Friday, October 31, 2014

International adoption made me a commodity, not a daughter

I was taken from my home in Ethiopia by a corrupt adoption agency. When I returned, I felt Ethiopian, but they saw me as an American
The author and one of her older sisters, Ribka Lemma, who had not seen each other in nine years following the author’s corrupt international adoption Photograph: Courtesy of Tarikuwa Lemma
In 2006, less than a year after my sisters and I were brought to Americaas the victims of a corrupt adoption agency, I told the Americans who were saying that they were our “forever” family that I wanted to return to Ethiopia. I didn’t want a new family, I wanted my family and my country back.
So, my adoptive family got in touch with my biological family in Ethiopia (using documents given to us by my father, that were confiscated from us by our adoptive family after we arrived) to find out the truth of our background, since they were lied to by the adoption agency. Through a translator in Ethiopia, my father told my adoptive family to bring my sisters and me back, where he would be able to enroll us in school.

Wednesday, October 29, 2014

Ginbot 7 Memorandum sent to The United Nations Security Council Sanctions Committee on SEMG’s report

October 28, 2014

Memorandum

TO: The United Nations Security Council Sanctions Committee 
Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

FROM: Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.
DATE: October 27, 2014

SUBJECT: Response to References made about Ginbot 7 in the Report of the Monitoring Group of Somalia and Eritrea (here after SEMG), Pursuant to UN Security Council Resolution 2111 (2013).
Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy expresses its high regards to The United Nations Security Council, and would like to use this opportunity and bring to the attention its reservations regarding some references made about it in SEMG report of October 13, 2014.
1. The SEMG report states that “Ginbot 7 is a banned opposition group”. We would like to call the attention of the International Community to the infamous “Anti-Terrorism Proclamation” promulgated by the TPLF/EPRDF regime of Ethiopia with the aim of stifling political dissent. The dictatorial regime has used this proclamation as an instrument to label and criminalize Ginbot 7, as well as other political opposition organizations, human rights advocacy groups, civil society, journalists and bloggers inside and outside of Ethiopia.
2. Let alone the claim in the report that Ginbot 7 was established in 2005, which is categorically false, even the so-called Anti-Terrorism Proclamation was not promulgated until 2009.
Ginbot 7 was formed in 2008 after few members among its leadership spent almost two years in prison in the aftermath of the ill-fated election of May 15, 2005. As well known by the International community, the regime overturned the election results that clearly showed the opposition party Coalition for Unity and Democracy (CUD) has won the majority throughout the country. This is a fact corroborated by international election observes such as the European Union’s Election Monitoring Group that was present in Ethiopia to observe the election in 2005. Those who formed Ginbot7, then leaders of the CUD, were among the leaders thrown in prison on trumped up charges.
Ginbot 7 was formed as a political movement in order to advance justice, freedom, and liberal democracy in Ethiopia. Ginbot 7 believes that no meaningful and genuinely competitive elections can take place in the country due to the prevailing and ever worsening egregious human rights violations, the closing of political space, the harassment and persecution of members of the legal and peaceful political opposition. Furthermore, an entrenched minority ethnocratic dictatorship in Ethiopia has determined to perpetuate its hold on power by all and any means necessary.

