Tuesday, February 25, 2014

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ጠረፍ ግጭት ተቀሰቀሰ! 71 ኢትዮጵያውያን ሞቱ! “ድረሱልን” እያሉ ነው!

ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ሲሉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ገለጹ::
ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢትዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን ይድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።
አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።

Sunday, February 23, 2014

ዛሬ በባህርዳር የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ፤ ሕዝቡ በባዶ እግሩ በመውጣት በብአዴን/ኢሕአዴግ ላይ ቁጣውን ገለጸ







(ሐበሻየአማራው ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን የሚመሩትን የአማራ ሕዝብ በጸያፍ ቃላት መሳደባቸውን ተከትሎ አንድነትእና መኢአድ ፓርቲዎች በጋራ በባህርዳር ዛሬ በባህርዳር የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በሰላም ተጠናቀቀ። “ህዝቡ ከባዶጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።
10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች ቁጣቸውን ለመግለጽ በወጡበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በአቶ አለምነው የተሰደበውን ለማስታወስናቁጣውንም ለመግለጽ በባዶ እግሩ እንደነበር ከስፍራው መረጃ ያደረሱን የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ገልጸዋል። “ሰልፈኛው ጫማውን አንገቱ ላይበማንጠልጠል በሰላማዊ ሁኔታ በባዶ እግሩ በመሄድ በአዲስ የተቃውሞ ስልት ድምጹን አሰምቷል” ያሉት በስፍራው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎችእንዲህ ያለው የትግል አገላለጽ የሚደነቅና ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል


ባህር ዳር በፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭተው የዋሉ ሲሆን ከከተማዋ አጎራባች አካባቢዎች ጭምር የተሰባሰቡት ልዩ ሃይሎችናየክልሉ ፖሶች በነዋሪው ላይ ውጥረት ለመፍጠርና በሰልፉ እንዳይሳተፍ በከፍተኛ ሁኔታ ቢሞክሩም ሕዝቡ ግን በአቶ አለምነውና በብአዴን ላይቁጣውን ከመግለጽ አላገደውም ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች “ወያኔ ለውድቀቷ አማራን ትሳደባለች” በሚል ቁጣ ካለምንም ፍራቻ አደባባይ ወጥተዋልብለዋል።


በተለይ ኢሕአዴግ በባህር ዳር ከተማ ሕዝቡ ሰልፍ እንዳይወጣ 5ጠርናፊና ተጠርናፊዎች “ሰልፉ ተሰርዟል” የሚል ሃሰተኛ ወሬ በማውራትሕዝቡን ለማደናገር መጣሩን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአንድነት እና የመኢአድ መሪዎች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ በመኪና እና  እግርበመሄድ ሕዝቡን በመቀስቀስ የዛሬውን ሰልፍ ለስኬት አብቅተውታል ሲሉ ዘግበዋል። በተለይም የከተማዋን የባጃጅ ሾፌሮችን በማህበራቸውአማካኝነት ኢሕአዴግ ሰብስቦ ይህን ሰልፍ የምታጅቡ ከሆነ ፈቃዳችሁን ትቀማላችሁ የሚል ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም አቶ አለምነው አማራውንከሰደቡት ስድብ አይበልጥም በሚል ባጃቻቸውን አስቀምጠው ሰልፉን መቀላቀላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል።

https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=MiSXwjwrvxM#t=4

Wednesday, February 19, 2014

ረዳት ፓይለቱ ለኢትዮጵያ ተላልፎ የማይሰጥባቸው 6 ምክንያቶች

ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ተላልፎ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም።
አንደኛ፣ ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን ተግባራዊ የምታደርግ አገር ናት።
ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ጥሰት በአለም የምትታወቅ ናት።
ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ( extradition treaty) የላቸውም::
አራተኛ፣አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝም ብለው አይቀመጡም።
አምስተኛ፣ እንደሚባለው ጭንቀት ኖሮበት ድርጊቱን ከፈጸመም የበለጠ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ያደርገዋል። ምክንያቱም በስደተኝነት ህግ የአእምሮ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ጥገኝነት ለማግኘት ከፍተኛ እድል አላቸውና።
ስድስት፣ የአእምሮ ጭንቀቱ መንስኤ የቅርብና ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ ከሆነ ደግሞ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጉዳዩን ይበልጥ ያከብድለታል ምክንያቱም የአጎቱ ሞት መንስኤ እስካሁን እንቆቅልሽ እንደሆነ አለና። እህቱ የጻፈችውም ደብዳቤ የሃይለመድህንን ችግር ይበልጥ የሚያሳይ ነው ። “ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ፣ ስልኩን እንደጠለፉት እንደሚያስብ፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን እንደማይከፍት እንዲሁም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ ” መጀመሩን መግለጿ፣ የሃይለመድህ መሰረታዊ ችግር የደህንነት ዋስትና ማጣት መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የደህንነት እጦት (insecurity) የሚያሳይ ነው። በቤተሰቡ በተለይም በአባቱ ላይ ተከፍቶ የነበረው የማጥፋት ዘመቻም ለጭንቀቱ መንስኤ ሊሆን ይችላል።
የሃይለመድህን ድርጊት ባለሁለት ሰይፍ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱም ሰይፍ መቆረጡ አይቀርም። ፓይለቱን የአእምሮ በሽተኛ አድርጎ ቢያቀርበው፣ ለአየር መንገዱ ትልቅ ኪሳራ ነው። መንገደኞች ከእንግዲህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጓዝ ድፍረቱ አይኖራቸውም፣ ለዚህም ይመስለኛል አቶ ሬድዋን ፓይለቱ ሙሉ ጤነኛ ነው ሲሉ መግለጫ የሰጡት። ወጣቱ ለስደት መጠየቂያ በማሰብ የወሰደው እርምጃ ነው ቢሉም፣ ” በደህና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሰው እንዴት ስደትን ሊመርጥ ቻለ?”፣ ከስደት የከፋ ችግር ቢያጋጥመው ነው ተብሎ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ መነሳቱ አይቀሬ ነው። መንግስት ግራ ሲጋባ ይታየኛል
posted by :Bethel Solomon