Wednesday, January 28, 2015

በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉ 3 አርቲስቶች

Kibebeew geda


ከሮቤል ሔኖክ

እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።
ዛሬ ዛሬ ደግሞ ላለፉት 23 ዓመታት ሃሳባቸውን በነጻነት ከሚገልጹት ጋዜጠኞች ባልተናነሰ በመንግስት ጥርስ እየተነከሰባቸው የሚገኙት የጥበብ ባለሙያዎች እየሆኑ ነው።
እንደሚታወቀው በስደት ዓለም ከ150 በላይ ጋዜጠኞች እንዳሉ ሁሉ ዛሬ ቁጥራቸው በዛ ያሉ አርቲስቶችም በስደት ይህንን ስርዓት በመሸሽ በስደት ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ መንግስት እንደታላቁ እስክንድር ነጋ አስሮ ለማሰቃየት ከሚፈልጋቸው ታላላቅ አርቲስቶች መካከል 3ቱ ዋነኞቹ ሲሆኑ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ገና መንግስት እያጎበጎበባቸው በመሆኑ የ3ቱን ገድል አሳይቻችሁ የሁለቱን እንስት አርቲስቶችን ማንነት አስተዋውቃችኋለሁ።
1ኛ. ታማኝ በየነ
ብዙዎች እንደስሙ ነው ይሉታል። አክቲቪስት ሆኗል ከአርቲስትነቱ በተጨማሪ። አላሙዲ ካደረገለት በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገልኝ ይበልጣል በሚል ዛሬም ድረስ የያዘውን አቋም ባለማዋዠቅ ይህን ተራ መንግስት ማንነቱን በማጋለጥ ላይ ይገኛል። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ “የሕዝብ ልጅ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ታማኝ በየነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አንባገነን ስርዓት ከዚህ አርቲስት ጎን ፎቶ የተነሳ፣ የታየ፣ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው የሚል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል። ታማኝ በየነ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ክብርን ያገኘ በመሆኑና ክብሩንም ለገንዘብም ይሁን ለታይታ ያልቀየረ በመሆኑ ብዙዎች የሚያከብሩት ሲሆን የሕወሓት መንግስት ይህን ታላቅ አርቲስት በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የማፈነቅለው ድንጋይ የለም።
ታማኝ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆን በግሉ በሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በነፃነት እያጋለጠ ዘረኛውን ስርዓት እርቃኑን እያስቀረው ሲሆን በተለይም መንግስትን የሚያጋልጠው ራሳቸው የመንግስት ባለስልጣናት በሚሰጡት እርስ በእርሱ በሚጣረስ በቪድዮ የታጀበ ቃለምልል መሆኑ በብዙሃን ዘንድ ተወዳጅነትን በሥርዓቱ ዘንድ ደግሞ ለመታሰር ከሚፈለጉ 3ቱ አርቲስቶች መካከል አንዱ ሆኗል።
2ኛ. ፋሲል ደመወዝ
አርቲስት ፋሲል ደመወዝን የማውቀው አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሚባል ሰፈር በተለምዶው ሸለቆ የሚባል አካባቢ ነው። በሸለቆ አካባቢ ሲራመዱ ፋሲል ሙዚቃ በመለማመድ ላይ እያለ የሚያሰማውን እንጉርጉሮ ማድመጥ የተለመደ ነው። ይህ ታላቅ ድምፃዊ የጎንደር መሬት ለሱዳን ተላልፎ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት በተሰጠበት ወቅት “አረሱት” የሚል ዘፈን ካወጣ በኋላ በስር ዓቱ ሰዎች ወፌ ላላ ተገርፏል። ፋሲል ታዝሎ እስኪሄድ ድረስ በዚህ ፋሽስት መንግስት የተገረፈ ከመሆኑም በላይ የዳነው በህክምና ብቻ ሳይሆን በጸበልም ጭምር ነው።
ፋሲል ደመወዝ አሁን ሰሜን አሜሪካ ከመጣ በኋላ ‘እንቆልሽ” በሚለው አልበሙ ‘ያውላችሁ’ የሚል ዘፈን ያወጣ ሲሆን በዚህም ዘፈኑ ሃገሪቱን ካለምንም ተቀናቃኝ በአፓርታይድ ስርዓት ለሚመሩት ሰዎች “ሰው አስተዳደራችሁን እና በደላችሁን ጥሎ ጥሏችሁ እየሄደ ነው” ሲል ነግሯቸዋል። ፋሲል ደሞዝ በአሁኑ ሰዓት በሕወሓት አስተዳደር ከሚፈለጉ ዋና አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው።
3ኛ. ክበበው ገዳ
ኮሜዲያን ነው። በጣም ይወደዳል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያም ይቀልዳል – ክበበው ገዳ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እሱን የሚያል ኮሜዲያን አለ ብሎ ለመናገርም ይከብዳል ይላሉ በሙያው ውስጥ ያሉ ሰዎች እና ባለሙያዎች። ክበበው ገዳ በማንኛውም ማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ በመቀልድ ይታውቃል። ይህ ኮሜዲያን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የተለያዩ የኮሜዲ ሥራዎችን አቅርቦ ተመልሷል። የዘንድሮው ግን ለጉድ ነው። የሥርዓቱን ሰዎች በእጅጉ እስቆትቷል።
ባለፈው ኦገስት 2014 ላይ ክበበው ገዳ በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በዓል አስተናጋጅነት ትልቅ በዓል ላይ ተገኝቶ ነበር። ይህ ኮሜዲያን አሁን ባለው የኢትዮጵያውያን ነባራዊ ሁኔታ ዙሪያ በርካታ ቀልዶችን አቀረበ። በተለይም አሁን ባለው ስርዓት ዙሪያ ልክ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ኮሜዲያን በመሪዎቻቸው እንደሚቀልዱት ሁሉ ቀለደ። የሕዝቡን ብሶትም በቀልዱ አሰማ። ስለሟቹ ጠ/ሚ/ር፣ ስለሟቹ ፓትሪያሪክ፣ አሁን ስላለው የመንግስት አካሄድ በቀልድ አዋዝቶ አቀረበ። ለዚህ ኮሜዲያን ከሕዝብ የቀረበለት አድናቆትን ቢሆንም ከ ስርዓቱ ግን የቀረበለት ማስፈራሪያና ዛቻ ነው። እንደውም ‘ሃገርህ ትገባታለህ” የሚሉ ዛቻዎች ከስርዓቱ ደርሶታል። ክበበው ሙያውን ተጠቅሞ ባስተላለፈው መልዕክት ከኢትዮጵያ መንግስት ተላላኪዎች የሚደርስበት ማስፈራሪያ ሃገርህ ብትገባ አለቀልህ የሚል ብቻ ሳይሆን አሁን ባለበት ሃገር ሳይቀር እንደማይለቁት የሚገልጹ ናቸው።
ማነህ ባለሳምንት?
ሜሮን ጌትነትና አስቴር በዳኔ።

