Friday, August 28, 2015

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት

August 27, 2015

የግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።
“ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የማኅበራዊ ስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ እና ደካማውን ወያኔን ጠንካራ በማስመሰል በሕዝብ የትግል መንፈስ ውስጥ ፍርሃትን የረጨ መሆኑ ግንዛቤ እየዳበረ በመጣ መጠን እየቀነሰ የመጣ ክስተት ነው። በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን ከህወሓት ባርነት እያላቀቅን ምሬታችንን በግልጽ መናገር የጀመርንበት ወቅት ነው፤ ከዚያም አልፎ የህቡዕ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃዎችን ማድረግ ደረጃ ላይ ደርሰናል።
አገር ውስጥ እየተዋረደ የመጣው “ወይን ለመኖር” በአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ዲያስፓራ) መካከል ነፃነታቸውን በጥቅም የሚለውጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ፍለጋ ተሠማርቷል። አገዛዙ ተስፋ ያደረገው ያህል ባይሆንም ጥረቱ የተወሰነ ውጤት እያስገኘለት ነው። በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ካመጣቸው ውስጥ በስርዓቱ ብልሹነት ያዘኑና የተሰማቸውን በግልጽ የተናገሩ መኖራቸው የሚያስደስትና የሚያበረታታ ቢሆንም ከመንደር ካድሬዎች ባነሰ ተለማማጮችና አጎብዳጆች በማየታችን ተሸማቀናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለነው አብዛኛው ሕዝብ አንፃር ሲታይ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ዲያስፓራዎች መካከልም ነፃነታቸውን በጥቅም ለመለወጥ የሚፈቅዱ መገኘታቸው አሳዛኝ ነው። እነዚህ ክብራቸውን በጥቅም የለወጡ ዲያስፓራዎች ዓለም ባንክንና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ተክተው ህወሓት ስላስገኘው ፈጣን እድገት በአገዛዙ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ሲነግሩን መስማት ያሳፍራል። የህወሓት አገዛዝ “ፍትህን፣ መልካም አስተዳርንና ዲሞክራሲን አስፍኗል፤ ይህንንም መጥተን በዓይኖቻችን ተመልክተናል” እያሉ የግፉን ገፈት እየቀመስን ላለነው ሲነግሩን መስማት ያማል።
እነዚህ ወገኖቻችን ህወሓትን በማሞካሸት የሚያገኙት መሬት ብዙ ድሆች የተፈናቀለቡት፤ ለእነሱ በብላሽ የተሰጠው ብድር በረሃብ ለሚጠቃ ወገን የተላከ እርዳታ መሆኑ ማሳሰብ ይገባል። ከህወሓትና አጫፋሪዎቹ ጋር ተስማምተው ባገኙት ገንዘብ የሚቆርሱት እያንዳንዱ እንጀራ የብዙ ወገኖቻችን ደምና እንባ የፈሰሰበት መሆኑ ማስገንዘብ ያሻል። ከህወሓት ጋር በማበር በወገኖቻችን ድህነትና ችጋር እየከበሩ ያሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት ከዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቅ ይገባል። እኚህ ወገኖች የራሳቸው ክብር ማጉዳፋቸውን ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻቸውም የሚያፍሩባቸው መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ከዚህም አልፎ የዛሬ ተግባራቸው ነገ በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ላይ የተሰማሩ፤ በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ያሉ፤ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአገዛዙ ጥብቅና የቆሙ የዲያስፓራ አባላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 “ከህወሓት ውድቀት በኋላ ያለው ጊዜ ለእናንተም ከዛሬው የተሻለ ይሆናል። ዛሬ ከህወሓት ጋር ያላችሁን ሽርክና አቋርጡ። ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እርዱ፤ መርዳት ባትችሉ እንቅፋት አትሁኑ፤ አለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት የማታመልጡ መሆኑን እወቁ” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!! !

