ከ1940 ዎቹ ዓመታት ጀምሮ የመጣው ትውልድ አሁን ኢትዮጵያ ለምትገኝበት አደገኛ ሁኔታ መከሰት የዳረገ ትውልድ እንደሆነ ሊክድ የሚችል ያለ አይመስለኝም ። በተለይም በአገር ቤትም ሆነ
በውጭ የትምህርት እድል ያጋጠመው ምሁሩ ክፍል በዚህ ጉዳይ ትልቁን ድርሻ ሊሸከም ይገባዋል።የችግሮቹ የእድገት ሁኔታ እንደሰደድ እሳት እየፈጠነና ሥርዓት አልበኝነት ሥር እየተሰደደ ባለበት
በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ምሁሩ ከተኛበት ባንኖ መነሳትና የአገሩን ችግር መፍትሄ መሻት ያልቻለበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ምሁሩን የአገር ዕዳ ተሸካሚና ተጠያቂ ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያቱም
ዝምብሎ ከሜዳ ላይ የተነሳ ነገር አይደለም ጌዴታና ኃላፊነት ስለአለበትና ያስተማረችው አገር ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ ነው ። መንግሥት ከነጋዴው፤ ከአርሶ አደሩ ከሌላውም የሕረተሰብ
ክፍል የመሬት መጠቀሚያ ፤ የትምህርት ፤ የጤና ፤የአገልግሎት ወዘተ…በሚሰበስበው ግብር የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይማር ያስተማረው ነው። ይህ ህዝብ ደግሞ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ
ከሚገባው በላይ ያውቃል ወይም ለማወቅና ችግሩን ተጋፍጦ መፍትሄውን ለማምጣት ባለመፈለጉ ራሱን ደብቆ (አድፍጦ) የራሱን የተመቻቸና የደላ ኑሮ እየመራ መኖርን መርጧል ማለት ነው። ይህ
ግን የትም የሚያደርስ አይደለም። ጥግ ይዞ ቆይቶ ህዝብ በሚወስደው እርምጃና ተጋድሎ ሥርዓቱ ሲወድቅ ሥልጣን ለመያዝ ራስን አርበኛ አድርጎ መቅረብ የተለመደና አፍላው ያለፈበት ፋሽን
ነው። በሀገር ሀብት ተምሮና ሰልጥኖ የባዕድ አገር መገንባት በባዕድ አገር ከማገልገል ለወገንና ለአገር መቆም ለትውልዱና ለሕዝቡ መመኪያ መሆን ኩራት ነው። የዜግነትንና የምሁራዊነትን ብቃትና ግዴታ
መወጣት የሚገባው እንደ አሁኑ አገር በአገር በቀል ጠላቶች ስትሞት ታሪኳ ሲጠፋ ፤ትውልድ ሲመክን፤ የሀገር ሀብት ሲመዘበር ወገን እንደ ጎርፍ ውሃ ወደ ስደት ሲጎርፍና በየበርሃው የአውሬ ቀለብ
ሆኖ መዳረሻው ሲጠፋ በማዳን ነው ታሪክ ሠርቶ ማለፍ ወይም ወንበር መመልከቱ አግባብ ሊኖረው የሚችለው ። በእርግጥ ለኢትዮጵያችን ለውጥ ለማምጣት እንደ ሻማ የቀለጡ ምሁራን አልነብሩም
ማለት አይደለም አሁንም የግል ኑሯቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ምክንያት ሳያደርጉ ይህን የጐሰኞችና የጠባቦች ሥርዓት ለማስወገድ የሚታገሉ የሉም ማለት አይደለም። ከቁጥሩ አንጻርና መወገን ወይም
ወደ ጋራ የሚያታግል መድረክ ለመምጣ ካለመቻሉ አይን ሲመዘን ግን አብዛኛው ምሁር የአገርና የሕዝብ ሞት ሞቴ አይደለም ፤ ችግሩም የኔ ችግሬ አይደለም ብሎ እንደሚገኝ ለመግለጽ እንጅ ። ለምን
ተነካን የሚሉ ምሁራን ሊኖሩ እንደሚችሉ ና ጣታቸውን ሊቀስሩብኝ እንደሚችሉ ግምት ውስጥ አስገብቸ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘውዳዊ አገዛዝን መዛል በመመልከት የቀጣዩ የሥርዓቱ ሰው ሆኖ
ለመገኘት እንደ አሸን የፈሉት የየካቲቶቹ ድርጅቶች የተመሠረቱት ምሁር ነኝ በሚለው ክፍል እንጅ በሰርቶ አደሩና በአርሶ አደሩ እንደአልነበር ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው። እንግዲህ የዚያ
ጊዜ ጦስ ነው ዛሬ ኢትዮጵያን ለዚህ ዳርጓት የምናገኘው። እውነቱን ለመናገርና ለ40 ዓመታት ያህል የዘለቀውን ጦርነት አዘልና አፈና የበዛበት የአገራችን ችግር መንስኤና መፍትሄውን ለማስቀመጥ
አለመታገል ሁኔታው ተባብሶ ህዝብ ይለቅ አገርም ትጥፋ ብሎ መወሰን እንደማለት ሊቆጠር ይገባዋል የአሁኑ ዝምታ። በተለይም ደግሞ መታሰብና መነሻችን ሊሆን የሚገባው በኃይለሥላሴ ፤በደርግ ፤
አሁን ደግሞ በአገር ውስጥ ጣሊያኖች ላይ የሚነሱ ድርጅቶች በምን እንደወደቁና ትግላቸው ሳይሰምር እንደቀረና ጠባብና የመገንጠል አላማ ይዘው የተነሱ እንዴት ግባቸውን ሊመቱ እንደቻሉ ሰከን ብሎ
ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው። ጀብሃ፤ ሻእብያና ህወሃት ሲጀምሩ ጀምሮ አንድነትን ተፃረውና በወቅቱ የተመሰረቱ ድርጅቶችን በመከፋፈል እንደሆነ ብዙ ሳንሄድ ከኢህአፓ ተገንጥሎ በህወሃት
የተቋቋመው ኢህዴን ለህወሃት እንዴት ነብስ እንደዘራለትና እስከ አሁንም አብሮ በመንገድ መሪነት መጓዙና አገር ማጥፋቱ በግልጽ ይታወቃል። ሕዝብ ዛሬ የድርጅት ቁጥር ሳይሆን የሚፈልገው ታግሎ
የሚያታግለውና የሚመራው ነው የሚፈልገው። ይህን ሀቅ ሊመር ቢችልም እንቀበለውና ወደ አንድነት እንምጣ ብሎ ለመግባባት መጣር ትልቅ ችሎታና አዋቂነት ነው።የውጭ አገር ዜግነት አግኝቶ
ለባእዳን እያገለገሉ መኖር ይቻላል።የማንነታችን መገለጫና መለያችን እምየ ኢትዮጵያን ማጣት ደግሞ የሞት ሞት ይሆናል።ትውልድን ይዞ ገደል መግባት ነው የሚሆነ።ጠላቶቻችን ጥቂቶችና በፍርሃት
የተዋጡ እርስ በርሳቸው እምነት የሌላቸው ከሕዝብ የተነጠሉ ስለሆነ መሣሪያውም በዘረፋ ያካበቱት ሀብትም ከቶም ሊያድናቸ ስለማይችል የሚፈሩትን አንድነት ከገነባን ይወድቃሉ። ይህ ደግሞ ሊመጣ
የሚችለው ምሁሩ ክፍል ያለውን አቅም አቅቦና በጋራ መነሳትና ማነሳሳት ሲችል ነው። ዛሬ እነ ማንዴላን፤ ጋንዲንና ማርቲን ሉተር ኪንግን የምናወድሳቸው በጎ ሥራ ስለ ሠሩ ስለሆነ ኢትዮጵያዊ
ምሁራንም ከመጠላለፍ አደጋ ወጥቶ ኢትዮጵያዊ ወገኑን ሊታደግ መቻል አለበት ያኔ እኛም በበጎ ሥራችሁ እንደነ ማንዴላ እናወድሳችኋለን።
ሀ/ህወሃት ጠባብና ጐጠኛ ድርጅት ነው፦ ጠባብነትን አውግዞ መነሳትና ሥሩን መንቀል ተገቢ ነው።ምሽጉን ደደቢት አድርጎ ለ17ዓመታት ያህል በትግራይ ወደኋላ ደግሞ በበጌምድርና ወሎ ትግራይን
ከኢትዮጵያ ነፃ ለማውጣት ሲንቀሳቀስ የህዝብ ማነሳሻ ( የቅስቀሳ አቅጣጫው ) በአጠቃላይ የድርጅቱ ዓላማ ስትራቴጅውና ታክቲኩ ሻእብያ ካነገበው ዓላማ የተለየ አልነበረም ። ሁለቱም ጠባቦችና
በኢትዮጵያ መንግሥት (በአማራ ገዥ መደብ ) በቅኝ ገዝዎች ሲጨቆኑና ሲመዘበሩ ሲረገጡ ስለኖሩ ነፃነታቸውን ለማግኘት መታገል ዋናው ዓላማቸው አድርገው የተነሱ ነበሩ ። ትግሉ ከደርግወታደራዊ መንግሥት ጋር ቢሆንም ዋናው ኢላማ ግን የነገደ አማራ ዘር ያለውን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማጥፋት ነበር ። ደርግ በአፍሪካ ቀንድ በወታደራዊ አቅሙ ወደር የሌለው እየተባለ
ይነገርለት የነበረ ሲሆን በዚህ ግዙፍ የሠራዊት ኃይል ውስጥ ደግሞ በርካታ ነገደ አማራ የሆኑ ከተራ ወታደርነት እስከ ከፍተኛ ማዕርግ የደረሱ የተሳተፉበት ነበር ። በመሆኑም ከመራሹ ሻእብያና
ከጉዳይ አስፈፃሚው ህወሃት ጋር በሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ከፍተኛ ይሁን ዝቅተኛ ወታደራዊ ውጊያዎችና በተራ ክስተቶች ሁሉ ይህ መከረኛና ምስኪን ነገደ አማራ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጥቃት
ሰለባ ሆኖ 17ዓመታትን አሳልፏል። ወታደራዊ ድል ተፈራራቂ ወይም አንዴ መሸነፍ ሌላ ጊዜ ማሸነፍ የግድ ስለሆነ በምርኮኛነት የተያዙ የአማራ ነገድ አባላት በነዚህ ሁለት ጠባብና ጐጠኛ ድርጅቶች
ወታደራዊ ኃይል እንደተረሸኑ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። በሌሎች አጋጣሚዎችም እነዚህ ጎጠኞች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢ የተገኘ አማራ የጥይት ቀለብ ሆኖ ማለቁን ማንም የሚክደው አይደለም።
በግልፅ አማርኛ(ቋንቋ) ጥሬ ሀቁን እንመርምር ከተባለ አማራው ከኤርትራዊው ወይም ከትግራዊው ነገድ የተሻለ ሕይወት እንዳልነበረው ራሳቸው ትግሬዎቹ ያውቃሉ። የአማራ ገዥ መደብ ተብሎ
የሚጠራ አንድም ነገደ አማራ የሆነ የአማራ ገዥ መደብ ሊጠቅሱ የሚችሉበት ሞራል እንደሌላቸው ከበቂው በላይ ሻእብያና ወያኔ/ህወሃት ግጥም አድርገው ያውቁታል። ኤርትራም ሆነ ትግራይ ኢትዮጵያ
ተብለው ከሚጠሩት የኢትዮጵያ ክፍለ ግዛቶች ውስጥ እንደነበሩናእንደሆኑ ያውቁታል። አማራውን ለይቶ ለመምታትና ነጥሎ የጥቃት ሰለባ ለማድረግ የታሰበበት አጀንዳውም የራሳቸው ሳይሆን የውጭ
ጌቶቻቸው ጣሊያንና እንግሊዝ እንዲሁም ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ የዐረብ ቱጃሮች አጀንዳ እንደሆነ ማንም ሊክደው ወይም ሊደብቀው የሚችል አይሆንም በመሠረቱ ለኤርትራምሆነ ለትግራይ ሕዝብ