የማለዳ ወግ…. የተመስገን ደሳለኝ እናት…

የማለዳ ወግ … ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ ! ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ ፣ ተናደድኩ …በቁጭት ግን አልቆዘምኩም - See more at: 
ምን እንደምል አላውቅም … ለተጎዱት እናታችን አዝናለሁ ፣ ብቻ ሳይሆን ለመስዋዕትነት ለቀረቡት ለዚህች ቁርጥ ቀን ግንባራቸውን እንደ ተሜ ለሰጡት ብርቱ የሃገሬ ልጆች እናቶች በሙሉ አዝናለሁ “..ልጅሽ ወንድሜ ታስሯል! ” ለምትለው የመርዶ ነጋሪው ያንተ ጭንቀት ቢገባኝም ወጣት ነህና እንባህን ጠራርገህ ወንድምህ የሰጠንን ቃል አክብር ፣ ተከተልም! የጀግና ዘር አያለቅስም ! ተሜ አልነገረህም ? ወንድ ልጅ አደኮ አያነባም … በቃ እንዲያ ነው !!!! አንድ ወዳጀ ማምሻው ላይ ጋዜጠኛ ተመስገንን ታውቀዋለህ? አለኝ … እንዲህ መለስኩለት ወዳጀ Abdu ጋዜጠኛ ተመስገንን በአካል አውቀዋለሁ፣ ከሳውዲ ለእረፍት ሄጀ በአንድ መአድ ቁጭ ብለን ክፉ ደጉን አውርተናል። ከርሴን ልሞላ የተሰደድኩትና “በካሳደገኝ ላስተማረኝ ወገኔ አልለይም ፣ ከምወዳት ኢትዮጵያ ፣ አልሰደድም እንቢ ” ካለው ጋዜጠኛ ጋር የነበረን ቆይታችን ያማረ ነበር። ተሜ ከሃገር ውስጥ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ ኑሮውና ከዚያም አልፎ በሳውዲ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ወንድም መሆኑን ባውቅም ያኔ ደግሜ አረጋግጫለሁ። በኢትዮጵያ ላይ የመጣው አበሳ እያዘነ እየተቆረቆረ እንደ ዜጋና እንደ ባለሙያ ራዕዩን ሲያንሸራሽር የደረሰበት እንግልት ግድ የማይሰጠው ጀግና ወጣት ጋዜጠኛ ነው። እንዲያው በአጠቃላይ እኔ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ ማለት ይቀል ይሆናል ፣ ኢትዮጵያን እንደ ተሜ እወዳታለሁ ማለት አይቻልም። እሱን መሆን የእሳይ ወላፈኑን ፣ ረመጥ እሳቱን ጭምር እየተለበለቡ ኢትዮጵያን መውደድ ከቶ ማንስ ይቻለዋል። ለብዙዎቻችን በጣም በጣም ከባድ ነው ! በቆይታችንና ከተሜ ጋር ባለን ቀረቤታ የተረዳሁት ይህን እውነታ ነው! ስለ ኢትዮጵያና ስለህዝቧ ራዕዮን ስድብ ፣ግልምጫ ማግለሉ፣ ከመቶ ያለፈ ክሱ ፣ እስራት ፣ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻው ምኑ ቅጡ ይህን ሁሉ ተጋፍጦ ጋዜጣ መጽሔቱን ሲዘጉበት እየከፈተ ” ትግሌ እስከቀራንዮ ነው ፣ አልሰደድም” ያለ እንደ ተሜ ብርቱ ጋዜጠኛ መች አለ ? ይህን ተሜ አውቀዋለሁ! የጀግና ቤቱ ወህኒ ነው እንዲሉ ፣ ተሜ ወደ ቤቱ ገብቷል ! በቃ ተሜ “ስለተገፋሁበት ምክንያት ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ትጉ እንጅ ስለእኔ እንዳታለቀረሱ ” ብሎኛል ተሜ …የማውቀው ብርቱው ወዳጀ ጋዜጠኛ ተመስገን …ብየ መለስኩ ! እናም እውነቴን ነው የምልህ ፣ በተሜ ኩራት የደም ስጋ ፣ የአንድ ማህጸን የእማማ ልጅ ስለሆንክ ክብር ይሰማህ እንጅ ተሜ ” አታልቅሱ ” ብሏልና አታልቅስ …ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ ቀራንዮ በግርማ በክብር እየሄደ ነው ፣ ሆዳችን አታባባው … ዳሩ ግና ምን የሚባባ ሆድ አለን ? … ብቻ ይሁን :
( ነቢዩ ሲራክ)

Link:- http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35768#sthash.jTNHEb3V.1mJY7PIL.dpuf

Monday, October 27, 2014

ተነስ

ተነሰ ያገሬ ሰዉ 
ከንድህን አበርታ
ሃሳብህን ሰብስብ 
ከሮሮ ጠዋት ማታ!
ወገብህን ታጠቅ ለነጻነትህ
ፍትህ ዲሞክራሲ ለከለከህ
መሬትህን ነጥቆ ባሪያ ላደረገህ
መብትህን ላሳጣህ በወንዝህ በሀገርህ
የበይ ተመልካች አርጕ ላስቀረህ
ከፋፍሎ ለገዛህ ሰላምህን ረግጦ
ህልውናህን ሊያጠፋው መብትህን ደፍጥጦ::
ለወያኔ ጕጀሌ ፊትህን አትስጠው
አትበርከክለት ወኔህን አሳየው
ተነስ ቶሎ ተነስ ጊዜው ነገ ሳይሆን
መነሻህ አሁን ነው::