Monday, August 24, 2015

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ እንዳይፈቱ እገዳ ተላለፈ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46143#sthash.5IHtjDti.dpuf

(ነገረ ኢትዮጵያ) ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡ አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46143#sthash.5IHtjDti.dpuf

Saturday, August 8, 2015

የአስመራ ሰዎች በአዲስ አበባ – (ዜና ትንታኔ)

ቻላቸው ታደሰ ለዋዜማ ራድዮ እንደዘገበው: 

ኤርትራ በ1990 ዓ.ም ኢትዮጵያን በወረረች ማግስት መንግስት በረፊረንደሙ የተሳተፉና ለብሄራዊ ደህንነት አደገኛ ናቸው ያላቸውን በሽዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በጅምላ ከሀገር ማባረሩ ይታወሳል፡፡ ሰዎቹ ሲባረሩ ያፈሩት ሃብትና ንብረት በአግባቡ ሳያደላድሉና በህጋዊ መንገድ ለተወካዮቻቸው ሳያስተላልፉ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ ይህ የግብር ይውጣ እርምጃ ብዙ ዓለም ዓቀፍ ወቀሳም አስከትሎ ነበር፡፡ 

የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ጦርነት ምንጭ ሳይደርቅና ዕርቀ ሰላምም ሳይወርድ ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ከአምስት ዓመት በፊት ባወጣው ደንብ በወረራው ወቅት የተባረሩ ኤርትራዊያን እንደገና በኢትዮጵያ ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያገኙ፣ የቀድሞ ንብረታቸው ከፈለጉም ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው እንዲመለስላቸው ብሎም ከሀገሬው ሰው እኩል ንብረት ማፍራት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡ መታወቂያና የእርሻ ቦታም ሳይቀር ተስጥቷቸው ከሀገሬው ሰው ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ በባንክም ተቀማጭ የነበረ ገንዘባቸውም ተመልሶላቸው እንደማንኛውም የውጭ ዜጋ በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሳተፉ፣ የማህበራዊ ግልጋሎቶችን ደግሞ ከዜጎች ጋር በእኩል እንዲያገኙ አድረጓል፡፡ ስለሆነም የዚህ ፖሊሲ መነሻና ግብ ምንድን ነው? ፖሊሲውስ በኢኮኖሚ በተዳከመችውና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጡንቻዋ በተመናመነባት ኤርትራ ላይ ምን ዓይነት የፖለቲካ፣ ፀጥታና ኢኮኖሚያዊ አንድምታዎች ይኖረው ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች መመርመር ተገቢ ነው፡፡ 

በእርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራዊያኑ ስደተኞች ላይ ፖሊሲውን ማስተካከል ያስፈለገው የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦችን ለማቀራረብና ግንኙነታቸውንም ለማደስ አስቦ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ሆኖም ግን ይህ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሲ ከሰብዓዊነትና ወንድማማችነት መርሆዎች ባሻገር ሌላ ዓላማ እንዳለው መታዘብ አይከብድም፡፡ 

መንግስት ለበርካታ ኤርትራዊያን ስደተኛ ወጣቶችም የከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሽፕ በመስጠት በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ተመዝግበው በነፃ እንዲማሩ እያደረገ ነው፡፡ የተማሪዎቹን ጉዳይ ምፀታዊ የሚያደርገው ግን ከጦርነቱ መቀስቀስ በፊትም በርካታ ኤርትራዊያን በሀገራችን ነፃ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ይማሩ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ መንግስትም ከዜጎቹ በላይ ለኤርትራዊያኑ ተማሪዎቹ ደህንነትና ምቾት አብዝቶ ይጨነቅ እንደነበር የዚህ ሪፖርት አዘጋጅ ሳይቀር በኣካል ያየው ሃቅ ነበር፡፡ ሆኖም ተማሪዎቹ በወረራው ማግስት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ከሀገር ከመባረር አልዳኑም፡፡