Saturday, September 21, 2013

በፀረ-ሽብርተኝነት ውይይት ላይ የግል አስተያየት

በሰኞ እና ማክሰኞ በተከታታይ ምሽት በፀረ ሽብርተኝበት አዋጅ ላይ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት
ላይ ያለኝ አስተያየት ይህ ነው፡፡
ሲጀመር ማንነቴን በማያሳይ የኢሜል አድራሻ ስለላኩኝ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ይህንንም ያደረኩበት ምክንያት አስተያየት በመሰጠቴ ብቻ
ልታሰር፣ልታገት፣ልገደል፣ቤተሰቤ ሊጉላላ፣ልሰደድ፣በገዥው ፓርቲ እስር ቤት ኮርማዎች ግብረ ሰዶም ሊፈጸምብኝ ይችላል የሚል ስጋት
ስላለኝ ነው፡፡ይህም ስጋቴ የመነጨው አካላቴ ከቆቅ ስጋ ስለተሰራ ሳይሆን በተግባር ብዙ ንጹሀን ኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጸም ስላየሁ
ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የዚህ አወዛጋቢ የሽብር ህግ ውይይት ጋሪው ከፈረሱ የቀደመ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ይህ ህግ ከዛሬ አመት እና ከዚያ
በላይ በፊት ፓርላማ ቀርቦ በቀድሞው ጠ/ሚ አቅራቢነት ጸድቋል፡፡ከጸደቀም በኋላ ተግባራዊ ተደርጎ ብዙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በዚሁ
ህግ ትርጓሜ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ አሁን ህጉ ላይ ፓርቲዎች ያላቸውን አስተያየት መጠየቅ ቅድም እንዳልኩት ጋሪው
ቀድሟል፡፡ከፈረሱ፡፡
ይህ ህግ አሁን ከፓርቲዎች ውይይት በኋላ እንኳን ይሰረዝ ወይም ይሻሻል ቢባል በዚህ ህግ ምክንያት ለእስር የተዳረጉ እና በሽብርተኝነተ
የተወነጀሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶ ጉዳይ እንዴት ሊታይ ነው፡፡በምን ምክንያት ታሰሩ ተወነጀሉ ሊባል ነው፡፡ ሰዎቹ እና ድርጅቶቹ
ለሚያቀርቡት ጥያቄ ምን መልስ ሊሰጥ ነው፡፡
ይህንን ካልኩ ዘንድ ወደ በውይይቱ ላይ ወዳለኝ አስተያየት ልግባ፡፡
በቴሌቭዥን መስኮት እንዳየሁት ገዥው ፓርቲ በሁለት ሰው ተወክሏል ሌሎቹ በአንድ ሰው ነው የተወከሉት፡፡ይህ ለም ሆነ ፡፡አቶ ሽመልስ
የኢሃዲግን ሃሳብ በደንብ ማስተላለፍ ስላልቻሉ ከሆነ አጋዥ የተደረገላቸው አንድ ብቁ ሰው ቢቀርብ ካልሆነ አድሎአዊ ይመስላል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ በአነሱት ነጥብ ላይ እኛ አገር ሽብርተኛ ብለን የፈረጅናቸው ሰዎች በአውሮጳ በአሜሪካ
ምሁራን ናቸው ላሉት አቶ ሽመለስ ሲመልሱ አሚሪካ ካላት የስጋት ደረጃ እና የሽብርተኝነት ህግ አንጻር የተጠቀሱት ግለሰቦች
በሽበርተኝነት ባትፈርጃቸውም ለእኛ ግን የሽብር ስጋቶች ናቸው ብለዋል፡፡ነገር ግን ነብሳቸውን ይማረውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር
አቶ መለሰ ዜነዊ በአንድ ወቅት ስለ ጸረ ሽብር ህጉ በፓርላማ መግለጫ ሲሰጡ ምርጥ ከተባሉ የጸረ ሽብር ኅጎች ቃል በቃል እንደተወሰደ
ነበር ያስረዱን፡፡እንዴት ይህ ቃል በቃል የተወሰደ ህግ አፈጻጸሙ የተለያየ ሆነ፡፡ጥያቄ ነው፡፡
በመጨረሻ በቴሌቪዥን የታየውን ፊልም አስመልክቶ አቶ ሽመልስ ላነሱት ተቃዋሚዎች ድራማ ነው ይላሉ ላሉት ለተቆራረጠ
አካል የማይሳሳ የሰው ልጅ የለም:: የአቶ ሽመልስ አንጀት እንደሚሳሳ ሁሉ ጥቃቱንም የፈጸመው አካል አንጀት አለው፡፡አቶ ሽመለስ ልጅ
እንዳለቸው ሁሉ የኦነግ መሪም ልጅ አላቸው፡፡ጥቃቱን የፈጸመው አካል እነዚያን ተቆረረጡ የሰው ልጅ አካሎች አንበሳ ጅብ ወይም ነብር
ሆኖ አይበለቸውም ግን አንደ የተከፋበት ነገር እንደለ የሚያስረዱ ምስክሮች ናቸው፡፡ስለዚህ እነዚህ የሽብር ተግባራት ለምን ተፈጸሙ ማን
ምን ከፍቶት ፈጸማቸው ብሎ ታላቁ መሪ እነደሚሉት ዘላቂ መፍትሄ መስጠቱ ይበጃል፡፡ ነግር ግን ሰው የተከፋበትን ነገር ሳያውቁ
ሽብርተኛ ነው ቢሉት ውጤቱ ይከፋል፡፡ሰው ካልበላው አያክም፡፡