የሚበጀውን ሻእብያና ወያኔ/ህወሃት ያስባሉ ወይም ያደርጋሉ ብሎ ማሰብ ቂልነት ከመሆን ባይዘልም መጀመሪያ ባለቤቱ የሆነው ሕዝብእሽ ብሎ እስከተቀበለው ድረስ ሁኔታው አደገኛ መሆኑን
ከመግለጽ ባሻገር ምንም ማድረግ ስለማይቻል ለጎረቤት የሚተርፈውን ጦስ ግን እንዲያስቡበት ማስገንዘብ ተገቢ ይሆናል። ሕዝብ ሊጠቀም የሚችለው ሻእብያ እንደ አደረገው ህወሃትን እንደሚያቃጀው
ትናንሽ መንደሮችን መሥርቶ ለጥቃት የመጋለጥ ትንሽ የሰው ኃይል፤ የደከመ ኢኮኖሚና የመገንጠል የፖለቲካ አባዜ በመከተልና በመተግበር ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ሁኔታውና ሕብረተሰቡ እያራመደ
ያለውን ተጨባጩን ዓለም ማየት የሚያስችል ብቃትና ችሎታ እንዲኖር መጣርና ሰልጥኖ መገኘቱ ነበር። ህወሃት ውስጥ ጎልቶ የሚታየው በሰፈር ዙሪያ መሰባሰብ በጎጥ መደራጀትና ሌሎችን ማግለል
መሰለልና ሁሉንም እኛ ካልባረክነው የተቀደሰ አይደለም። እኛን ከተመቸን ሌላው ገደል ቢገባ ምን አገባን ማለትና የሚፈሩትን ደግሞ ማጥፋት ነው። ተለያይተው የነበሩ አገሮች በጋራ ለመኖር የሚወስዱት
እርምጃ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ኩድኩድ ሃሳብ ይዞ መንከራተት ቀሽምነት ነው።ጠባብነት የደካሞችና የግብዞች የመፍትሄ ሃሳብ ነው።ጠባብነት ሊወገዝና ሊወገድ የሚገባው የበከተ አመለካከት ነው።
በተለይ በኢትዮጵያችን አይሰራም ምክንያቱም ትዕዛዙ የመጣው ከዐረብ ከበርቴዎችና ከምዕራባውያን ኢምፔሪያሊስቶች ስለሆነ ይህን አስተሳሰብ ደግሞ ኢትዮጵያ ድሮ ጀምሮ የታገለችው ሁሌ
የምትታገለው የባዕዳን (የጠላት)ፍላጎት ስለሆነ ሊቆምና ሊወገዝ የሚገባው ስንኩል አስተሳሰብ ነው። አሁን ያለው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሥልጣን፤ የኢኮኖሚ ምንጩ በጥቂት ጠባቦችና ጎሰኞች እጅ ያለ
ወይም የተያዘ ቢሆንም የአገር ጉዳይ ሲነሳ ጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ንብ ተሞ እንደ መብረቅ እያጉረመረመ ጠላትን ድባቅ መምታት ልማዱ ስለሆነ ቱጃሮቹ ዐረቦች ፤ ምዕራባውያንና አገር በቀል
ጠላቶቻችን ህወሃት በቃ የሚለው ቃል ትርጉሙ ሊገባቸው መቻል አለበት።
ለ/ህወሃት ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ዴሞክራሲ ድርጅት ነው፦ህወሃትን ፀረ-ሕዝብ ብሎ መፈረጅ ተገቢ ነው።ምክንያቱም ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እነሆ ወደ 40ዓመታት ያህል የዘለቀው ታሪኩ ሕዝብ
በመጨፍጨፍ ሲሆን የአርባ ጉጉ፤ የወተርና የበደኖውን ትተን ሀውዜን ያለቀውን ህዝብ ታሪካዊ ሁኔታ በውል እንመርምረው ከተባለ የፀረ-ሕዝቡ ህወሃት ሴራ ለመሆኑ ብዙም መድከም የሚገባ አይደለም።
ተገፍቷል ጭቆና ያስመረረው ሕዝብ ነውና ነፃ እናውጣው ብሎ የሚታገል ድርጅት ተፈጥሮ ያስከተለውን የድርቅ ችግር ከደርግ ጋር በማሳበብ በደርግ መንግሥት እርዳታ እንዳያገኝ ከቀየው እየኮለኮሉ
ማሰደድና በዚህ ሕዝብ ስም እርዳታ እየሰበሰቡ ፖለቲካዊ ጥንካሬ ለማግኘት ማሰብና ተረጅው ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንደ ቅጠል ሲረግፍ የችግሩ ዋና መንስኤ ሆኖ መገኘት ከፀረ-ሕዝብነትም በላይ
ፋሽስትነት ነው። ህወሃትን ፀረ-ዴሞክራሲ ድርጅት ነው ብሎ መፈረጅ ተገቢ ነው።አንድ ህዝብ የዴሞክራሲ መብቶቹ ሲረጋገጡ ሊያገኛቸው የሚችሉ ብዙ ጥቅሞች አሉ። ሀሳብን በነፃ መግለጽና በጹሑፍ
መተቸት የዴሞክራሲ መብት ነው ።ህወሃት ይህን መብት በኢትዮጵያ ካፈነ 40ዓመታት ሊጠጋው ነው።ከበርሃ ጀምሮ እስከ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት ባስቆጠረው እድሜ ማለት ነው።ሐቀኛውና ወጣቱ
ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ፤ ብርቅየዎቹ ጋዜጠኞች እስክንድር ናጋ፤ርዕዮት ዓለሙ፤ ውብእሸት ታየና ሌሎችም የሕሊና እስረኞች፤ የድምጽሳችን ይሰማ መሪዎች ለእሥራት የተዳረጉት እውነት