ከቤቴል ሰለሞን

Sunday, October 26, 2014

በአገር ላይ የሚመጣ አደጋን አቅልሎ የማየት ያልሰለጠነ አስተሳሰብ




(ኤፍሬም እሸቴ) 
ታዳጊ አገሮችን በሙሉ የሚያመሳስላቸው አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ከገደል አፋፍ ቆሞ ገደሉን መናቅ፣ ከአደጋ ጫፍ ቆሞ አደጋን ማቃለል፤ ከዚያም ከገደሉ ወድቆ መሰበር፣ በአደጋው ተጠራርጎ መወሰድ። ይህ ሐሳብ በርግጥ ፍንትው ብሎ የታየኝ የማሌዢያ አውሮፕላን በዩክሬይን ሰማይ ላይ በሚሳኤል በጋየበት ጊዜ ነበር። ሁላችሁም እንደምታስታውሱት የሰው አካል ቁርጥራጭ ከሰማይ ይዘንብ እንደነበር እማኞች ሲናገሩ መልክተናል። ታላላቆቹ የዜና አውታሮች ራሺያ ላይ አተኩረው ነገሩን በዚያ ፈፀሙት አንጂ “አውሮፕላኑ በጦርነት ሰማይ ላይ ለምን ሄደ?” የሚለውን የሚያነሱ ሰዎችም ተደምጠዋል። ብዙ አየር መንገዶች አቅጣጫቸውን ቀይረው በሌላ መስመር መሔድ ከጀመሩ ቆይተው ነበር። የሳንቲም ስባሪ ለማትረፍ አንድም በማሌዢያኛ “አቦ አታካብዱ” ብለው ሳይሆን አይቀርም በዚያ በታዳጊ አገር አስተሳሰብ መንገዳቸው ሳይቀይሩ ቀሩ። “የእባብ ጉድጓድ በጅል ክንድ ይለካል” እንደሚባለው የዩክሬይን አየር በማሌዢያ አውሮፕላን ክንድ ሲለካ ጅልም እጁ አይተርፍ፣ አውሮፕላኑም አልተረፈ። ተመሳሳይ ነገር እነሆ ሊከሰት ነው። ኢትዮጵያ በበኩሏ 200 ነርሶች ወደ ኢቦላ ዞን (Ebola ZOne) ልትልክ ጀብደኛ ውሳኔ ወስናለች። የማሌዢያ ውሳኔ። ኢቦላ ምዕራብ አፍሪካን ምን እያደረገ ነው? ከበሽተኛው በሚወጣ ፈሳሽ በሚተላለፈው በዚህ በሽታ የአገራች ኢኮኖሚ እንዴት እንዴት እየሆነ ነው? የዚያ አገር ዜጋ የሆኑ በማለው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች እንዴት እየታዩ ነው? ምን ዓይነት ችግር እየገጠማቸው ነው? አይበለውና በሽታው አገራችን ቢገባ ዘመዶቹን በማስታመም የሚታወቅ የአገራችን ሰው እንዴት ባለ አደጋ ላይ ይወድቃል? የትኛው ሆስፒታል በርግጥ ብቁ ነው? መቸም በፌዴራል ፖሊስ ዱላ አታስቆሙት ነገር።“የሕዳር በሽታን” በአገራችን በ21ኛው ክ/ዘመን ልታመጡብን ካልሆነ በእውነቱ ምን ሌላ ምክንያት ይኖራችኋል? በዓለም ላይ በሕክምና አያያዛቸው ጥራት የተመሰገነላቸው ብዙ አገሮች አሉ። ኢቦላን በረዓድ እያዩት ነው። ሕዝቡ ገና ስሙን ሲሰማ ሽብር ይይዘዋል። አንድ ሰው ቴክሳስ ግዛት በበሽታው በመሞቱ መላው አሜሪካ ከሥሩ ነው የተነቃነቀው። በርግጥ እነርሱ ፈሪዎች ስለሆኑ እኛ ጀግንነት ይዞን ይሆን? የሚመጣውን ጉድ ስለሚረዱት ነው። ይህንን ያልሰለጠነ አስተሳብ እንዴት ማስለቀቅ ይቻል ይሆን? አለመሰልጠን ወንጀል አይደለም ነገር ግን አገር ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ እያወቁ ለጋ ወጣቶችን ወደ እሳት መላክ ግን ሌላ ዓላማ እንዳለው ነው የሚረዳኝ። ምናልባት በበሽታው የሚገኝ ትርፍ እንዳለ እንጃ። ፈጣሪ ሕዝቡን ይታደገዋል። ለእናንተ ግን እንጃ!!! - 


