በግጭቱ ሁለት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው ሲሞቱ 4 ቆስለዋል።
ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጭት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን» እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋሉ በእርስ በእርስ ግጨቱ የተሳታፊ 4 ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው ላይ ከደረሰው መለስተኛ ጉዳት አገግመው በአሁኑ ሰዓት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በኢትዮጵያውያኑ መሃከል በሚከስት ግጨት በደም የተጨማለቀ በጠራራ ፀሃይ በሳንጃ አንጀቱ የተዘረገፈ ሬሳ መንፉሃ ውስጥ ማየት የተለመደ መሆኑን የሚገልጹ የአይን እማኞች የዛሬ አመት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በቡድን ይከስት የነበረ የዕለት ተዕለት ዘግናኝ ትእይንት ለወራት ጋብ ብሎ ቢቆይም ሰሞኑንን በአዲስ መልክ በማገርሸቱ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ አስደንግጦል ብለዋል።
በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን መሃክል በሚከስት ግጨት ህይወቱ የሚያልፈውን ወገን ለማታደግ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከአመት በፊት የጀመሩት ጥረት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድክመት መስተጓጎሉ የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች በአሁኑ ሰዓት ጭካኔ የተሞላበት የኢትዮጵያውያኑ የእርስ በእርስ ግጨት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንፉሃ በሚኖሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ ይነገራል።
ቀደም ብሎ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሚናገሩ ወገኖች መንፉሃ እንደወትሮው በኑሮ ውድነት ሃገራቸው ውስጥ መኖር ተስኗቸው መሄጃ ባጡ ኢትዮጵያውያን ዳግም መጨናነቋን ይናገራሉ።
እልባት ያላገኘው ይህ የኢትዮጵያኑ የብሄር ግጭት በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ግምት ወስጥ በማስገባት በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን ሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ በመደውል ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ባይሳካም አምባሳደር መሃመድ ሃሰን አፈጉባኤ አብዱላ ገመዳ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት ከመግባታቸው በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸውንና ኤምባሲው በጊዜያዊነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እየተመራ መሆኑን አንድ ስማቸውን መጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የኤምባሲው ሰራተኛ ከስጡኝ መረጃ ማረጋጋጥ ፡ተችሏል።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.