በመናገራቸውና ሃሳባቸውን በነፃ በመናገራቸው እንጅ ህወሃት እንደሚለው አሸባሪ ሆነው ተገኝተው አይደለም። ምናልባት እውነት ሲነገረው የሚሸበረው ህወሃት ብዙ የመሰንበቻ መንገዶችን ሊከተል
ይችል ይሆናል። ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ። የዜግነት መብት ተፈጥሮአዊና የዴሞክራሲ ገደብ ሊደረግበት የማይገባ መብት ነው።ማንናውም ዜጋ በተወለደበት ባደገበት አገር ዜግነቱ ተከብሮ
የመኖር ሥራ የማግኘት ሀብት የማፍራት ቤተሰብ የመገንባት ፤በአገሩ ተከብሮ የመኖር መብት በሕግ ሊከበርለት ይገባል።ህወሃት የዜጐቹን መብት የገፈፈ ድርጅት ነው።ህወሃት ግዜጎቹን ለዐረብ ቱጃሮች
የሸጠ፤ ያሰደደ ፤የድርጅት አባል ካልሆናችሁ በማለት የሥራ እድል የነፈገ፤ካልመረጣችሁኝ ብሎ በርዳታ የተገኘን ስንዴና ዘይት የሚከለክል፤ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መኖርን ጐሳን መሰረት አድርጎ የከለከለ፤
ጎሳን ለይቶ ሀብት እንዳይኖራቸውና ትውልዳቸው እንዳይራባ ብሎ በደል የሚፈጽም፤በጥቅማጥቅም ሰውን ለመጥፎ ዓላማ የሚያሰልፍ ፤የዜጎችን የመምረጥና የመመረጥ መብት የገፈፈ የዘቀጠ ድርጅት
ነው።መደራጀት የዴሞክራሲ መብት ነው።ዛሬ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ብለው የተሰለፉ ተቃዋሚ ኃይሎችን እያዋከበ፤ሲያስርና ሲገድል የምናየው ህወሃት የተደራጀን ሕዝብ ስለሚፈራ ነው።
ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ እስካልሆነ ድረስ ህወሃት ፈቅዶ የሚደራጅ ማንም ተቋም ሊኖር አይችልም ምናልባት በራሱ ስር በሚፈልገው መንገድ ያደራጀው ካልሆነ በስተቀር መደራጀት በኢትዮጵያአይቻልም። ይህ ደግሞ ሳይወዱ ወደ ትጥቅ ትግሉ የሚሰድ መንገድን ከፍቷል። ዛሬ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ኃይሎች ሕወሃት በሰላማዊ መንገድ ሥልጣኑን ይለቃል ወይም ያካፍላል ብለው
የሚጠብቁት ውጤቱ ከዚህ በፊት ተንኮላሽተው የስርዓቱ አጋፋሪ እንደሆኑት መሆን ወይም ህወሃትን በትጥቅ ኃይል ለማስወገድ ወደ ጫካ ከመግባት እንደማያልፍ መገመት ይቻላል። ይህ እንዲሆን
የሚያደርገው ምክንያት ህወሃትና ነጭ ለባሾችሁ የያዙትን ሥልጣን ከለቀቁ በሰላም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መኖር እንችላለን ብለው ተስፋ የሌላቸው በመሆናቸው ነው።ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ
የዴሞክራሲ መብት ነው። የነዋሪውን ሰላም እስካላወከና ችግር እስካልተፈጠረ ድረስ ተቃውሞ ማሰማት ብሶትን መግለጽ ከሰው ልጅ መብቶች አንዱ ነው። ይሁንና ህወሃት እነዚህን መብቶች በማፈን
የግዛት ዘመኑን ለማራዘም ተግባሮቹ ይፋ እንዳይወጡበትና እንዳይገለጥ አፈናውን ቀጥሎበታል። የሕዝብን አንደበት ሸብቦ ይዞ መቆየት ማለቂያው የከፋ እየሆነ ተመልክተናል ለዛውም ጠንካራ የአንድነትና
የአገር ሉዓላዊነትን ማዕከላቸው አድርገው በነበሩት የቀዳማዊ ኃይለሥላሤና የደርግ መንግሥት ። የህወሃት አወዳደቅ ከሁሉም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ለማንም የተሰወረ አይደለም ።
ሐ/ህወሃት በደም የሰከረ ድርጅት ነው፦አፈና ግድያ በአፄ ኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ ጊዜ ነበረ። በደርግ ጊዜ የነበረውንና አሁን በህወሃት የተከሰተውን ስናነፃጽር ደርግ እያቅራራና እየፎከረ እንዲሁም
በአደባባይ ሰው ገዳይነቱን እያወጀ በሥልጣኔ ይመጡብኛል ያላቸውን ሁሉንም ይገድል ነበር። የህወሃት የተለየ የሚሆነው በስውርና በአማራው ላይ ብቻ ያነጣጠረ አንድ ነገድ ላይ ያተኮረ ሲሆን ምን ያህል
የአማራ ነገድ ትውልዶች እንዳመከነ ቤት ይቁጠረው ተብሎ የሚታለፍ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ከህዝብ የተነጠለና የበሰበሰ ቢሆንም ለይቶለት መቃብር ውስጥ የገባ ስለአልሆነ አሁንም
ሊቀጥፈው የሚችል ሕይወት እንደሚኖር ስለሚታወቅ አማራው ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ ነው። በተለይም ነገዳቸው አማራ ሆነው ለሆዳቸው የተገዙ አማራዎች ያስከተሉት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ
እስከመቸውም የሚዘነጋ አይደለም ተለይተው እንዲታወቁና ለፍርድ የሚቀርቡበት ሁኔታም እንዲመቻች በማድረጉ ረገድ የታሰበበት አይመስልም አንድ ውጤታማ ሥራ መሰራት አለበት። ህወሃት
ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ምንያህል የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዳለቁ መረጃ ማሰባሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው። የሰው ልጅ ሕይወት እንደ ጐማ ተነፍቶ ተመልሶ የሚያገለግል አይደለም።
አማራ ደግሞ የህወሃት የነፍጥ መለማመጃ አይደልም። አማራ ኢትዮጵያዊ ነው።አማራ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራና የሚመካ በደሙና በአጥንቱ የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነቷን አስከብሮ የኖረና
የሚኖር የሌሎች ኢትዮጵያውያንን መብት ጠብቆና አክብሮ በፍቅርና በመግባባት አንድነትን ገንብቶ የኖረ ሕዝብ ነው አማራ ማለት።
መ/ህወሃት ዘራፊና አዘራፊ የስግብግቦችና ጥርቅም ነው፦አቶ ገብሩ አስራት የትግራይ አስተዳዳሪ በነበረበት ወቅት አለቃ ፀጋየ ምክትል አስተዳዳሪ ነበር።በዚህ ወቅት ከሰሜን ጎንደር ጠለምት ፤ጠገዴና
ወልቃይን ወደ ትግራይ በመከለል ሰፊና ከጎረቤት አገር (ሱዳን) ጋር የምትዋሰን ትግራይን ኒዎርክ ለማስመሰል ቆርጦየተነሳው አለቃ ፀጋየ በወልቃይ ጠገዴና አርማጭሆ አዋሳኝ ግማሹን ወደ አማራ ክልል
የተሰየመውን የጠገዴ ክፍል ከሰሮቃ እስከ ማርዘነብ ድረስ ያለውን ለም መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል በተደጋጋሚ ሰላይ ይልክ ነበር። በወቅቱ ድርጊቱን በጥንቃቄ መከታተልና በምሥጢር መያዝ
ስለነበረብኝ ለማንም አልገለጽኩትም ምክንያቱም ከፈለጉ አዲሱ ለገሰን ወይም በረከትን ጠይቀው መውሰድ እንደሚችሉ አውቅ ነበር። ያ አካባቢ አሁንም የተረጋጋ ሰላም የሌለው መሆኑን እሰማለሁበዚህ
አጋጣሚ ትኩረት ሰጥቼ እንድመለከተው ያደረገኝ ነገር ግን ህወሃቶች ከሚገባው በላይ የመሬት ገፀ በረከት ከነታምራት ላይኔና አዲሱ ለገሰ ሲቸራቸው አገርን ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ከደቡብ እስከ ሰሜን
ጨሌ እንዳጠገበው አጋሰስ ሲጋልቡበት አልጠግብ ብለው ማርዘነብን በተደጋጋሚ ሰላይ እየላኩ መቃኘት ምን ያህል ስግብግቦችና ከራሳቸው ጥቅም ውጭ የማያስቡ ፈሪሐ እግዚአብሔር የጎደላቸው (ጠላየ
-ሰናይ )የሚጋልባቸው ደንቆሮዎች የተሰባሰቡበት ህወሃት የበለጠ ምንም ቢሆን ጠግበው ሊያድሩ የማይችሉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ። አዞ ወሃ ላይ ተኝቶ ጀጀባ ላይ ያለን ጤዛ ይልሳል የሚለውን
የአበው ምሳሌያዊ አባባል ያመለከታል።አንድ ወቅት አዲስ አበባ እያለሁ አንድ ዘመዴ ቤት ሄጀ ኮሎኔል ሐጎስ የሚባል በአንድ ጊዜ እንዴት እንደከበረ ስታጫውተኝ በጥሞና አዳመጥኳት ፦ ግለሰቡየህወሃት የመከላከያ ኃይል ኮሎኔል ነው እናም በኮንትሮ ባንድ (ሕገ-ወጥ) በሆነ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በመያዝና ለመንግሥት ገቢ ማድረግ ሲገባው ወደ ግል
መኖሪያውና በየቅምጦቹ ቤት እያስቀመጠ በደላላ እንደሚሸጥና የብዙ ገንዘብ ባለቤት እንደሆነ፤በላንድክሮዘር እንደሚንቀሳቀስና አጃቢዎችም እንዳሉት ነገረችኝ ።እዚህ ላይ ይህን ጉዳይ መጥቀስ ያስፈለገኝ
ዋናው ምክንያት የህወሃት የመከላከያ ሠራዊ፤ደህንነት፤ፖሊስ፤ካድሬ፤ቅልቡ የአጋዚ ሠራዊት(የፌደራል ፖሊስ የሚሉት) በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እጃቸው ከዘረፋ እንደማይቆጠብ ፤እዚያም አልፎ ዘርፎ
ማዘረፍም የሥርዓቱ መደበኛና የየዕለት ተግባር እንደሆነና ይህም የወገኖቻችን ሀብት እንደሆነ ለመጠቆም ነው። 30 ሰከንድ በማትሞላ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያው የቁርጥ ቀን ልጅ አክቲቪስትና ጋዜጠኛ አበበ
ገላው በተሠነዘረው ቃል ደንግጦ በራስ ምታት ከሞተው ጠቅላይ ሚንስትር ጀምሮ እስከ ተራ የቀበሌ ሠራተኛ ድረስ አገር ስትመዘበር እኛ ምን እያደርግን ነው?