Link:-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35726

Saturday, October 25, 2014

“አርማጌዶን” የፍጻሜያችን ፍጻሜ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

በዚያው ሰሞን ነው የወያኔ ባለሥልጣናት ሲያሾፉብን “ይሄንን ሁሉ ሰይጣናዊ ድርጊት የሚፈጽሙት በዓላማ እነሱ መሆናቸው ተረስቶ” ከመሀከላቸው አንዱ ምን አለ “የሕወሀት መሪዎች በዚህ ወቅት በብሔሮች መካከል ያለው የጥላቻ መንፈስና የወደፊት የሀገሪቱ ሁኔታ እጅግ አሳስቧቸዋል በጣምም እየተጨነቁበት ያሉበት ጉዳይ ነው የብሔራዊ እርቅ ጉዳይ አስፈላጊነቱ የግድ እንደሆነ ያስባሉ እንዴትና ከማን ጋራ እንደሚጨርሱት ተቸግረው ነው እንጅ….” ብሎ ቀለደብን፡፡
ከእኛም ወገን ደግሞ ጅሎቹ የዋሀኑ ተላሎቹ እውነት መስሏቸው በየፊናቸው አንዳንድ ነገሮችን እስከማለት ደረሱ፡፡ ወያኔ ግን ወያኔ ነውና ንጹሕ መስለው አሳሰበን ካሉ በኋላም እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም በዓላማ ይሄንን ሰይጣናዊ የዘርና የሃይማኖት ግጭት ፍጅት ለመፍጠር ሴራውንና ድርጉቱን እየፈጸመ ይገኛል ተፈጥሯዊ ባሕርይው ነውና እስካለ ጊዜ ድረስም ሲፈጽም ይቆያል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በቀደም ጥቅምት 7-2-2007ዓ.ም. በነበረው ዝግጅቱ የመ.ኢ.አ.ድ ተወካይ ከሆኑት ሰውና ከሁለት ተጠቂ የአማራ ተወላጅ ቁስለኞች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከዚህ ዓመት ዋዜማ ከጳጉሜ 5 ጀምሮ እስከ አሁንም ድረስ በመከላከያ በፌደራልና በፖሊስ ሠራዊት አባላት ሁለቱ ብሔረሰቦች በቦታው ከሐምሳ ዓመታት በላይ አብረው ተከባብረው እንዳልኖሩ ሁሉ በአማራ ተወላጆች ላይ ከመዠንግር ተወላጆች የተቃጣ የተፈጸመ ጥቃት አስመስለው የወሰዱትና እየወሰዱት ባሉት ጭፍጨፋ ወይም የጅምላ ግድያ ወይም የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከ አሁን ድረስ ከ540 በላይ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል፣ ከ25 ባለይ ቤቶች በኗሪዎቹ ላይ እንደተዘጉ እሳት ተለቆባቸው እንዲቃጠሉ ተደርጓል፣ ከዚህ የተረፉት ሕፃናት እናቶች አረጋውያን ዕድሜ ልክ የለፉበት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለው እንዲሰደዱ ተደርጓል፡፡

Wednesday, October 22, 2014

ሚሊየኖች ድምጽ – ሃብታሙ አያሌው በጠና ታሟል – ሆስፒታል ነው ዛሬ የዋለው

  • 588
     
    Share
Habitamu Ayalewየአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ግብረ ኃይል ሰብሳቢ የነበሩት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው በጸና መታመማቸዉንና ዛሬ በሆስፒታል መዋላቸዉን ለማረጋገጥ ችለናል።
የማእከላዊ እሥር ቤት ብዙ ቶርቸር የሚደረግበት እስር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። አቶ ሃብታሙ አያሌው ከብሎገር አብርሃ ደሳታ፣ ዳን ኤል ሺበሺና የዚዋስ አሰፋ ጋር ሐመሌ 1 ቀን የታሰሩ ሲሆን፣ ፖሊስ «መረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ ይሰጠኝ» በሚል አራት ጊዜ ለሃያ ስምንት ፣ ሃያ ስምንት ቀናት መጠየቁ መዘገቡ ይታወሳል። በፍርድ ቤቱ የተቀመጡ ዳኞችም፣ ፖሊሲ ምንም አይነት መረጃ ሳያቀርብ፣ የእነ ሃብታሙን የዋስትና መብት በመከልከልና በወህኒ እንዲቆዩ በመፍቀድ፣ ሕግን የሚያስፈጽሙ ሳይሆን ፣ ለሕጉ ዉጭ በቀጥታ የፖሊስን መመሪያ የሚይሳተናግዱ መሆናቸዉን አሳይተዋል።
አቶ ሃብታሙ በአገራችን ፖለቲክ ትግል በዘመናችን የተነሱ አንጋፋ ፖለቲከኛ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ገዢው ፓርቲ በርሳቸው ላይ ኢሰብአዎና ኢፍትሃዊ ግፍ መፈጸሙ በካላላቸው ላይ ጉዳይና ሕመም ቢያስከትለም፣ በመንፈሳቸው ግን ከመቼዉም ጊዜ በላይ ጠንካራ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/2154#sthash.oVNLqWH5.MKpBDX8Y.dpuf

