በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።
በብሔራዊ የደህንነት መዋቅር ውስጥ መሰላቸት፣ አለመተማመን፣ ጫና እንዲሁም ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ የሚደረግባቸው ክትትል ጤና የነሳቸው ተበራክተዋል። በተለይም የህወሃት ያልተማሩ ነባር /አንጋፋ ባለሥልጣናት/ ታጋዮች የሚሰጡት ቅጥ ያጣ መመሪያና ወሬ ለቃሚዎቸ ከየመንደሩ ለብር እያሉ የሚያቀረቡት የሰላማዊሰዎችን ህይወት የሚያናጋ መርጃ ዕረፍት እንደነሳቸው የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።
“በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ተቀምጠው የሚያገለገሉ ባብዛኛው ደስተኛ አለመሆናቸው በገሃድ ስለሚታወቅና የመውጫው ቀዳዳ ስለተዘጋ” በሁሉም አቅጣጫ መሹለኪያ ፈላጊውና በሰላም መኖር የሚመኘው ክፍል እንደሚያይል ያመለከቱተ ዜና አቀባዮች “የኢህአዴግ ዙሪያ መለሱ ቆሽሾዋል፤ የእርስ በርስ መተማመኑም ኮስሷል” ብለዋል። በማያያዝም በርካታ አመራሮች አገር ለቅቀው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (ሚያዚያ 2፤2006ዓም/April 10,2014) “ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው፤ “አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል”” በሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለአንባቢያን እንዲረዳ ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ።
ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።