ሠ/ህወሃት አገርና ህዝብን የካደ ድርጅት ነው፦እንደ ገብረመድሕን አርአያ የሕዝብ ልጅነቱን ካስመሰከረው በስተቀር ማንኛቸውም ህወሃት ውስጥ የነበሩ አባላቱም ሆኑ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉ ወይም
ድርጅቱን ጥለው የወጡ ሁላቸውንም በህዝብ ክህደት በተለይም ከጉያው ደብቆ ያሳደጋቸውን የትግራይን ሕዝብ በእጅጉ የካዱ ዛሬም እምነት ሊጣልባቸው የማይገቡ እንደሆኑ ተግባራቸው እየመሰከረ
ይገኛል። የሚዲያ ድህረ- ገጾችን ቢቻል በቀን ሁለት ጊዜ አለዚያም አንድ ጊዜ መመልከት ልማዴ ነው።በአጋጣሚ ስየ አብርሐ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ሥራ እንዳገኘና ወደ ኋላ ላይ
የተሰለፈበትን ድርጅት አስመልክቶ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠውን መልስ ሳነብና የመለስ ዜናዊ ሞት ያሳዘነው መሆኑን ከተናገረ ወዲህ ጊዜ እየገዛ ያለ ድብቅ ጠላት እንደሆነና ሲያዘናጋን የነበረ ሰው ነው ብየስጋቴን እንድጨምር አድርጎኛል።የነ ግደይ ዘርአጽዮንና አረጋዊ በርሄን ቃለ ምልልስም ተከታትየው ነበር የለየለት አይመስልም በተለይም መሬት መቀራመትን በሚመለከት ከወልቃይት ጋር የተነሳውን ጥያቄ
አድበስብሰው ማለፍ መምረጣቸው ተቀድመው ነው እንጅ አሁን ህወሃትን ከሚመሩት የተሻሉ አይደሉም የሚል እንድምታ እንድይዝ አድርጐኛል። የገብሩ አስራት አረና የነአረጋዊ በርሄው ዴምሕት ዓላማና
ተግባርም ግልጽነት ስለሚጐድለው የሚለየው አሁን አገር ከሚያደማው ህወሃት ጋር አለመሰለፋቸው ብቻ ነው የሚሆነው። ከዚህ የተሻለ እንቅስቃሴና ለጋራ የኢትዮጵያ ነፃነት የሚታገሉ ከሆነ ስህተቴን
እወስዳለሁ።ከ30-እስከ 40 ሽህ የሚደርስ ሠራዊት እንደሰለጠነና እንደታጠቀም ሰለሰማሁ በማን ላይ ለማነጣጠር የታጠቀ ነው ? የሚለውም መልስ ያላገኘ ስለሆነ ይህን መነሻ አድርጌ ከህወሃት ውጭ
ያሉትን ስተች በአገር ውስጥም መለስ ከንስየ ጋር ከስልጣን ያስፈነጠራቸው የእነ አረጋሽ፤ዓለምሰገድና ተወልደ ድምጽ ከፖለቲካው ዓለም መጥፋቱም ሱባይ ገቡ እንዴ የሚያሰኝ ነው። ሌላው የህወሃት
አመራር አካልና የሥርዓቱ ጠባቂዎች ኢትዮጵያን በመካድ ለመገንጠል የታገሉ ፤ኤርትራን ያስገነጠሉና ኢትዮጵያን የወጉ፤ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረጉ፤የትግራይን ሕዝብ የካዱ፤ልጆቹን የሥልጣን
መወጣጫና መጠቀሚያ ያደረጉየዘመኑ እብድ ውሻዎች ዳግማዊ ሂትለርና ግራዚያኒዎች ጊዜው ደርሶ ሥርዓተ ቀብራቸው እስከሚፈፀም ድረስ ወደ መቃብራቸው የሚያደርሰውን መንገድ እንዲከተሉ
እየታገልናቸው እንቆያለን እንጅ እጅ እግራችን አጣጥፈን እኛ ያጣነውን ሰላም እነሱ በፍጹም ሊኖራቸው አይገባም እንደ አለቆቻቸው አባ ጳውሎስና መለስ ዜናዊ በድንጋጤ እንደባነኑ የሚሄዱበትን ጐዳና
እናሳያቸዋለን። የጣሊያን ጉዳይ አስፈፃሚና የካሃዲ ባንዳ ልጅ ኢትዮጵያን የሚገዛበት ሞራል የለውም።ሕጉም አይፈቅድ። ከእባብ እንቁላል ሊፈለፈል የሚችለው ያው እባብ እንጅ እርግብ ሊሆን
አይችልምና።
ረ/ህወሃት ፀረ እምነትና ፀረ አንድነት -መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል የሌላቸው ስብስብ ነው፦ ህወሃትን እመነት የሌለው ፀረ-አንድነት፤መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል የሌለው ድርጅት መሆኑን ከሊቅ እስከ
ደቂቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ያውቀዋል በተለይ የትግራይና የሰሜኑ የአማራ ሕዝብ። ኢሠፓውያን ኮሚኒስት ለመባል በይፋ ልጆቻቸውን ክርስትና አያስነሱም ቤተክርስቲያን ሄደውም እግዚአብሔርን
አያመልኩም አይጸልዩም ነበር። ህወሃቶችም ይህን እንዳለ ወርሰው ጦርነት ሲጭሩ ቦታ መርጠው ቤተአምልኮ በሚደረግባቸው ገዳማትና ቤተክርስቲያናት አካባቢ እንደነበር ይታወቃል። ይህም የሚያሳየው