Monday, October 13, 2014

“መፈንቅለ ዓለም ባንክ!”

   ኢትዮጵያን ኦባንግ በብቸኝነት ወክለዋል
ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል የዓለም ባንክ በተለይ ከሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ስብሰባ “በመፈንቅለ ዓለም ባንክ” ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች በመወከል ድምጻቸውን የሚያሰሙትኦባንግ “በመፈንቅሉ” ከተሳተፉት የዓለም ሲቪል ማኅበረሰቦች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡
የዓለም ባንክ ስለሚሰጠው ብድርና ዕርዳታ በተመለከተ ሊያካሂድ ያሰበው የፖሊሲ ለውጥ ሰነድ አፈትልኮ ከወጣ ጀምሮ በርካታ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሟገቱ ዓለምአቀፍ የሲቪል ማኅበረሰቦችን ያስቆጣ ሆኗል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ ለታዳጊ አገራት ብድር ከመስጠት ባለፈ በተለይ አምባገነናዊ አገዛዝ በሰፈነባቸውና አገዛዞቹንም ለሚደግፉ ድርጅቶች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ገንዘብ መስጠትን የሚፈቅድ ነው፡፡
በዚህ አሠራር መሠረት ማንኛውም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለማድረግ የሚፈልግ ድርጅት ወደ አንድ ታዳጊ አገር ለመሥራት በሚፈልግበት ጊዜ ባንኩ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሳይጠይቅ ብድር ይፈቅድለታል፡፡ ሆኖም ድርጅቱ በዚያ ታዳጊ አገር ላይ የሰብዓዊ መብቶችን በመርገጥ፣ ከአምባገነናዊ ሥርዓቶች ጋር በመመሳጠር የፈለገውን ሕገወጥ ድርጊት ቢያከናውን የሚጠይቀው አይኖርም፤ ይህም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦ ብድሩን አያስከለክለውም፡፡
ለምሳሌ፤ መሬት ያለአግባብ ቢነጥቅ፣ ነዋሪዎችን ከቦታቸው ቢያፈናቅል፣ ለስደት ቢዳርግ፣ ህጻናትን በሥራ በማሰማራት “ባርነት” ቢያካሂድ፣ … ማንኛውንም ሰብዓዊ መብቶችን የሚረግጥ ሥራ ቢሰራ ለኢንቨስትመንት እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ባንኩ ተጠያቂ አያደርገውም፤ ብድርም አይከለክለውም፡፡ ይህ አሁን ባንኩ ካለውና በበርካቶች ከሚተቸው አሠራሩ እጅግ መረን የለቀቀ ነው፡፡
የብሪክሶችን (BRICS – Brazil, Russia, India, China and South Africa) አሠራርና አካሄድ ለማክሸፍ የተነጣጠረ ነው የተባለለት ይህ የዓለም ባንክ ፖሊሲ ለውጥ ከ750 በላይ ዓለምአቀፍ የሲቪል ማኅበረሰቦች ተቃውመውታል፤ አሠራሩ እንዲቀየርም የማሻሻያ ፖሊሲዎችን ነድፈው አቅርበዋል፤ ለሳምንት ያህል በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለባንኩ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ  በመዠንገርና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል በተነሳው ግጭት ብዙ ነዋሪዎች መገደላቸው ተሰማ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቴፒ አካባቢ በመዠንገር ብሄረሰብና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ህዝብ ካለቀ በሁዋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ለጊዜያው ያበረደው ቢመስልም፣ ግጭቱ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ አቅጣጫ ተዛምቶ እስካሁን ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶችም በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የተነሳው ግጭት በማየሉ፣ በተለይ ... Read More »

