Friday, July 10, 2015

ስለ እውነት፣ ስለፍትሕ እናት ኢትዮጵያ አሁንም ትጮኻለች!!

July 9, 2015
በዲ/ን ተረፈ ወርቁ
Few bloggers and journalists freed in Ethiopia
የኢሕአዴግ መንግሥት አሸባሪዎች ናቸው፣ በዜጎች ክቡር ደም የቆመውን ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ የተደራጁ ናቸው፣ በውጭ አገር ካሉ ሰላማችን፣ ዕድገታችን በቅናት ብግን እያደረጋቸው ካሉና አገራችንን ለማተራመስ ቆርጠው ከተነሡ ከፈረደበት ሻቢያ፣ ሽብርተኛ ድርጅቶችና ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር አብረው ይሠራሉ፣ የአገርንና የሕዝብን ደኅንነትና ፀጥታ አደጋ ላይ ጥለዋል፣ በኢትዮጵያ ሰላምና በሕዝቦቿ ልዑላዊነትም ላይ በመደራደር ይቅር የማይባል ክህደት ፈጽመዋል ያላቸውን የዞን ፱ ጦማርያንና ሌሎች ጋዜጠኞችን ከአንድ ዓመት በላይ ፍርድ ቤት ሲያመላልሳቸው ቆይቷል፡፡
ማብቂያ የሌለው በሚመስል ቀጠሮ በነጋ ጠባ ወደ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩ ወገኖቻችንም ያን አምኖ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት እንኳን የሚከብድ ክስና የወንጀል ማስረጃ አቅርቤባችኋለኹ ያላቸውንና ፍርዳቸውን ከእውነት፣ ከፍትሕ አምላክ ሲጠብቁ የነበሩ ወገኖቻችንን መንግሥት በነጻ ተሰናብታችኋል ሲል የመለቀቃቸውን ዜና እንደ ዋዛ አበሰረን፡፡ መንግሥት እነዚህን ወገኖቻችንን በነጻ ያሰናበተበትን ምክንያቱን አልነገረንም፡፡ ቅሉ እንዲነግረንም የምንጠብቀው ሰዎችም ያለን አይመስለኝም፡፡
ኢሕአዴግ እንደቀደመው ጊዜም መንግሥት መሐሪ ነውና በአገርና በሕዝብ ላይ ላደረሳችሁት ክህደትና ወንጀል ይቅርታ ጠይቁና ነጻ ውጡ የሚለውን የተለመደች ብልጣብልጥነቱንም አልተጠቀመም፡፡ በዚህ ሰበብም ሽማግሌዎችንም እነዚህን ሰዎች እባካችሁ ማልዱኝ፣ አማልዱኝ በሚል አላደከመም፡፡ እንደው ብቻ ደርሶ ነጻ እኮ ናችሁ ሲል በአንድ ሺ አንድ መረጃና ሰነድ ወንጀላቸውን፣ ኃጢአታቸውን ሰማይ የሰቀለውን እነዚህን ሰዎች በአንዲት ማዘዣ ቃል ብቻ ነጻ ናችሁ ሲል አሰናበታቸው፡፡
