ መንግስት የሚደግፉ ደንቆሮዎችን ለማየት አብቅቶናል።
○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○ ○
ከየምታዩት ክሊፕ በ1954 ንጉሱ ለኖርዌይ ከሰጡትን የመቶ 150 000 ክሮነር እርዳታ አንዱን የሚያሳይ ሲሆን በ1955 ደግሞ የተባበሩት መንግስታት የኤርትራን የማስተዳደር ጉዳይ ለኢትዮጵያ መሰጠቱን ያሳያል።
Source: Ethiopia at Bay: A Personal Account of the Haile Selassie Years
By John H. Spencer
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.