ድርጅቱ ፀረ-እምነት መሆኑንና አማኒያንን እንዲጨፈጨፉ የቤተአምልኮ ታሪካዊ ሀብቶችን እንዲቃጠሉ በማድረግ ሕዝብን በደርግ ላይ ለማነሳሳት የሚፈጸም ጭፍን አስተሳሰብ ነበር። ያ ባህሪ አብሮ አድጎ
ዛሬም መስጊዶችን፤ ገዳማትንና አብያተ ቤተክርስትያናትን በስኳር ፋብሪካ ቅብጥርሴ ሰበብ እያወደሙና እያራከሱ ይገኛሉ።«አንድ ወቅት ላይ ተፈራ ዋልዋ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የአድሃሪያን መሸሸጊያ
ነው»ያለው ድንገት ከአፍ አምልጦት ሳይሆን ድርጅቱ ዓላማየ ብሎ የተነሳበት የፀረ-እምነት አባዜው ነበር። በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ትራጀዲ ኢትዮጵያን ሲገጥማት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምንግሥታዊ ትዕዛዝ በሽግግሩ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ዛሬ ደግሞ በዚህ በአሜሪካ የፕሮቴስታንት ፓስተር ነኝ እያለ የሚያላዝነው ታምራት ላይኔ
ፓትሪያርኩን እንዲሰደዱና በምትካቸው ሌላ ካድሬ ፓትሪያርክ በመሾም እነሆ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ህወሃት በጐሳ የከፋፈለው ሕዝብ እምነቱንም ተከፋፍሎ እያመነ ተያይዞታል ይህም የአጋጣሚ ጉዳይ
አይደለም። የድርጅቱ መርህ ነው። ስለዚህ ህወሃት መንፈሳዊ ሞራል ፈጽሞ የለውም ቢባል ማጋነን አይሆንም። አንድ ሊታለፍ የማይገባው እውነታ አለ የዛሬን አያድርገው እንጅ ድሮ የኢትዮጵያ
ቤተክርስቲያን ለጅም ጊዜ ጸንቶ ለቆየው የኢትዮጵያ አንድነት መሠረቱ እንደነበር ታሪክ የሚመሰክረው ጉዳይ ነው።ይህን ለመናድ አባይ ፀሀየ በቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ዘመቻ ቢያካሂድ ሊገርመን አይገባም
ምክንያቱም ብሔራዊ ሞራሉ ከታጠበና የኢትዮጵያ አንድነት ሲያባንነው እንቅልፉን ከሚያውከው ሰው ምን ይጠበቃል? የነበረከትና ተፈራ ዋልዋ አዲሱ ለገሰ መቀላመድም ያችን ከአንበሳዎቹ ተርፋ
የምትወረወርላቸውን የከርሳቸው መሙያ ጥቅማጥቅም ለማግኘት የግድ ማለት የሚገባቸው ነበርና ለሆዱ ካደርና ከአድርባይ የሚጠበቅ ነው። ችግሩ ግን ይህች ሥልጣን ሾልካ የተዛወረች ቀን መታጠፊያው
ሲጠፋ ነው።ኢትዮጵያን የመሰለች አገር ክዶ መቆም ለማጥፋት መታገል ልጆቿን በጭፍጨፋ የማምከን ዘመቻ ትንሽ እንኳን አርቆ ለማሰብ አለመታደል ነው። ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ናት አትጠፋም
እኛ አንድ አልሆን ስንል መግባባትና ተከባብሮ ለመኖር ባለመቻላችን እግዚአብሐር ሻእብያንና ወያኔን ለቅጣት ነው የላካቸው እስከ ማለት የደረሱ ወገኖቼ ወደውም አይደለም። በርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ
እግዚአብሔርን አማኝና አክባሪ ነው እግዚአብሔርም ኢትዮጵያን ክዷት አያውቅም ወደፊትም አይክዳትም የካዷት መሬት ትክዳቸዋለች እግዚአብሔርም ይክዳቸዋል ክደውታልና በአምሳሉ የፈጠረውን
ሕዝብ ገድለዋል አሰድደዋልና።ኢትዮጵያውያንም ጨርሰው አያልቁም ሕብረት ከፈጠሩና በአንድነት አብረው ከቆሙ ጠላታቸውን ማንበርከክ ይችላሉ።
ሰ/ህወሃት አሸባሪና አጭበርባሪ ድርጅት ነው፦ በስልክ ማውራት፤በስካይፕ መነጋገር ፤ኢሜይል መለዋወጥ፤ደብዳቤ መላላክ፤የኢሳትን ቴሌቪዥን ማየት፤መናገር፤መፃፍ፤መደራጀት መሰብሰብ ሁለት ሶስት
ሁኖ መነጋገር፤ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፤ የትቃውሞ ሃሳብን መግለጽ በሙያ መደራጀት፤ ለልማት መደራጀት፤ለእር መሰብሰብ፤ተሰባስቦ ማህበር መዘከር ፀበል መጠጣት፤ ሰንብቴ መጠጣትና በሰንበቴ
መሰባሰብ፤ ለእቁብ መሰብሰብ፤ሠርግ፤ክርስት ፤ሰው ሞቶ ማልቀስም ሆነ በመርዶ ተሰብስቦ ሐዘንተኛን ማፅናናት፤ሰላማዊት ትግል ማካሄድ፤የትጥቅ ትግል ማድረግ፤ በስብሰባ ላይ ንግግር ማድረግ፤ጥያቄ
መጠየቅ….ወዘተ በአሁኑ ሰአት አሸባሪ እያስባሉ የሚያስገድሉ ፤የሚያሳስሩና የሚያሰድዱ ሆነዋል።ተመስገን ደሳለኝ ለእነት የቆመና እውነትን የሚናገር ወጣት ጋዜጠኛ ነው።ፖሊስ፤ደህንነት ስንት ጊዜ