መቼም ዘንድሮ ኢሕአዴግ እፍረትና ይሉኝታ ይሉትን ባህላችንን አሸቀንጥሮ የጣለ ነው የሚመስለው፡፡ ምርጫውን መቶ በመቶ አሸንፌያለኹ ብሎ ባወጀ መሬት አንቀጥቅጥ ድሉ ማግሥት ደግሞ እነዚህን በአገር ልዑላዊነት በሕዝብ ጥቅም ላይ የተደራደሩ ሰዎችን ማን ወንድ ነው ፍርዳቸውን ሳያገኙ፣ የእጃቸውን ሳይከፈሉ ከእጄ የሚያወጣቸው ሲል እንዳልነበር፣ እንዳልተገዘተ ኹላ ‹‹ሾላ በድፍኑ›› እንዲሉ አበው ከአንድ ዓመት በላይ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን እነዚህን ወገኖች በነጻ አሰናብቼቸዋለኹ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ ሲል ዜናውን፣ የምስራቹን አበሰረን፡፡
እኛም መንግሥትን እንደው እነዚህን ወገኖች ስታስርም ሆነ ስትፈታ ምክንያትህ ምንድን ነበር በሚል ጥያቄ ራሳችንን ስናሞኝ አንገኝም፡፡ መንግሥት ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም እነዚህ ወገኖቻችን በነጻ በመለቀቃቸው የሁላችንም ደስታ፣ ሐሤትና እረፍት ነው፡፡ ሌሎችም ያለ ፍርድ የታሰሩ፣ ፍትሕን የተነፈጉ ወገኖቻችንም ነጻ ይወጡ ዘንድም ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ከዚህ ግማሽ ደስታ ባሻገር ግን አሁንም ሌላ ጥያቄ፣ ሌላ ብሶት፣ ሌላ ቁጭት አሁንም በብዙዎች ልብ ውስጥ ተከድኖ አለ፡፡
‹‹በፍርድ ከኼደች በቅሎዬ፣ ያለ ፍርድ የኼደች ቆሎዬ›› እንዲሉ አበው እንዲህ በእናት ኢትዮጵያ ምድር ስለተረገጠው እውነት፣ ስለዘመመው ፍትሕ፣ ስለተዛነፈው ፍርድ የብዙዎች ቁጭት፣ ብሶትና ምሬት ከትናንትና ይልቅ ዛሬ ተባብሶ ይቀጥላል፡፡ እናም መንግሥት ሆይ ‹‹የፍትሕ ያለ፣ የእውነት ያለኽ፣ የፍርድ ያለኽ!›› የሚለው የሕዝብ፣ የኢትዮጵያ እናቶች እንባና ጩኸት ሰማይን እንዳናወጠ፣ ምድሪቱን እንዳጨቀየ ወደ ሰማይ መፍሰሱን ቀጥሏል፡፡ ግና መንግሥት አሁንም ድረስ በዚሁ ኹሉ በሕዝብ ብሶት፣ እዬዬና እሮሮ ውስጥ የሚሰማ ጆሮን፣ የሚያይ ዓይንን የታደለ አይመስልም፡፡
ግና የራሄሎች እንባ ወደ ጸባኦት አምላክ ጆሮ በደረሰ ጊዜ፣ ያ የፍርድ ጽዋ የሞላ ጊዜ ግን… ወየው ፍርድን ለሚያጣምሙ፣ ፍትሕን ለሚያዛቡ የእውነት ጠላቶች!! እነዚህ ልባቸውን እንደ ግብጻዊው ፈርኦን ልብ ፈጽመው ያደነደኑ፣ በኢትዮጵያ አምላክ ላይ ልባቸውን ያኮሩ፣ በሕዝባቸው ላይ የጭቆናን ቀንበር ያጠበቁ፣ ፍርድንና ፍትሕን ያዛቡ፣ መበለቲቱንና ባልቴቶችን ያስለቀሱ፣ የሽማግሌዎችንም ፊት ያላፈሩ ዓመፀኞች፣ የአምላክን ወሰን የሌለውን ትዕግሥቱንና ምሕረቱን እንደ ከንቱ ነገር የቆጠሩና ያጣጣሉ አምባገነኖች ኹሉ ራሳቸውን ለመቅሠፍት፣ ለውርደት ሞት የጠበቁ፣ አጥፊው የሞት መልአክ በቤታቸው ደጃፍ አድብቶ፣ ቆሞ ያለ መሆኑን ያውቁት ዘንድ በእርግጥም የግድ ይላቸዋል፡፡