አሁን ያስታወስኩት ደግሞ ይህ ነው፡፡ማንም ኢትዮጵያዊ አባይን ሚያክል ውሃ ያላት አገር ውስጥ ያለ እና ፊደል የቆጠረ አገሪቱ
ሽብርተኝበት አያሰጋትም የሚል የለም፡፡አራቱም ተቃዋሚዎች ይህንን ኣላሉም ነገር ግን ገዥው ኣካል ሽብተኝነት ህጉን በአሸባሪዎች ላይ
ተግባራዊ እያደረገው አደለም፡፡እንደውም ዋነኞቹን ሽብረተኞች ትቶ ስልጣኔን ሊቀሙኝ ይችላሉ ብሎ በሚያስባቸው እራሱ ፈቅዶ
እንዲደራጁ ባደረጋቸው ተቃዎሚዎች እና ሃሳባቸውን በነጻነት ለመግለጥ በሚፈልጉ ዜጎች ላይ ነው ተግባራዊ እደረገው ያለው ነው እያሉ
ያሉት፡፡ለምሳሌ እኔ አሁን በግልጽ ብገኝ ሽብርተኛ እንደምባል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም፡፡
አቶ ሽመልሽ እስላማዊ መንግስት ማቋቋምን እንደ ሽብርተኝነት ወስደውታል፡፡ በራሱ እስላማዊ መንግስት መመስረተት
ሽብረተኝነት አይደለም፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ህዝብ እስላማዊ መንግሰት እፈልጋለሁ ካለ መብቱ ነው ፡፡መንግስት ህዝቡ አይደለም
እስላማዊ ሰይጣናዊ መንግሰት እፈልጋለሁ ብሎ በድምጹ ካረጋገጠ ምን አገባው፡፡አሁን ኢሃዲጋዊ መንግሰት እፈልጋለሁ ስላለ አደል እንዴኢሃዲግ ስልጣን ያያዘው፡፡ስለዚህ የሰዎች የተፈጥሮ ሰብአዊ መብት አይነካ እነጂ ማንኛውም አይነት መንግሰት በየትኛውም አገር በህዝብ
ይሁንታ መቋቋም ይችላል፡፡
አቶ ሙሼ በሰጡት አስተያየት ላይ የታዘብኩት ነገር ስለ ቀይ ሽበር አንስተው ካወገዙ በኋላ ስለ ነጭ ሽብር ግን ማንሳት እልፈለጉም፡፡
በግዜው ቀይ ሽብር በደርግ መሪነት ነጭ ሽብር በኢሃፓ መሪነት ተፈጽመዋል ፡፡በእርግጠኝነት የአቶ ሙሼ እድሜ ፎርዋርድ ተደርጎ ካልሆነ
ወይም ኢሃፓ ካልሆኑ በስተቀር ነጭ ሽብር እነደነበረ አይረሱትም፡፡አቶ ሙሼ ግን ኢሃዲግን ስለሚፈሩት እሱ የማይወደውን ነገር
ከማንሳት ተቆጠቡ፡፡ይህ የሚያሳየው እራሳቸው አቶ ሙሼ ሽብር ውስጥ እንዳሉ ነው፡፡ገና አእምሮአቸው ነጻ አልሆነም ስለዚህ በተቻለ
መጠን መጀመሪያ ነጻ የሆኑ ሰዎች ቢቀርቡ፡፡
ሌላው ከፕሮግራሙ አቀራረብ የተረዳሁት ነገር ቢኖር የመደረኩ ተወካይ በሁለተኛ ዙር ላይ አስተያታቸውን ሲያቀርቡ ንግግራቸው
ሳይልቅ ተቆርጧል፡፡ኢዲት እንደተደረገ ያስታውቃል፡፡ስለዚህ ውይይቶች ሳይቆራረጡ ቢቀርቡ፡፡
በስተመጨረሻ የአንድነት ተወካይ ያነሱት መሰረታዊ ጥያቄ አለ፡፡በዚህ አሸባሪ ህግ ላይ አሌ የማይባል የህግ እና የህግ መሰረታዊ ጽንሰ
ሃሳብ መፋለስ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡የአሸባሪ ህጉ አውጭ እና ተርጓሚው አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ይህ ነገር እውነት ከሆነ በእውነቱ እኛየኢትዮጵያ ነዋሪዎች በፍትህ ደረጃ ገና አካሄዱ እንኳ አልገባንም ማለት ነው፡፡በእውነቱ ህግ አውጭ እና ተርጓሚ አንድ ከሆኑ ህግ የለም
ማለት ይቀላል፡፡ስለዚህ ኢሃዲግ እዚህ ላይ ፈጣን መልስ ቢሰጥ፡፡
ሌላው በእውነቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይህንን ፕሮግራም ማስተላለፉ ያስመሰግነዋል፡፡ስርጭቱ ቢደገም እና በክልል ጣቢያዎችም
ቢተላለፍ ማህበረሰቡ እንዲወያይበት ደርገዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ከውይይቱ የተረዳሁት ድምዳሜ፡፡
ድምዳሜ አንድ
ከውይይቱ የመጨረሻውን ድምዳሜ እንደተረዳሁት ኢሃዲግ ለሚቀጥለው ምርጫ ስጋት እንዳለበት በጣም ያሳየ ነው፡፡
ድምዳሜ ሁለት፡
ኢሃዲግ በድምዳሜ አንድ እንዳስቀመጥኩት ለሚቀጥለው ምርጫ ስጋት ስለያዘው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከአመት በፊት በጸደቀ ህግ ላይ
ካወያየ በኋላ እነዚህን የተቃዋሚ ፓርቲዊች መሪዎች እና አባላት የጸረ ሽብር ህጉን አልደገፉም በመሆኑም ሽብረተኞች ናቸው ብሎ ቃሊቲለማውረድ እንዳቀደ ከውይይቱ ተረድቻለሁ፡

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.