ሁለቱም ሴት አርቲስቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደርሰውን የሴት ልጅ ተጽ ዕኖ ተቋቁመው አደባባይ የወጡ ሴቶች። ሁለቱም ያመኑመትን ይናገራሉ። ሁለቱም በተለይ ሃገር ቤት ካሉ አርርቲስቶች የሚለዩበት ነገር አላቸው። እነዚህ አርቲስቶች ስለ እውነት እውነትን ስለመሰከሩ ዛሬ በ ሥ ር ዓቱ ሰዎች እየተነከሰባቸው ያለውን ነገር አብረን እያየነው ነው።

ሰላማዊ ትግሉ በጭፍጨፋና በውንድብና ለማቆም መሞከር ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው! – ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4191#sthash.cdt1wSCV.dpuf

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/
የተሰጠ መግለጫ

UDJ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የጥር 17/2007 በአዲስ አበባ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል። ነገር ግን ስርዓቱ ህገ ወጥ ሰልፍ ነው በማለት በአንድነት አመራሮችና አባለት ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ድብደባ ወደር የማይገኝለት ነው። እርጉዞች፣ ህፃናት፣ አዛውንቶችና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ደማቸው ፈሷል፤ አጥንታቸው ተሰብሯል። ሰላማዊ ሰልፉ ስርዓቱ እንደሚለው ህገ ወጥ አልነበረም፤ ስልፍ እንደምናደርግ ደብዳቤ ስንልክላቸው አንቀበለም ብለው ሲያንገራግሩ ደብዳቤውን እዚያ አስቀምጠንላቸዋል፤ ይህ ብቻ አይደለም በሬኮማንድ በድጋሚ ተልኮላቸው ተቀብለዋል። ህጉ አስተዳደሩ በአስራ ሁለት ሰዓት ውስጥ መልስ መስጠት አለበት ቢልም ከሰባ ሁለት ሰዓት በኋላ በሚዲያ “ሰልፉ ህገወጥ ነው” የሚል መግለጫ ከማውጣት ውጪ በደብዳቤ የመለሱት ነገር አልነበረም። በመሰረቱ በስብሰባና በሰልፍ አዋጁ መሰረት አንድ ፓርቲ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለአስተዳዳሩ ማሳወቅ ነው ያለበት። አስተዳደሩ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይል በመመደብ ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንጂ ሰልፍ መፍቀድም ሆነ መከልከል አይችልም።