Thursday, July 9, 2015

የ ‹‹ይቅር ባይ›› መንግስት ‹‹ይቅር የማይባል›› ድርጊት!!

July 9, 2015
አሌክስ አብርሃም
‹‹በመንግስት›› ካባ የተጀቦኑት ግለሰቦች ፈፅሞ ‹‹ይቅር ባይ ›› አይደሉም!! …ይቅር የማይባል ስህተት የህዝብ ልጆች ላይ የሚሰሩ ጭፍን ጥላቻ እና የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው አንባገነኖች እንጅ …አሁንም ‹‹ መንግስት ›› በጭፍን ጥላቻ ያሰራቸውን በርካታ ኢትዮጲያዊያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ … የማንንም አገር መሪ መምጣት ሳይጠብቅ ሊፈታ ይገባል ! እኛ ኢትዮጲያዊያን አባቶቻችን በከፈሉልን ንፁህ መስዋእትነት ከነድህነታችን ተከባብረንና ተፋቅረን የምንኖር የተከበርን ህዝቦች እንጅ …መንግስት ለብድርና እርዳታ ጥማቱ አበዳሪ በመጣ ቁጥር እንደዘንባባ እየዘነጠፈ ሃያላን መሪዎች እግር ስር የሚያነጥፈን ርካሽ ህዝቦች አይደለንም !!Ethiopian arrested zone 9 bloggers
እዝኛለሁ … ከእስሩ የበለጠ የተፈቱበት መንገድ አሳዝኖኛል …መንግስት ለዜጎች ያለውን እጅግ የወረደ ንቀትና ‹‹ማን አለብኝነት›› የሚያሳይ ድርጊት ነው … ኢትዮጲያዊያን ባልቴቶች በምርኩዝ ፍርድ ቤት ድረስ ሂደው እያለቀሱ ሲለምኑት በወታደር እያስገፈተረ ያስባረረ መንግስት …ህዝቦች በአደባባይ ወንድማ እህቶቻችንን ፍታልን እያልን ስንለምን ከነደጋፊወቹ ያሻውን ፀያፍ ስም እየለጠፈ ሲሳለቅና ሲያሽጓጥጥ የኖረ መንግስት… አሁን የባርነት ስነልቦናው በፈጠረው መሽቆጥቆጥ ‹‹ወደቤታችሁ ሂዱ›› ብሎ ከየቤታቸው አፍኖ የወሰዳቸውን ዜጎች መፍታቱ … ብሔራዊ ውርደት ነው !! እንዲህ አይነት ‹‹ስፈልግ አስራችኋለሁ ስፈልግ እፈታችኋለሁ ›› መልእክት ያዘለ ‹ነፃነት› ከጠባብ እስር ቤት ወደሰፊ እስር ቤት ሰዎችን ማዘዋወር እንጅ ፍትህ ያመጣው ነፃነት አይሆንም …አይደለምም!
ህገ መንግስቱን ባሻው ሰአት የሚጥስ ምንም ዋስትና ሊሰጥ የማይችል መንግስት እንዳለን ማሳያም ነው ! መንግስት እስካሁንም ባሰራቸው ጋዜጠኞች ጦማሪያንና ሌሎችም ንፁሃን ላይ ከመረረ የግል ጥላቻ ውጭ ምንም ምክንያት እንደሌለው የሚያሳይ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት !! ህዝብን የማያከብር በህዝብ ስም እርዳታና ብድር ለመለመን የሚሽቆጠቆጥ መንግስት ለአገርም ለዜጎችም ዋስትና አይሆንም !!
ለማንኛውም አንድ አመት ሙሉ ልጆቻችሁ በግፍ ‹‹ለታገቱባችሁ›› ወላጆች… በአሜሪካ መሪ ስም ከእገታ ነፃ ወጥተዋልና እንኳን ደስ ያላችሁ!! በእስር ላይ ያላችሁም ወገኖቻችን ከኢትዮጲያ ህዝብ በላይ የሚከበር የአገር መሪ እስከሚጎበኘን ፅናቱን ይስጣችሁ ! ኢትዮጲያዊነት ዋጋው ምንም እንዲሆን ለሚታትረው መንግስታችንም በክብር የተጠየቀውን በውርደት ስለፈፀመ ‹‹መቶ ፐርሰንት የውርደት ምልክታችን ሁኖ ይኖራል››
Alex Abreham በነገራችን – ላይ

Friday, July 3, 2015

Ethiopia: Respect court rulings and release opposition members


Ethiopia: Respect court rulings and release opposition members

















Ethiopian authorities must stop harassing two men and two women linked to the opposition Semayawi (Blue) Party, and immediately release them from detention, Amnesty International said as they were expected to face fresh charges in court today in the capital Addis Ababa.

 “On five separate occasions over the course of the last 10 days, three different courts have ordered the police to release these four people,” said Michelle Kagari, Deputy Regional Director for East Africa, the Horn and Great Lakes. “Their continued detention is blatantly unlawful and in clear violation of their rights to liberty and a fair trial.”

Read More at Amnesty