Tuesday, February 25, 2014

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ጠረፍ ግጭት ተቀሰቀሰ! 71 ኢትዮጵያውያን ሞቱ! “ድረሱልን” እያሉ ነው!

ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ሲሉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ገለጹ::
ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢትዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን ይድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።
አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።

Sunday, February 23, 2014

ዛሬ በባህርዳር የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ፤ ሕዝቡ በባዶ እግሩ በመውጣት በብአዴን/ኢሕአዴግ ላይ ቁጣውን ገለጸ







(ዘሐበሻ) የአማራው ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን የሚመሩትን የአማራ ሕዝብ በጸያፍ ቃላት መሳደባቸውን ተከትሎ አንድነትእና መኢአድ ፓርቲዎች በጋራ በባህርዳር ዛሬ በባህርዳር የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በሰላም ተጠናቀቀ። “ህዝቡ ከባዶጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።
በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች ቁጣቸውን ለመግለጽ በወጡበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በአቶ አለምነው የተሰደበውን ለማስታወስናቁጣውንም ለመግለጽ በባዶ እግሩ እንደነበር ከስፍራው መረጃ ያደረሱን የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ገልጸዋል። “ሰልፈኛው ጫማውን አንገቱ ላይበማንጠልጠል በሰላማዊ ሁኔታ በባዶ እግሩ በመሄድ በአዲስ የተቃውሞ ስልት ድምጹን አሰምቷል” ያሉት በስፍራው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎችእንዲህ ያለው የትግል አገላለጽ የሚደነቅና ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል።


ባህር ዳር በፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭተው የዋሉ ሲሆን ከከተማዋ አጎራባች አካባቢዎች ጭምር የተሰባሰቡት ልዩ ሃይሎችናየክልሉ ፖሶች በነዋሪው ላይ ውጥረት ለመፍጠርና በሰልፉ እንዳይሳተፍ በከፍተኛ ሁኔታ ቢሞክሩም ሕዝቡ ግን በአቶ አለምነውና በብአዴን ላይቁጣውን ከመግለጽ አላገደውም ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች “ወያኔ ለውድቀቷ አማራን ትሳደባለች” በሚል ቁጣ ካለምንም ፍራቻ አደባባይ ወጥተዋልብለዋል።


በተለይ ኢሕአዴግ በባህር ዳር ከተማ ሕዝቡ ሰልፍ እንዳይወጣ በ5ለ1 ጠርናፊና ተጠርናፊዎች “ሰልፉ ተሰርዟል” የሚል ሃሰተኛ ወሬ በማውራትሕዝቡን ለማደናገር መጣሩን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የአንድነት እና የመኢአድ መሪዎች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ በመኪና እና በ እግርበመሄድ ሕዝቡን በመቀስቀስ የዛሬውን ሰልፍ ለስኬት አብቅተውታል ሲሉ ዘግበዋል። በተለይም የከተማዋን የባጃጅ ሾፌሮችን በማህበራቸውአማካኝነት ኢሕአዴግ ሰብስቦ ይህን ሰልፍ የምታጅቡ ከሆነ ፈቃዳችሁን ትቀማላችሁ የሚል ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም አቶ አለምነው አማራውንከሰደቡት ስድብ አይበልጥም በሚል ባጃቻቸውን አስቀምጠው ሰልፉን መቀላቀላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል።