Monday, October 13, 2014

በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ  በመዠንገርና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል በተነሳው ግጭት ብዙ ነዋሪዎች መገደላቸው ተሰማ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቴፒ አካባቢ በመዠንገር ብሄረሰብና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ህዝብ ካለቀ በሁዋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ለጊዜያው ያበረደው ቢመስልም፣ ግጭቱ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ አቅጣጫ ተዛምቶ እስካሁን ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶችም በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የተነሳው ግጭት በማየሉ፣ በተለይ ... Read More »

በአዳማ በተደረገው የኢህዴድ ግምገማ አባላትና አመራሩ ተዘላለፉ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ከኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከየከተማው እና ከየወረዳው የተውጣጡ ከ300 በላይ አባላት በተሳተፉበት ግምገማ በአመራሩና በአባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እርስ በርስ መዘላለፍ ደረጃ ደርሰው እንደነበር በስብሰባው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማው የተመራው በአዳማ ከተማ ከንቲባ ሲሆን፣ ከንቲባው ቀደም ብለው ያዘጋጁዋቸው አባላት በምክትሉ ከንቲባ በአቶ አህመድ የሱፍና በድርጅት ጉዳይ ሃላፊው በአቶ ፍቅሩ ጂረኛ  ላይ ... Read More »

መንግስት የ20 በ80 አሰራር እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላለፈ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የ20 በ80 አሰራርን ተግባራዊ እንዲያድረጉ ታዘዋል። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ጊዜያቸውን ለመንግስት ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ለሚሰሩዋቸው ስራዎች እንዲያውሉ ተነግሯቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነው የሰው ጉልበት፣ ባጀት፣ ጊዜና የመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ ለምርጫ ማደራጃ፣ ለአባላት ቅስቀሳና ማደራጃ እንዲውሉ ... Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በኢምባሲ ውስጥ ገብተው የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን እንዲከሰሱለት ጠየቀ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የአሜሪካ መንግስት የአገሪቱን ሰንደቃላማ በአወረዱ  ተቃዋሚዎች ላይ ክስ ይመሰርታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ቃል አቀባዩ ተቃዋሚዎቹ ከኤርትራ መንግስት እና ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱን አለመወጣቱን የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ ተቃዋሚዎቹን ለፍርድ ያቀርባል ብለው እየጠበቁ መሆኑንም አክለዋል። አምባሳደር ግርማ ብሩ ተቃዋሚዎቹ ክስ ... Read More »

የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች የ8 ቀን ስልጠና ቅጣት ተጣለባቸው ሲል ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን እንዲሰለጥኑ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የዘገበው ነገረ ኢትዮጵያ፣ ከመስከረም 19/2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 4 ሺ 100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ መደረጉን አስታውሷል፡፡ ... Read More »

አምባሳደር ሚኒልክ የስራ መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄነቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፅ/ቤት ባለሙሉ ስልጣን በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታሁን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ማግኘታቸውን ተከትሎ  ሃላፈነታቸውን መልቀቃቸውን  ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል። የኢህአዴግ ዋና ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው አምባሳደር ሚኒልክ ፣ ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ በመቆየታቸው ” ታጋይ ሚኒልክ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ... Read More »

መንግስት የባንዲራ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ጀምሯል።

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከሚፈስባቸው የመንግስት ክብረ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የባንዲራ ቀን ዘንድሮም ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓም በአዲስአበባ ስታዲየም በድምቀት እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል። “በሕዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯን እና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር!” በሚል መሪ ቃል  ለ7ኛ ጊዜ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከአዲስአበባ ... Read More »

በአዋሳ አንድ ባለሀብት ጠበቃ ገድለው ተሰወሩ

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ ባለሀብቱ የመንግስት ታክስ አልከፈሉም ተብለው ... Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች በመሰረተ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኋላ መቅረታቸውን  የወረዳ አመራሮች  በግልጽ በማቅረባቸው ከክልልና ዞን ባለስልጣናት ግሳጼ እንደደረሰባቸው ተናገሩ፡፡

መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ህብረተሰቡ ምን ይለናል የሚለውን ለማዳማጥ ከሰሜን ጎንደር ከተሰባሰቡ የወረዳ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ የወረዳ አመራሮች በንባብ እንዲያሰሙት ከየዞን ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ማስታወሻና አቅጣጫ ወደጎን በመተው መንግስት እንዲያስተካክላቸው በጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ምክንያት ከስብሰባው በኋላ ወከባና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ለከፍተኛ አመራሮች ... Read More »

“ሰራዊታችን ህብረብሄር ሆኗል” ሲል ኢህአዴግ ገለጸ

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች  እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ”  በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ እያለና በመጀመሪያዎቹ አመታት ከትግሉ ... Read More »
Link:-http://ethsat.com/amharic/

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.