በአዳማ በተደረገው የኢህዴድ ግምገማ አባላትና አመራሩ ተዘላለፉ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ከኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከየከተማው እና ከየወረዳው የተውጣጡ ከ300 በላይ አባላት በተሳተፉበት ግምገማ በአመራሩና በአባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እርስ በርስ መዘላለፍ ደረጃ ደርሰው እንደነበር በስብሰባው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማው የተመራው በአዳማ ከተማ ከንቲባ ሲሆን፣ ከንቲባው ቀደም ብለው ያዘጋጁዋቸው አባላት በምክትሉ ከንቲባ በአቶ አህመድ የሱፍና በድርጅት ጉዳይ ሃላፊው በአቶ ፍቅሩ ጂረኛ  ላይ ... Read More »

መንግስት የ20 በ80 አሰራር እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላለፈ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የ20 በ80 አሰራርን ተግባራዊ እንዲያድረጉ ታዘዋል። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ጊዜያቸውን ለመንግስት ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ለሚሰሩዋቸው ስራዎች እንዲያውሉ ተነግሯቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነው የሰው ጉልበት፣ ባጀት፣ ጊዜና የመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ ለምርጫ ማደራጃ፣ ለአባላት ቅስቀሳና ማደራጃ እንዲውሉ ... Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በኢምባሲ ውስጥ ገብተው የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን እንዲከሰሱለት ጠየቀ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የአሜሪካ መንግስት የአገሪቱን ሰንደቃላማ በአወረዱ  ተቃዋሚዎች ላይ ክስ ይመሰርታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ቃል አቀባዩ ተቃዋሚዎቹ ከኤርትራ መንግስት እና ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱን አለመወጣቱን የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ ተቃዋሚዎቹን ለፍርድ ያቀርባል ብለው እየጠበቁ መሆኑንም አክለዋል። አምባሳደር ግርማ ብሩ ተቃዋሚዎቹ ክስ ... Read More »

የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች የ8 ቀን ስልጠና ቅጣት ተጣለባቸው ሲል ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን እንዲሰለጥኑ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የዘገበው ነገረ ኢትዮጵያ፣ ከመስከረም 19/2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 4 ሺ 100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ መደረጉን አስታውሷል፡፡ ... Read More »

አምባሳደር ሚኒልክ የስራ መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄነቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፅ/ቤት ባለሙሉ ስልጣን በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታሁን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ማግኘታቸውን ተከትሎ  ሃላፈነታቸውን መልቀቃቸውን  ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል። የኢህአዴግ ዋና ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው አምባሳደር ሚኒልክ ፣ ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ በመቆየታቸው ” ታጋይ ሚኒልክ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ... Read More »

መንግስት የባንዲራ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ጀምሯል።

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከሚፈስባቸው የመንግስት ክብረ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የባንዲራ ቀን ዘንድሮም ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓም በአዲስአበባ ስታዲየም በድምቀት እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል። “በሕዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯን እና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር!” በሚል መሪ ቃል  ለ7ኛ ጊዜ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከአዲስአበባ ... Read More »

በአዋሳ አንድ ባለሀብት ጠበቃ ገድለው ተሰወሩ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ ባለሀብቱ የመንግስት ታክስ አልከፈሉም ተብለው ... Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች በመሰረተ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኋላ መቅረታቸውን  የወረዳ አመራሮች  በግልጽ በማቅረባቸው ከክልልና ዞን ባለስልጣናት ግሳጼ እንደደረሰባቸው ተናገሩ፡፡

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ህብረተሰቡ ምን ይለናል የሚለውን ለማዳማጥ ከሰሜን ጎንደር ከተሰባሰቡ የወረዳ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ የወረዳ አመራሮች በንባብ እንዲያሰሙት ከየዞን ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ማስታወሻና አቅጣጫ ወደጎን በመተው መንግስት እንዲያስተካክላቸው በጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ምክንያት ከስብሰባው በኋላ ወከባና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ለከፍተኛ አመራሮች ... Read More »

“ሰራዊታችን ህብረብሄር ሆኗል” ሲል ኢህአዴግ ገለጸ

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች  እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ”  በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ እያለና በመጀመሪያዎቹ አመታት ከትግሉ ... Read More »
Link:-http://ethsat.com/amharic/