አዋከቡት/ ስንት ጊዜ ፍርድ ቤት አቀረቡት ዳኛውም ቃቢ ህጉም የጠፉ ናቸው።ህወሃት ሲጃጃ ባደረ ቁጥር ተመስገን ምስኪኑ በምን ሂሳብ ነው እንደ በግ የሚጎተተው?መቼ ነው ሕግ ተከብሮ በሕግ አምላክ
የምንለው?አንዱ ዓለም አራጌ እኮ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነው እውነተኛ ተናጋሪ ነው።እኔ የሱን ንግግር ሌት ቀን ብሰማው አልሰለቸውም።እንዴት አንዱዓለም አሸባሪ ተብሎ ይታሰራል ይፈረጃል?ኧረበኢትዮጵያ አምላክ።ርዕዮት ዓለሙ፤እስክንድር ነጋ፤ውብእሸት ታየ እውን አሸባሪዎች ተብለው ነው የታሰሩት እንዴት ብሎ?ለመሆኑ ሕዝቡ ነው የተሸበረው ወይስ ህወሃት?ሕዝቡን እያሸበረ ያለው ህወሃት
ነው፤ገዳዩ ህወሃት፤ዘራፊው ህወሃት፤ደብዳቢው ህወሃት፤ሕግ ያማያክበር ህወሃት ነው።ሲሸበር የሚውል፤ሲሸበር የሚያድር ህወሃት ነው።ምክንያቱም ንፁሃንን በሐሰት አስሮ ደብድቦ አሰቃይቷል ገድሏል
ከደደቢት እስከ አዲስ አበባ ሕዝብ እየፈጀ ነው የዘለቀው።ዜጎችን ከአገር አስድዷል ለሽያጭ አቅርቧል፤የሀገር ሀብት ዘርፏል አዘርፏል፤አገር ሸጧል፤አገር ወደብ አልባ እንድትሆን አድርጓል፤ሕዝብ አፈናቅሏል
በርሃብ ሊፈጅ ታግሏል፤የአገሪቱን ሉዓላዊነት አስደፍሯል።በዚህ ምክንያት ሲሸበር እንዳይውል እንዳያድር የኢትዮጵያ ህዝብ ተማክሮ ሁሉም እንደ ከብት መንጋ እስር ቤት መግባት አለበት
እንዴ?አትሰብሰቡ ከተባለስ ለእያንዳንዱ ሰው መታጎሪያ አንዳንድ እስር ቤት ይገናል ወይ? ለ85ሚሊዮን ህዝብ የሚሆን?ገበዝ እስቲ ይህን ነገር በደንብ አገናዝቡት አይገርምም?እያጭበረበሩ የሚቀበሉት
ገንዘብ የወህኒ ቤት ግንባታ ለማስፋፋትና የጥይት መግዣ እንዲሆን ነበር እንዴ?እኔ ህወሃትን ከፍርሃት ሊያድነው የሚችለው ሁሉም እንደ አለቃቸው ሲገላገሉ ብቻ ነው።ኢትዮጵያዊ አሽባሪ ሆኖ የተገኘ
ህወሃት ነው።ሁሉም እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ በጋራ እንታገል።
በመጨረሻ የምለው ቢኖር ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ከህወሃት ባልተናነሰ መንገድ የኢትዮጵያን ሕዝብ እየጎዳችሁ እንደሆነ ማስገንዘብ እወዳለሁ።ምክንያቱም እኔ የምውለውና የማድረው ከሕዝቡ ጋር
ነው። እናም ኑሮው ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰና አንዲት የክብሪት መጫር ብቻ የቀረው እንደሆነ ደፍሮ መናገር ይቻላል።ከዚህ በፊትም ግፍና በደሉ ሲበዛበት የወሰደውን ርምጃ አንዘነጋም።ዳሩ ግን
በለስ ሳይቀናውና የሚያስብለት መሪ ሳያገኝ ሁልጊዜ ከችግሩ ላይ ቆሞ ይኖራል ዛሬም ቢሆን ያን የሚፈልገውን ቅንና ለሕዝብ አገልጋይ የሆነ መሪና አታጋይ ሊታደል አልቻለም።ህወሃት በከፈተው ቦይ
መጓዙን እየገፋችሁበት ከቀጠለ ህወሃትን መጣል አትችሉም ወንበርም አታገኙም ሲያምራችሁ ይቅር። ልዩነታችሁ የኋላ ቀርነት መገለጫ መሆኑን በመዋጥ አስቸኳይ ግንባር ፈጥራችሁ ለመታገል ብትነሱ ግን
ከሕዝቡ እውቀት፤የማይነጥፍ ድጋፍ፤ገንዘብ በኋላም የምትፈልጉትን ሥልጣን ሊሰጣችሁ ስለሚችል ለሕዝብ ተገዥ የሆነ አመለካከት ይኑራችሁ መልካም እድል ቀሪውን በሚቀጥለው ይዥ እመለሳለሁ።
አንባቢዎቼ ከዚህ በታች በእንግሊዘኛው የተፃፈች ኮቴሽንን በልባችሁ አስቀምጧት
The seven builders of society the seven things that will destroy are
Politics without principle
Pleasure without conscience
Health without work
Knowledge without characteር
Business without morality
Science without humanity
Worship without sacrifices:-have no healthy society and government
(Mahatma Gandhi)
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com – July 11, 2013
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.