Monday, December 15, 2014

ኢሳት ይቀጥላል!

ኢሳት ይቀጥላል! 

በኖርዌይ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ በሆነችው በርገን ከተማ ለመጀመርያ ጊዜ ቅዳሜ ዲሴምበር 13/2014 ኢሳት ይቀጥላል በሚል መርህ ልዩ የኢሳት ምሽት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዝግጅቱም ላይ የኢሳት ጋዜጠኞች አበበ ቶላ/አቤ ቶኪቻው/ ፥ ገሊላ መኮንን እና ፍስሃ ተገኝ በተጋባዥነት የተገኙ ሲሆን፥ በኢሳት ኖርዌይ የበርገን ተወካዮችና ለዝግጅቱ ባዋቀሯቸው በርካታ የኮሚቴ አባላት ታላቅ ብርታት የተሳካና አስደሳች ምሽት እንዲሁም ትልቅ ውጤት የተገኘበት ሲሆን በተጨማሪም በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በመሰባሰብ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ነበሩ፥፥

በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች በተጋባዥ እንግዶቹ እና ባዘጋጅ ኮሚቴው የቀረቡ ሲሆን፥ ለኢሳት የተዘጋጀ ኢሳት ይቀጥላል የተባለ አዲስ መዝሙር በ አቶ ማርቆስ ተገጥሞ፥ በአቶ ቶማስ አለባቸው ዜማው ተሰርቶ በአቶ ኢሳያስ ተቀነባብሮ ባስደሳች ሁኔታ ከተለያዩ ከተሞች በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ሲሆን፥ እንዲሁም በአቶ አይንሸት የተደረሰው የሳኦል ፍሬዎች በሚል ርእስ እየተዘጋጀ ያለ አዲስ ፊልም ባጭሩ ለተሳታፊው የቀረበ ሲሆን፥ በቅርብም ስራው ተጠናቆ ለህዝብ እንደሚቀርብ ታውቋል፥፥

በዝግጅቱ ላይ የተሳታፊውን ቀልብ ስቦ የነበረው የግማሽ ማራቶን እሯጭና የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት እንደዚሁም በሚሮጥባቸው መድረኮች ላይ የኢሳትን አርማ በመልበስ እንዲሁም የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን ስርአት የሚያሣዩ መፈክሮችን በማንገብ የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት የሆነው አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ፥ የኢሳትን ቲሸርቶች ለብሶ ካሸነፈባቸውና ከተሸለማቸው በርካታ ሽልማቶች መካከል ሁለት ዋንጫዎችን፥ አንደኛውን ለዝግጅቱ ጨረታ እንዲውል እንዲሁም ሁለተኛውን በኢሳት ስቱዲዮ ያበረከተ ያበረከተ ሲሆን፥ ለታዳሚውና ለመላው የኢትዮጰያ ህዝብ የኢሳትን ወሳኝነትንና ሁሉም የበኩሉን እንዲረዳ በመልእክቱ ላይ አስተላልፏል፥፥

በዚህ አጋጣሚ የኢሳት ኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ ሰብሳቢዎች አቶ ሰለሞን አሸናፊ፥ አቶ ዳዊት እያዩና አቶ ሺበሺ ጌታቸው፥ እንደዚሁም ለመላው የአዘጋጅ ኮሚቴዎች፥ ለተጋባዥ እንግዶችና ጋዜጠኞች አቤ ቶኪቻው፥ ፍስሃ ተገኝና ገሊላ መኮንን እንደዚሁም በመላው ኖርዌይ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፥ ዝግጅቱን የተሳካ ለማድረግ የበኩላችሁን ያበረከታችሁ፥ እንደዚሁም በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ ከተሞች በመጓዝ የተሳተፋችሁና፥ በተለያዩ ምክንያቶች ለመሳተፍ የልቻላችሁ ግን ትኬት በመግዛትና የተለያዩ ተሳትፎዎችን ላደረጋችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ የኢሳት ኖርዌይ እና የኢሳት ኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ ታላቅ ምስጋናውን ያቀርባል፥፥

ኢሳት ይቀጥላል!

ኢሳት ኖርዌይ (8 photos)

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.