Saturday, October 11, 2014

ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ


ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት
ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ
መስከረም 2007 ዓ.
ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ ትግራይ (ሕወሓት) ምን ያክል የኢትዮጵያን የፖለቲካ መዋቅሮች እንደሚቆጣጠር ለማወቅ በአገሪቱ የመከላከያ፣ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች ዉስጥ ዋና ዋና የትዕዛዝ ሰጪና ቁጥጥር ቦታዎች ላይ በሀላፊነት የተቀመጡትን የትግራይ ተወላጆች ብዛት መመልከቱ በቂ ይመስለናል። የሕወሓት መሪዎች ስልጣን በያዙባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት ዉስጥ እየገነቡት ላይ ያለዉን ስርዐት መልካምና ሁሉን አቀፍ ስርዓት ለማስመሰል አንዳንድ ከነርሱ ቁጥጥር ዉጭ መተንፈስ እንኳን የማይችሉ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆችን አልፎ አልፎ ስልጣን ላይ አስቀምጠዋቸዉ ነበር። ዛሬ ሕወሓቶችን እራሳቸዉን እጅግ በጣም በሚያሳፍር መልኩ እነዚህ በጥንቃቄ ለቅመዉ ያመጧቸዉንም የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ወደመጡበት መልሰዋቸዉ በሁሉም መስክ ቁልፍ የሆኑ የአገሪቱን  የስልጣን ቦታዎችን የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ተወላጅ ሕወሓቶች ብቻ ሆነዋል። አያሌ ኢትዮጵያዉያን የህወሓትን አገዛዝ “ዘረኛ” አገዛዝ ነዉ ብለዉ የሚጠሩት ይህንን ሙልጭ ያለ በዘር ላይ የተመሰረተ ጭፍን አገዛዝ ተመልክተዉ ይመስለናል።
images (2)

Friday, October 10, 2014

ትምክህተኛና ጠባብ ማን ነው? – ከአስገደ ገ/ስላሴ መቀሌ


አቶ አስገደ ገ/ስላሴ
አቶ አስገደ ገ/ስላሴ
የህወሓት ኢህአደግ መንግስት ፖሊሲና ስትራተተጂ ስልጠና በሚል ሽፋን ተማሪዎች በሃገር ደረጃ ከ300 ሺ በላይ የፍትህ አካላት ማለት ዳኞች ቸቃብያን ሕግ ፖሊሶች በሙሉ መጀመርያ በየ ክልሉ ለ15 ቀናት ስልጠና ተሰጣቸው በተለይ በትግራይ የፈትህ አካላት በውቅሮ 15 ቀን በአክሱም ከዛ በላይ እየሰለጠኑ ይገኛሉ::
በዚሁ ስልጠና በሁሉም ቦታ ማለት ይቻላል:: የድሮ ነገስት በማንሳት በፊሊም የተቀረፀ እነዛ ነገስታት የትምክህትና የጠባብነት ምንጭ መሆናቸው:: ሃገራችን ዘር ሃይማኖት ቢሄር ከቢሄር እያጋጩ የትምክህትና ጠባብነት መፈንጫ አድርጎዋታል በማለት ሲያማርሩ ከርመዋል:: በሌላ በኩል የህወሓት ኢህአደግ መንግስት ካለፉት ስርዓቶች የበለጠ ሃገራችን እንደቀየረ ሲነግሩን ከርመዋል::
በተሰብሳቢዎች ግን የምትነግሩን ያላቹሁ በንቃተህልናቸው አሁን ካለው ትውልድ እጅጉን የወረዱ ነበሩ:: ያም ሆኖ ሃገራችን አንድነቷና ሉኦላዊነቷ ጠብቃ እንድትኖር አድርጓታል:: እናንተ ግን የዚህች ሃገር ሉኦላውነቷ ያስደፈራቹሁ ናቹሁ:: ኢትዮዽያ የባህር በሯን አሳልፋቹሁ ሰጥታቹሁ በሁሉም ነገረ ጠገኛ አድርጋቹሁን አላቹሁ ሃገራችን በቋንቋ በወንዝ እንድትከለልና ዜጎች በፈለጉት በሃገራቸው ክልል ሰርተው እንዳይኖሩ በማደረግ ጠባብነና ትምክህት እንዲነግስ ከማድረጋቹሁ አልፎ የሃይማኖት የቢሄር ግጭት ተስፋፍቶ ዜጎች እርስ በእርሳቸው እንዳይተማመኑ አድርጋቹሁ እነ አፀይ ዩሃንስ አፀይ ምንሊክ የቴክኖሎጂ እውቀት ባልነበረባቸው ምንም እንኳ አንዳንድ ስህተቶች ቢኖሩዋቸው እቺ ሃገረ ስትደፈር የኢዮዽያ ህዝብ እንደ አንድ ሰው ሆኖው ሕብርና ሃገራዊ ወኔን በመፍጠር ሃገራችን ከባዕድ ወረራ ተከላክለው አቆይቶውናል:: እናንተ ግን በጥቂት የፓርቲ አመራር ውሳኔ ብዙ ስህተት ፈፅማቹሃል:: በተጨማሪም ለህዝቡ ይሁን ለመንግስት ሰራተኛ በአንድ ወጥ በማስተማር ፈንታ የትግራይና የኦሮሞ ህዝብ የአፀይ ምንሊክ መጥፎ ገፅታ በፊልም በማሳየት በአማራም በኦሮሞ ወይም የትግራይ ነገስታት መጥፎ ገፅታ በማሳየት በሌሎች ቢሄሮች ቢሄረሰቦችም እንደዚሁ እንዲናናቁ አድርጋቹሃል ተብለዋል::