አምባገነኑ የህወሀት/ኢህአዴግ መንግስት የዘንድሮውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ጭምር በማበላሸት ጠንክራ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ውጪ እንዲሆኑ ለማድረግ ላይ ታች እያለ ነው። በተለይ አንድነት ፓርቲ ላይ በምርጫ ቦርድ፣ በኢቲቪ እና በሬዲዮ ፋና የሶስትዮሽ ግንባር በመክፈት በህዝቡ ዘንድ ብዥታ እንዲፈጠር፣ ምርጫው ያለጠንካራ ተዋዳደሪ እንዲካሄድ በማድረግ የምርጫውን ዋጋ ቢስነት ከማረጋገጡም በተጨማሪ ፓርቲውን ለማፍረስ ቀን ከሌሊት እየሰራ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ስርዓቱና ምርጫ ቦርድ የጥቅም ምንደኞች በማዘጋጀት ተለጣፊ አንድነትን በመጠፍጠፍ ፓርቲውን ከእውነተኛ አባላቱና ደጋፊዎቹ ለመቀማት እጅግ አሳፋሪ የሆነ የሽፍትነት ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።
አሁንም ቢሆን አንድነት ይህን የህወሀት/ኢህአዴግ ሴራና ውንብድና በመቃወም ለሚቀጥለው እሁድ ጥር 24/2007 በአዲስ አበባና በሌሎች የተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ ሰልፍ ያድርጋል። በአዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው ሰልፍ በተለምዶ ኢትዮ ኩባ አደባባይ (ድላችን ሀወልት) ሲሆን በትናንትናው ጥር 18/2007 ለአስተዳደሩ በደብዳቤ አስገብተናል። ይህ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ሰልፍ አስተዳደሩ አሳማኝ ምክንያት አቅርቦ ተለዋጭ የጊዜ ወይም የቦታ አማራጭ እስካላቀረበ ድረስ በምንም ሁኔታ የሚታጠፍ አይደለም። አንድነት ስብሰባና ሰልፍ የማድርግ ህገመንግስታዊ መብት እስኪረጋገጥ ድረስ በህዝባዊ ንቅናቄና በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ይቀጥላል።

ድል የሕዝብ ነው!!
ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ስልክ ቁ. ዐዐ11-1- 22-62-88 ፖ.ሣ.ቁ 4222

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4191#sthash.cdt1wSCV.dpuf

Tuesday, January 27, 2015

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።

የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።
በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

andi-uk-oslo
አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don’t support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል::
እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።
ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን!
ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የወጣቶች ክፍል

Sunday, January 25, 2015

የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ዳግም የሰላማዊ ሰልፈኞችን ደም አፈሰሱ * ነብሰ ጡር ሳይቀር በቆመጥ ቀጠቀጡ (ፎቶዎች ይዘናል)

udj
udj 2
udj 3
udj 4
udj 5
udj 6
udj 7
udj 8
udj 9
udj 10
udj 11
udj1

















































































































































































































































ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተነሳው ከ 150 በላይ የሚሆን ሰልፈኛ ከጽ/ቤቱ 100 ሜ/ር ርቀት ላይ ከሚጠብቁ ከ500 በላይ ሰልፈኞች ጋር ከመቀላቀላቀላቸው አስቀድሞ የህወሓት/ኢህአዴግ ፖሊሶች ቆርጠው በመግባት ከባድ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ አራት ኪሎ፣ በፒያሳና የሰልፉ ማጠናቀቂያ በሆነው ኢቲዮ ኩባ አደባባይ ይጠባበቅ የነረው ሰልፈኛ ሊበተን ችሏል፡፡ ጉዳት የደረሰባችው 24 ሰልፈኞች ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ፖሊሶች ያደረሱትን ጉዳት በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአንድነት አመራሮችን እና ጉዳት ደርሶባቸው በየሆስፒታሉ የሚገኙ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን አነጋግረዋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ከአባላትና ከደጋፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን አንድነት በአዲስ አበባ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል፡፡ አንድነት ፓርቲ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡
የፍትህና የነፃነት ጥያቄያችን ደም በማፍሰስ አይቀለበስም!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ገዥው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድና የገዥው ፓርቲ ልሳን በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሚዲያዎች በመተባበር ከምርጫ ለማስወጣትና ተለጣፊ አንድነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ብናሳውቅም መስተዳድሩ በ12 ሰዓት ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ሰልፉ እውቅና አለው፡፡ መስተዳድሩ ግን የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደ ጎን በመግፋት የተወሰኑና የማይታወቁ ግለሰቦች ፔቲሽን ተፈራርመው አምጥተዋል በማለት ብዥታ ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ ፓርቲያችን ህጉን ጠብቆ ህጋዊ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ቢሞክርም አሁንም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ እንዳየነው ፖሊስ ደንብ ማስከበር ሲገባው አድሎ ለፈፀመው አካል በመወገን ድብደባ መፈፀሙ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን እንድናረጋግጥ አድርጎናል፡፡

ጥያቄያችን አሁንም የፍትህ፣ የእኩልነትና ህግ እንዲጠበቅ የማድረግ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ የመንግስትነት ስልጣኑን በመጠቀም የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም እየከወነ ያለውን ሴራ ማስቆም ነው፡፡ ጥያቄያችን የነፃነትና ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲ ይረጋገጥ የሚል ነው፡፡
ጥቄያችን ምርጫ ቦርድ የገዥው ፓርቲ አጋር መሆኑ ቀርቶ ገለልተኛ ሚናውን ይወጣ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ደም በማሰስ፤ በድብደባም ሆነ በእስር ፈፅሞ አይቆሙም፡፡ ትግላችን የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ እስከሚያበቃ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንትም በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሰላማዊ ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!