Monday, October 27, 2014

ተነስ

ተነሰ ያገሬ ሰዉ 
ከንድህን አበርታ
ሃሳብህን ሰብስብ 
ከሮሮ ጠዋት ማታ!
ወገብህን ታጠቅ ለነጻነትህ
ፍትህ ዲሞክራሲ ለከለከህ
መሬትህን ነጥቆ ባሪያ ላደረገህ
መብትህን ላሳጣህ በወንዝህ በሀገርህ
የበይ ተመልካች አርጕ ላስቀረህ
ከፋፍሎ ለገዛህ ሰላምህን ረግጦ
ህልውናህን ሊያጠፋው መብትህን ደፍጥጦ::
ለወያኔ ጕጀሌ ፊትህን አትስጠው
አትበርከክለት ወኔህን አሳየው
ተነስ ቶሎ ተነስ ጊዜው ነገ ሳይሆን
መነሻህ አሁን ነው::

ከቤቴል ሰለሞን

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.