Sunday, October 5, 2014

የወያኔው ወመኔዎች መንግስት የደህንነት ቡድን በድጋሚ በአዲስ መልክ ተዋቀረ

(ምንሊክ ሳልሳዊ)
የቀድሞው መዋቅር ከተቃዋሚ ሃይሎችና ለሚዲያዎች የመረጃ ክፍተት ፈጥሮላቸዋል።
– የዲያስፖራውና የተቃዋሚዎች ትግል ፍሬ ማፍራቱ የደህንነት ተቋሙን አደፍርሶታል።…
– የተጀመረው ፍሬያማ ትግል እያደገ መሄዱ መጪውን ጊዜ ለወያኔ ጨለማ አድርጎበታል።

የተቃዋሚ ሃይሎች እና የዲያስፖራው ህዝባዊ ተቃውሞ በርትቶ እና ገኖ መውጣት፣በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣የካድሬዎች እንቢተኝነት፣ የውጪ ሃይሎች ጫና፣ የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ የሃገሪቱን እና የሕዝቡን አንጡረ ሃብት ስድሳ ከመቶውን ካለምንም እውቅና በዘፈቀደኝነት ለደህንነት እና ለስለላ ተግባር የመደቡት ከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መልክ እንደገና መዋቀሩን ምንጮች አስታውቀዋል።
ኢሕአዴግ ውስጥ በተነሳው የብሩህ ተስፋ ክሽፈት የመጣ በባለስልጣናቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት አመራሮችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። ባለፉት 23 አመታት በህዝብ እና በሃገር ላይ የተደረገው ከፍተኛ የሆነ በደል እና ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ እንዳስነከሰባቸው እና መጪው ጊዜ ይጨልምብናል ብለው ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው በአራት ቡድኖች የተከፋፈለ በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ እና በመላው ሃገሪቱ የተበተነ የድህንነት እና የስለላ ሃይል ማሰማራታቸው ታውቋል።
tplf-rotten-apple-245x300
በከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ዳግም የተዋቀረው በየአከባቢው ከመንደር እና ቀበሌ ጀምሮ እስከ ከተሞች የገጠር ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በወያኔ ላይ ደባ ይሰራሉ ይፈጸማሉ ይመከራሉ የተባሉ እያንዳንዱን የዜጎች እንቅስቃሴዎች ሪፖርቶችን በትጋት በመሰብሰብ ወደ መሃል አገር በመላክ መታፈን ያለባቸው መገደል ያለባቸው ደብዛቸው መጥፋት ያለባቸውን ሰዎች በተመለከተ ከበላይ በሚተላለፍለት ትእዛዝ መሰረት መፈጸም ዋናው ስራው ነው።

ወያኔ የሚጠራው መጪው ምርጫ ሕዝቡ በ1997 እንዳደረገው አሁንም እንዲሁ ቂሙን በካርድ ይገልጽብናል በማለት የሚሰጋው ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እርምጃ በመጠቀም ለማክሸፍ የሚያስችለው በየትኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሊሆን እንደሚችል ስለላውን ተያይዞታል፤በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች የካድሬዎች እንቢተኝነት የውጪ ሃይሎች ጫና የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ ማጣፊያው አጥሮት የሃገሪቱን ግማሽ በጀት የሚሆነውን ለደህንነት እና ለስለላ ተግብር በማዋል ከፍተኛ የሆነ አደጋ በሃገር ላይ አውጆ ሕዝብን እያሸበረ ይገኛል።
Link:-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35094