በትላንትናው ዕለት ጥር 13 ቀን 2007 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከሰልፍ በዘለለ ጉባኤ እንደማያካሄድ አስታወቀ፡፡
ከአንድነት ፓርቲ፣ አፈንግጠው የወጡት ሰዎች ፓርቲው ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ እንደጠራ በማስመሰል አባላትን ለማወናበድ እየሞከሩ እንደሚገኙ ምንጮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አንድነት እሁድ ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳልጠራ ገልፀዋል፡፡ በአንድነት ስም ጠቅላላ ጉባኤ የጠሩት ግለሰቦችም ሆን ተብሎ ህዝቡን ውዥንብር ውስጥ ለመክተት ጉባኤ እየጠሩ እንደሚገኝ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ አንድ ላይ በማበር አንድነት ፓርቲን ከምርጫው ለማስወጣት በመስራት ላይ እንደሚገኙ›› የገለፁት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ይህንን ድርጊት በመቃወም ፓርቲው በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ሰልፋ እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ከተሞች ላይ ሰልፉ እንደሚካሄድ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሠረት በደብረማርቆስ ፣ በጂንካ፣ በከምባ ወረዳና በሸዋ ሮቢት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት የተቃውሞ ሰልፉ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረገው ሰልፍ መነሻውን ቀበና ከሚገኘው የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት መድረሻውን ደግሞ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ እንደሚያደርግ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለፍኖተ-ነፃነት አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ በሁለት ሳምንት ውስጥ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ ግፊት ለማሳደር እየሞከረ የሚገኝ ሲሆን ፓርቲው ግን ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ጠቅላላ ጉባኤ እንደማያካሄድ አስታውቋል፡፡

No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.